በሰሜን እዝ ከትግራይ መውጣት ፊታችሁን አትንጩት፤ ገና ብዙ ያላወራረድነው ቀሪ ሂሳብ አለን (አያሌው መንበር)

የኢትዬጵያ መከላከያ ከሰሜን (ከትግራይ) ወጥቶ ወደ መሃል አገር መግባት ጉዳይና አንድምታው፦

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እዝ ብዛት ከስድስት ወደ አራት ዝቅ ማለቱን ከሳምንታት በፊት ሰምተናል።
ይህ ውሳኔ ጠ/ሚኒስትሩ ከወሰናቸው ውሳኔዎች ሁሉ የተሻለ በሚል በአጭሩ መግለፄን አስታውሳለው።
ምክንያቱም የመከላከያ ሰራዊት የእዝ መብዛት ያመጣው ለውጥ የለምና። ይልቁንም በምትኩ የሰሜን እዝና በዙሪያው ያሉ ክፍለ ጦሮች የተሰጣቸውን ሚሽን እየተወጡ እንዳልሆነ እና ለጠላት መውጊያ ሳይሆን ለአመራርና ቡድኖች ጥብቅና እየቆሙ ነበርና።
መከላከያውን ቁመና ያጠነክረዋል ተብሎ የተከፈቱ እዞች ወደ አድገኛ ሁኔታ እየገቡ ነበር።

ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ በሰሜን በኩል እንደ ሀገር ስጋት የለብንም።ኤርትራ የአምሳላችን ክፋይ ናት።ከኤርትራ ጋር ብንኮራረፍ እንኳን በመከላከያ ሀይል መፈታት አለበት የሚል እምነት የለኝም።በተለይ አሁን ከኤርትራ ጋር ወዳጅነታችን ጠንክሯል።ስለሆነም ሪሶርስ ማባከን ነበርና በሰሜን በኩል እዝ አስፈላጊ አይደለም።

ጠ/ሚኒስትሩ እነዚህን እና ሌሎች ምክንያቶችን ግምት ውስጥ አስገብቶ የእዞችን ቁጥር ሲቀንስ ሰሜን እዝ ከታጠፉት መካከል ነው።ይህ ትክክለኛ ውሳኔ ነው።የስጋት ቀጠና ባልሆነ ቦታ መከላከያን እስከ ሙሉ ሪሶርሱ እዛ መድቦ ማስቀመጥ የሀገርን ሀብት እንደማባከን ነው የሚቆጠረው።ህወሃት ሀገራዊ ራዕይ ስለሌለው እንጅ እንደ ሀገር ማሰብ ቢችል ይህንን በደንብ መደገፍም ነበረበት።

ታድያ የሰሜን እዝ መታጠፍ እና የመከላከያው ሀይል እስከ ትጥቁ መውጣት የትግራይ ፖለቲከኞችን ለምን አንጨረጨረ? ብለን ስንጠይቅ ምክንያቱ ግልፅ ነው።

የሰሜንን እዝ ማጠፋ ዋናው ምክንያት ከኤርትራ ጋር ሰላም መሆናችን እንዲሁም ሪሶርስ ለመቆጠብ ብቻ አይመስለኝም።ይልቁንም የህወሃት እና ብአዴን ጡረተኞችን በሰሩት ወንጀል ልክ በህግ አግባብ ለመጠየቅም ጭምር እንዲያግዝ ታስቦ ይመስለኛል።
ሀገር ሻጭ ባንዳዎችና ህዝብ ላይ ጅምላ ፍጅትን ያቀነባበሩ ሁሉ ዛሬ ጉዳዩ ጠበቅ ሲል “እኔ እኮ ትግሬ ስለሆንኩ ነው፣እንዲህ ያደረገን ሻዕቢያ (ኢሳያስ) ነው፣ CIA ነው” ምናምን እያሉ ወንጀልን በሌላ ለማሳበብ እንዲሁም በህዝብ ጉያ ውስጥ ለመደበቅ ሲሞክሩ ተመልክተናል።እነዚህ ሰዎች በህግ ይጠየቁ ቢባል ባላቸው ኔትወርክ አማካኝነት ልክ እንደዚህ በፊቱ መከላከያውን abuse በማድረግ ሀገር የመጠበቅ ተልዕኮውን እንዳይወጣ ሊያደርጉ ይችላሉ።ሰሞኑን በትግራይ አርሶ አደርና ሚሊሻ እጅ የታዩ የከባድ ጦርነት መሳሪያዎች ምንጫቸው መከላለያው ነው ማለት ይቻላል።የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብቻ ሊይዘው የሚችለው መሳሪያ በትግራይ ክልል አርሶ አደር፣ሚሊሻና ልዩ ሀይል ተይዞ ተመልክተናል።ይህ ትልቅ የሀገር ክህደት፣የሀገር ሀብት ብክነትና የማዕከላዊ ሉዓላዊ መንግስት ስጋት ነው።ከመከላከያ ግምጃ ቤት የወጣ መሳሪያ ነው ተብሎ የሚገመት ነው የታጠቁት።ይህ ደግሞ ምክንያቱ መከካከያው ነው።መፍትሄውም መከላከያውን አስተሳሰቡን እያሳደጉ ማሻሻያዎችን መስራት ነው።አብይ ይህንን ነው እየሰራ ያለው።
እናም የእነዚህን ሰዎች እጅ መቁረጥ የሚቻለው አንዳንድ ማሻሻያዎችን በማድረግ ነው።

ስለሆነም ወደድንም ጠላንም የሰሜን እዝ መዘጋት ተጨማሪ ምክንያት ህወሃቶች ወንጀላቸውን ለመደበቅ ወደ ህዝብ መመሸጋቸውና የትግራይ ህዝብም የወለደ አንጀት ሁኖበት ወንጀለኛን በጉዳያው አቅፎ ደግፎ መያዙ ነው።
ይህ ግን ህወሃትንም ሌላውን ትግሬም ያስደሰተ አይመስልም።

ትግራይ ራሷን እንደ ሀገር የምትቆጥር፣በኢትዮጵያውያን ንብረት ክልሏን የገነባችና አሁንም በኢትዮጵያውያን ጉሮሮ እና ደህንንነት ላይ ቁማ እኔ ብቻ ልብላ የምትል ቀናኢ ፖለቲከኛ ያላበቀለች እርጉም ምድር ሆናለች።
በዚህም ምክንያት አይኗ ከአሸንጌ ሀይቅና ከተከዜ ማዶ የሚያየው ለፍቅርና ለጋራ ብልፅግና ሳይሆን ሌሎችንን አጥፍቶ ራስን ስለማበልፀግ ነው።ራስ ወዳድነቷ በሌሎች መጥፋት ላይ ብቻ የተቃኘ የስስታሞችና የቅናተኞች ስብስብ ናት።
እናም በሚያሳፍር ሁኔታ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በክልል ለማዘዝ ስትሞክር እናያለን።እርግጥ ለእርሷ ይህ አዲሥ ተግባር አይደለም።የመከላከያ ጀነራሎችን እየተጠቀመች ዘርፋለች፣ሀገር ሽጣለች፣ንፁሃንን አሰቃይታለች።ዛሬ በአፀፋው መቀጣት ሲገባት እርሱ ይቅር ቢያንስ ወንጀለኞች ይጠየቁ ሲባልም እነርሱን ለመሸሸግ ነው ክንፏን የዘረጋች።
እናም ሰሞኑን የምናየው የቁራ ጩኸትና መንፈራገጥ ምንጩ ይህ ነው።

ምን ይከሰት ይሆን?

አንድ ክልል የሀገር መከላከያ ሰራዊትን (ሰውንም ትጥቁንም) የመቆጣጠር ቀርቶ የመጠየቅ መብት የለውም።ይህ የማዕከላዊ መንግስቱ ስልጣን ነው።ትግራይም ያላት አማራጭ በተወካዮቿ በኩል በኢህአዴግ ቤት አልያም በፓርላማ ቅሬታዋን ማቅረብ ነው።ያነሳችው ሃሳብ እንደሀገር ትክክለኛ ስጋት ከሆነ ሊታይ ይችላል።ካልሆነ ግን እዙ ወደ መሃል አገር የማምጣቱ ጉዳይ ይቀጥላል።
በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ መከላከያው ለምን ወጣ እያሉ ሲያለቃቅሱ እያየን ነው።እነዚህ ሰዎች 27 ዓመት ሀገር መርተው የማዕከላዊ መንግስትን ሀላፊነት የማያውቁ፣ ራሳቸው ያረቀቁትንና ያፀደቁትን ህገ መንግስት እንኳን ለማክበር ፈቃደኛ ያልሆኑ፣ሁልጊዜ እኔ እንጅ እኛ የሚባል. ነገር ያልፈጠረባቸው ናቸው።ዳሩ ግን ምንም ማድረግ አይችሉም።ያላቸው ምርጫ መጮህ ብቻ ነው።ጩኸታቸው ይቀጥላል።

በነገራችን ላይ ባለፈው የተነገረን የሆነ ክልል ውስጥ ሁለተኛ የሀገሪቱ ቴሌ እና ደህንነት ሰርቨር ያለ መንግስት ፈቃድና እውቅና አለ የተባለውስ መቸ ነው ወደ ማዕከላዊ መንግስት አስተዳደር የሚመለሰው?

ሀዘናችሁን አትጨርሱት ገና ብዙ ቀሪ ሂሳብ አለን በሉልን።

((N.B መከላከያን ለደቂቃ እንኳን ማገድ የሚያስከፍለው ዋጋ ቀላል አይሆንም።ቢያንስ አሟሟታችሁን ብታሳምሩ መልካም ነው።))

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.