ቀይ መስቀል የማን ነው? የኢትዮጵያ ወይስ የኦሮሚያ?

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ችግር ካወሳሰበው አንዱ ባፉት 27 ዓመታት ስለ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት እየተሰበከ በተግባር የአንድ ቡድንን የበላይነት፣የአንድ ወገንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ብዙ ርቀት ተሂዱዋል። ተከታዩ ዜናን የተመለከቱ ኢትዮጵያ ንቂ ማለታቸው ተገቢ ይመስላል።ይህ አስቀድሞ ሊታረም ይገባል።ለመሆኑ ባለፉት 27 ዓመታት።ስንት አንቡላንስ ተገዝቶ ለየትኛው ክልል ምን ያህል እንደተከፋፈለ ሪፖርቱ ቢታይ መልካም ነው።የትላንቱን ስህተት በመድገም ብዙ ርቀት መጉዋዝ አይቻልም።ያንብቡት።ያጋሩት።

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ድጋፍ ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገዙትን 30 አምቡላንሶች በስሩ ለሚገኙ ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ርክክብ አካሄደ፡፡ የማህበሩ የሃብት ልማትና ማሰባሰብ ምክትል ዋና ፀሐፊ አቶ ወንዳዉክ አበዜ የ24ቱን አምቡላንሶች ቁልፍ ለየክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶቹ ተወካዮች ያስረከቡ ሲሆን ቀሪዎቹ ስድስት አምቡላንሶች ርክክብ ደግሞ በቀጣዩ ሳምንት ይከናወናል ተብሏል፡፡ በዕለቱ

 #ለኦሮሚያ14

ለአማራ 2፣

ለትግራይ 2፣

ለደቡብ 3፣

ለአፋር 2

እንዲሁም ለአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ደግሞ የአንድ አምቡላንስ ርክክብ ተካሂዷል፡፡

2 COMMENTS

  1. እየተካሄደ ያሉትን ነገሮች በትእግስት ማየት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ዋናው ነገር ሀገር ትረጋጋ፣ ሰላም ወጥተን በሰላም እንግባ፡፡ ለውጡን ለማደናቀፍ እየታተሩ ያሉትን ጠላቶቻችንን ላንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ እናስወግዳቸው፡፡ ከዛ በኋላ ስለ ቁሳቁስ መወያየት እንችላለን፡፡ ለተወሰነ ጊዜ እንታገስ እባካችሁ፡፡

  2. በተገኘው ዜና ሁሉ አትባንን! ሽንት ነበራቸው፣ ስንት ተጨመረላቸው? ብለህ ጠይቀሃል? ከህዝቡ ቁጥርና ካገሩ ቆዳ ስፋት ጋር ይመጣጠናል? ወይስ ኦሮሞ የሚል ቃል ያለበት አረፍተ ነገር ሁሉ ያባንነሃል? I know, for some worshipers of Minilik, the words Oromo and Oromia are totally unbearable!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.