ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶር አበራ ሞላ -እንዳላማው ክንዴ

ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ዶር አበራ ሞላ
……
መብራት በሱስ እንደወደቀ ጎረምሳ ፀባዮ እየተቆራረጠ ካስቸገረህ ዳቦ መጋገሩን ትተህ ሻማ ነግድ፡፡ ከቻልክም ሻማ ፋብሪካ ክፈት፡፡ ላምባ እና ጧፍም አዋጭ ንግድ ነው፡፡ የነሀሴ ዝናብ ፣እያለቀሰ ሲውል አንተ ጥላ ነግድ፡፡ ጃኬትና ቦት ጫማም አያከስሩም፡፡
ምንግዜም ትርፍ የሚገኘው ባንዱ መክሰር ነው፡፡
ጨለማ ባይፈሩ እነ ቤንጃሚን ፍራካሊን መብራትን መቼ ይሰሩ ነበር? ይላል በጎ መካሪ!!.መካሪ አያጥፋ!! ሞክር እንደ ቴሌ message ከሰለቸህ አለመዋጥ ይቻላል፡፡
ምክር የችግር መፈወሻ ብቸኛ ክኒን ሳይሆን አማራጭ ማሳያ ነው፡፡

ግን ኤች አይ ቪ ባይኖር ማሌዥያ የኮንዶም ምርቷን ማን ይገዛት ነበር? እነ ማሊያዥያ፣ አሜሪካ..በኮንዶም ኢኮኖሚያቸውን ጠግነዋል፡፡ የኤች አይ ቪ መድሃኒት መገኘት ለእነዚህ ሀገራት መርዶ ነው፡፡ በእንግሊዛዊው ዶክተር ኮንዶም የተሰራው ኮንዶም ከነዳጅ እና ከጦር መሳሪያ በላይ አዋጭ ንግድ ነው፡፡ እዚህ በስጦታ ስለሚመጣ ዝም ብሎ የሚታፈስ ከመሰለህ ተሳስተሃል፡፡

በነገራችን የኤች አይን መቋቋሚያ መድሃኒት ከፈጠሩ የዓለማችን ሳይንቲስቶች መካከል ዶክተር አበራ ምላ አንዱ ናቸው፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለኤችአይቪ ምንነት ገና በ 1981 በኢትዮጵያ ያስተማሩ፣የፃፉ ዶክተርም ናቸው፡፡ ኑሯቸውን ለ 42 ዓመታት ያህል በአሜሪካ ያደረጉት ዶክተር አበራ የአማርኛ ስራዓተ ፅህፈትን ለኮምፒዩተር ያስተዋወቁ ሙህርም ናቸው፡፡ ከ 1980 ዓም በፊት በአማርኛ ደብዳቤ እንኳን በታይፕ ራይተር ለመፃፍ ቀናትን ይፈጅ ነበር፡፡መፅሀፍት ለማሳተማ አሳር ነበር፡፡ በዚህም ብዙዎች ተስፋ ቆርጠው ፊደላት እንዲቀነሱ ወተወቱ፡፡

እነደራሲ ሀዲስ አለማየሁ፣አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በአማርኛ ፊደላት ጉዳይ ውዝግብ ውስጥ ነበሩ፡፡ዶክተር አበራ የአማርኛ ችግር ገዷቸው ከእንስሳት ዱክትርናቸው ጎን ለጎን ኮምፒውተርን አሀዱ ብለው ተማሩ፡፡ የልጅነት ትውስታቸውን ፊደል እስከ ባህሪያቱ ተመልሰው ጠንቅቀው አጠኑ፡፡ አጥንተውም፣ አልቀሩም በ 1982 ዓም ዛሬ የምንገለገልበትን የአማርኛ ስራዓተ ፅህፈት ለኮምፒዩተር አስተዋወቁ፡፡ የግዕዝ ፊደላትን በሙሉ ወደ ኮምፒውተር መርሃግብር አስገቡ፡፡
ዶክተር አበራ፣ከአፕል የቴክኖሎጂ ኩባንያ ጋር በመደራደር ወደ ተንቀሳቃሽ ስልክ የአማርኛ ፕሮግራም እንዲኖር አድርገዋል፡፡

አማርኛችን ከፊስቡክ እስከ ጎግል ከዓለም ግዙፍ ቋንቋዎች ጋር እንዲቀላቀል አድርገዋል፡፡ የበለጠ ለማሻሻልም እየሰሩ ነው፡፡ ተግባር ሰሪ ሙህራን ዓለምን ይቀይራሉ፡፡
የዛሬ ብላቴናዎች 3 “ዮ”ዎች እንደዚህ ገራሚ ፈጠራ ሳያበረክቱ ይቀራሉ? (ዮፍታሄ:633፣ዮሴፍ፣626 ዮናታን:623) ….
እንዴት ነው ነገሩ ግን ዮ ዎች አልተቻሉም!!
በስነፍጥረታዊ የፊደል አመጣጥ ንድፈ ሀሳብ መሰረት “የ “የተባለችው ሆሄ ትርጉሟ “የማነ እግዚአብሄር ገብረት” የእግዚአብሔር ሀይል ቀኝ አደረገ ማለት ነው፡፡
የማነ – ቀኝ ማለት ነው፡፡ ጌታ ሲሰቀል በቀኝ ና በግራ የማናይ እና ፀጋማይ ነበሩ፡፡ የማናይ በአዲስ ኪዳን ቀድሞ ከሰው ልጆች መካከል ገነት የገባ እንደሆነ ስነፍጥረቱ ያትታል፡፡የ – ወርቃማ ሆሄ ናት፡፡ ( የግዕዝ ፣ሆሄያት ሙሉ ትርጉም እንዳላቸው ይታወስልኝማ!!)
“የ” የተባለችዋ ሆሄ የዋዛ አይደለችም፡፡ ግን ሆሄ ነው ፊደል ነው የሚባለው?
✍ፊደል( alphabet) የሆሄያ አሰዳድር ሲሆን፣ሆሄ 
( letter ) የነጠላ ድምፆች መጠሪያ ነው፡፡ 
..
ግዕዝ በመጀመሪያ 22 ፊደላትን ከአርብ እስከ እሁድ ባሉ ፍጥረታት ልክ ፈጠረ፡፡ ከዚያ በኃላ ለንበት (pronunciation) አራት ፊደላትን አከለ (ሰ፣ኃ፣ዐ፣ፀ)፡፡

አማርኛ ደግሞ ሰባት ሆያትን ጨመረና (ቸ፣ኸ፣ዠ፣ሸ፣ኘ፣ቨ) ፊደላችን 33 ደረሱ:: እነዚህን ፊደላት ሳይቆራርጡ ዶክተር አበራ ከቴክኖሎጂ ጋር እስከ ስራዓተ ነጥባቸው አስቀመጡ፡፡

የግዕዝ ፊደላት ለአማርኛ እንዲመቹ ሆነው የተሰደሩት ከዛሬ 700 ዓመት በፊት በአፄ ይኮኖአምላክ ዘመን ነው፡፡በዚህን ወቅት አማርኛ የበለጠ ወደ ፁሁፍ ቋንቋነት የተሳበት ዘመን ነበርና፡፡ከቅርቡም አለቃ ተስፋ ስላሴ ዘ ብሄረ ቡልጋ ፊደላት ተደርድረው እንዲወጡ በማድረግ የሀገር ውለታ ውለዋል፡፡”ድንቁርና ይጥፋ፣ይሄ ነው የኢትዮጵያ ተስፋ!” የሚለው የዘወትር መፎክራቸው ነበር፡፡

አሁንም አማርኛን የበለጠ ለቴክኖሎጂ ለማቅረብ ፈረንሳይ ያሉ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከሀገር ወዳድ ወገኖቻችን ጋር በመሆን ፊደላት ያዘለ የኮምፒውተር መጫኛ (key board) ሰርተዋል፡፡
አማርኛ የዘመን ክስተቶቻችን ሙሉ ሸብሎ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ የቴክኖሎጂ እና የሳይንስ ቋንቋ ማድረግ ሊገፋበት የሚገባ ተግባር ነው፡፡ ፊደላችንም ቴክኖሎጂን ተላምዶ፣ ለስራዓተፅህፈት ምቹ ስለሆነ ይቀነስ የሚለው ሀሳብ አሁን ላይ ሚዛን አይደፋም–
ዕድሜ ለዶክተር አበራ ሞላ፡፡


እኔም ዶክተር አበራ ሞላን በማግኘቴ ደስ ብሌኛል
.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.