ሕወሃት ካድሪዎችን አሰማርቶ ከባባድ መሳሪያ ከትግራይ እንዳይወጣ ለማድረግ ሞከረ

ከኤርትር ጋር በነበረው ጦርነትና አለመረጋጋት ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት ከከፍተኛ ክባባድ መሳሪያዎች በትግራይ ይገኙ እንደነበረ የሚታወሰው ነው። ሆኖም በአንድ በኩል የዶ/ር አብይ አስተዳደር ከኤርትራ ሰላም እንዲሰፍን በማድረጉ ከፍተኛ የጦር ሰራዊት ክምችት በትግራይ ባለማስፈለጉ፣ ሁለተኛም በኦሮሞ ክልል ኦነግና አክራሪ የኦሮሞ ቡድኖች የቀሰቀሱትን ችግር ለመፍታትና በምእራብና ደቡብ ኦሮሞ ክልል መረጋጋት ለማምጣት አስፈላጊ ስለሆነ፣ የመከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ወደ ደቡብ እንዲንቀሳቀስ በታዘዘው መሰረት ወደ ከትግራይ ወደ ደቡብ በሚሄድበት ወቅት፣ በምስራቅ ትግራይ ዞን ፋጺ ከተማ ህወሃት ያደራጃቸው ካድሪዎች የመከላከያ ሰራዊቱና ከባባድ መሳሪያዎቹ እንዳያላፉ እንዳገቱ መረጃዎች እየወጡ ነው።

በአገሪቷ ሕግ መንግስት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስተሩ ፣ ዶ/ር አብይ ነው። ዶ/ር አብይ በማንኛቸው ጊዜ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ከአንድ ቦታ ወደ አንድ ቦታ የማንቀሳቀስና የማሰማራት ስልጣን አለው። ሕግ መንግስታዊ ስልጣኑንም በመጠቀም የመከላካያ ሰራዊት ከትግራይ ወደ ደቡብ እንዲንቀሳቀስ በሚያዝበት ጊዜ ሕወሃት ያሰማራቸው ካድሬዎች የመከላከያ ሰራዊትን አላሳልፍ ማለታቸው፣ ፣ ድርጅቱ ህወሃት በይፋ በፌዴራል መንግስት ላይ እያመጸ መሆኑን አማላካች እንደሆነ ብዙዎች ይናገራሉ።

አፍቃሪ ሕወሃት ድህረ ገጽ ትግራይ ኦንላይን፣ ሕወሃት ካድሬዎቹን አሰማርቶ የፈጸመውን ድርጊት፣ ህዝብ እንዳደረገ በመዘገብ ፣”የፋጺ ምስራቅ ትግራይ ህዝብ፣ ታሪክ ሰራ፤ ወደ ወለጋ መራብ ኦሮሚያ የሚሄድትን ከባባድ መሳሪያ ህየተሸከሙ የጭነት መኪናዎችን አስቆሟል” ሲል በፌዴራል መንግስት ላይ የተደረገውን አመጽ አድንቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ህወሃት ህዝቡን እያስፈራ፣ ከሕዝብ ጀርባ ሆኖ አሁንም አፍራሽ ተግባራቱን ከመፈጸም ባይታቀብም፣ በተለያዩ አካባቢዎች የትግራይ ነዋሪዎች፣ ፍርሃታቸው እየገፈፉ ተቃዉⶁቸውን በድፍረት ማሰማት የጀመሩበት ሁኔታ እንዳለ አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተንቤን ከፍተኛ ተቃዉሞ የተነሳ ሲሆን በመቀሌም፣ በአባይ ወልዱ በጉልበት ቤታቸው የፈረሰባቸው በሺሆች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም ደፍረው ሕወሃትን መክሰስ ጀምረዋል።

1 COMMENT

  1. ህገመንግሥቱ ሊከበር ይገባል ። ሠራዊቱ የኢትይጵያ ነው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.