የ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም ጉዳይ

ታዋቂው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም  ከዚህ ዓለም ሐምሌ 2010  በሞት መለየቱ ይታወቃል ፡፡ ቀደም ሲል የኩላሊት ህመሙን ለመታከም  ከአገር ውስጥና ከውጭ የሚገኙ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ ገንዘብ አዋጥተውለት እንደነበርም ይታወቃል፡፡  
    ነገር ግን ከውጭ አገር  በ  አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በኩል የተሰበሰበው  ገንዘብ የት እንደገባ  ያልታወቀ ሲሆን ፣ በሚያሳፍር ሁኔታ ግለሰቡ  ሀውልቱን ለማሰራት እንኳ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል፡፡
          በ አቶ ቴዎድሮስ ተሾመ በኩል ያለው ጉዳይ ተስፋ አስቆራጭ በመሆኑ  ከአገር ውስጥ  ለተሰበሰበው ገንዘብ በአቶ ሀይሉ ከበደ (ሮህቦት ፕሮሞሽን) ሰብሳቢነት የሚንቀሳቀሰው ኮሚቴ በተመሳሳይ  ለ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም  መታሰቢያ ሃውልት ለማሰራት በቤተሰቡ በኩል ጥያቄ ቢቀርብም ሰብሳቢውና አባላቱ በቂ ምላሽ ሳይሰጡ ሁኔታውን በማድበስበስ ላይ ይገኛሉ፡፡
       አሁን የአርቲስቱ ቤተሰቦች የሆንን የመቃብሩ ቦታ እየተረገጠ እና መታሰቢያ ሳይደረግለት በመቅረቱ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንገኛለን በመሆኑም ቦታው ጨርሶ ሳይረሳ ለግዜው በገመድ ያጠርነው ሲሆን ይህ የህዝብ ኩራት የነበረ አርቲስት በጥቂት ወዳጅ ነን ባዮች ክፋት ክብር ሳያገኝ በመቅረቱና   የተሰበሰበው ገንዘብ በሰበብ ባስባቡ ተበልቶ ከመቅረቱ በፈት በሚዲያችሁ ለኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳዩን ይፋ እንድታደርጉትን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡ የ መቃብሩን የታህሳስ 15 ቀን  2011 ዓ.ም ፎቶ ከዚህ መልዕክት ጋር ተያይዟል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ካስፈለጋችሁ  +251911445856   ወይም     + 251 911 8643 96      +251911675177 ይደውሉ
ቤተሰቦቹ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.