የቀድሞው የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት በአሁኑ ጊዜ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ አያሌው ጎበዜ ወደ ሀገር ቤት ከተጠሩ በኋላ በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቢመደቡም በራሳቸው ፈቃድ ከመንግስት ስራ መልቀቃቸው ተሰማ

አምባሳደር አያሌው ጎበዜ የአማራ ክልልዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ሆነው ለ7 ዓመታት እንዲሁም በተለያዩ የስራ ሀላፊነቶች ክልሉን ለበርካታ ዓመታት በቅንነት አገልግለዋል ።
ከአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድርነት ከተነሱ በኋላ በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አያሌው ጎበዜ በብአዴን አመራርነታቸው ጊዜ የሕወሀት ጣልቃ ገብነት በስራቸው ላይ ጫና ያደርግባቸው ስለነበር ክልሉ ለተለያዩ ጉዳቶች ተዳርጓል ። ይሁንና በበጎ ስራቸውና ህዝብን ለማገልገል ባላቸው ቀናነትም ይታወቃሉ።
አምባሳደር አያሌው ጎበዜ በባሕር ዳር ለመኖርያ ቦታ ግንባታ በማህበር ከህዝብ ጋር ተደራጅተው በከተማው ቀበሌ 14 በተሰጣቸው ቦታ 
በገንዘባቸው ሰርተው ለማጠናቀቅ የፈጀባቸው ጊዜ 8 ዓመት እንደሆነ ይነገራል ።
ልጆቻቸውን እንደማንኛውም ህብረተሰብ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ያስተማሩት አምባሳደር አያሌው ጎበዜ የመንግስት ተሽከርካሪን ለቤተስቦቻቸው አገልግሎት የማይጠቀሙ ሀቀኛ ሰውም ናቸው።
በአሁኑ ጊዜ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ቢመደቡም ከመንግስት ስራ በራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል።አምባሳደር እያሌው ጎበዜ በጡሮታ ዘመናቸው መልካም ጊዜ እንዲገጥማቸው እንመኛለን።

ጢስ አባይ ገንጂ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.