ሰመጉ በታህሳስ 24/2011 ዓ/ም ያወጣው 146ኛ ልዩ መግለጫ ገለልተኛና ሚዛናዊ አይደለም

የሰብዓዊ መብት አያያዝና አጠባበቅ ጉዳይ ለተወሰኑ ቡድኖች ወይም ወገን ብቻ የሚከበር መብት ሳይሆን ለሰው ልጅ ዘር በሙሉ ከጥቃት ፣ ከአደጋና ከሞት ከለላ ወይም ሽፋን የሚሰጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተባበሩት መንግስታት የተደነገገ ድንጋጌና መርሆ ነው ። ይህ ድንጋጌ በ193ቱም የተመድ አባል ሀገሮች በሙሉ የሚተገበር ሲሆን ኢትዮጵያም ይህንን ድንጋጌ ለመተግበር ፈርማ ተቀብላለች ። ይሁን እንጂ ባለፉት 27 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያን ሲመራ የነበረው የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት መሪዎች በዓለም አቀፍና በአፍሪካ ደረጃ የተፈራረሙበትን የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ ድንጋጌዎችንና ስምምነቶችን ወደ ጎን በመተው በመላው አገሪቱ ሽብር እየፈጠሩና የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች እየጣሱ እንደነበር በገሃድ የሚታወቅ ጉዳይ ነው ። በዚህ ውስጥ ዋና ተዋናይ የነበሩት ሀገሪቱን በቁንጮነት ስመሩ የነበሩት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዘናዊና እርሱን ተክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ እና የነርሱን ትዕዛዝና ተልዕኮ የምፈጽሙ የፖለቲካ ካድሬዎቻቸው ነበሩ ። ስለዚህ እነዚህ መሪዎችና ካድሬዎች በሰው ልጆች ሰብዓዊ መብቶችና ባገሪቱ ላይ ባደረሱት ጉዳት መጠንና በፈጸሙት ወንጀል ልክ ተመጣጣኝ የሆነ የህግ ቅጣት መቀበል ስገባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በሚመራው መንግስት ውስጥም ትርጉም ያለው የስልጣንና የአማካሪነት ቦታ ተሰጥቶአቸው በዜጎች ቁስልና ሀዘን ላይ እየተሳለቁ ይገኛሉ ።

ለአብነት ለመጥቀስ ያህል ፍሰሀ ጋራደው (የቀድሞ የደቡብ ክልል ፖሊሲ ኮሚሽን ኮሚሽኔር) እና ተስፋዬ ቤልጅጌ (የቀድሞ ደኢህዴን ጽ/ቤት ሀላፊ) በሰኔ ወር 2010 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማና በሲዳማ ዞን በተለያዩ አካባቢዎች ገዳይ ግብረ ሀይሎችን አሰማርተው በርካታ የሲዳማ ልጆችን ያስገደሉና ያስጨፈጨፉ ለህግ መቅረብ የሚገባቸው ወንጀለኞች ወደ አዲስ አባባ ከተማ አስተዳደር ተወስደው ተሹመው ይገኛሉ ። ከዚህም በተጨማሪ አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝና ካቢኔው የደቡብ ክልልን በምመሩበት ወቅት በ1994 ዓ/ም የሲዳማ ህዝብ መብቱን ለመጠየቅ በባዶ እጁ ባንድራና ቅጠል ይዞ በወጣው ላይ የግድያ ትዕዛዝ በመስጠት ጭካኔ በተሞላ ሁኔታ ንጹሀን ሲዳማዎችን አስጨፍጭፈው ለፍርድ መቅረብ ስገባቸው ሀገር እመራለሁ ብሎ ለሺዎች ሞትና ለሚሊዮኖች መፈናቀል ዋና መንስኤ የሆነ ግለሰብ ባለስልጣን ዛሬም በዶ/ር አብይ መንግስት ውስጥ ልዩ አማካሪ መስሎ በመላላክ በሲዳማ ህዝብ ላይ ያደራጃቸውን የጠላትነት መረቦቹን ያንቀሳቅሳል ። ለምሳሌ ያህል ባሁኑ ጊዜ በጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት ውስጥ የኮሙኒኬሽን ሀላፊ ተደርጎ ተሹሞ እየሰራ ያለው ግለሰብ ከድሮ ጀምሮ የሀ/ማሪያም ደሳለኝ ቀኝ እጁና የተልዕኮው ዋና ፈጻሚ ነው ። ይህ ግለሰብ ስለሲዳማ ህዝብ ጉዳይ ከአቶ ሀ/ማሪያም ቀጥተኛ ተልዕኮ እየተቀበለ የሲዳማን ህዝብ ለማሸበር በተለይም የሲዳማ ብሔር ክልል እንሁን ዳግመኛ ጥያቄ ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት የሚያወጣቸው መግለጫዎች ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አይደሉም ። እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ የሲዳማ ህዝብ ጠላቶች በህዝባችን ላይ ለፈጸሙት በደልና ወንጀል ወደ ፍርድ መቅረብ ይገባቸዋል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰመጉ ታህሳስ 24 ቀን 2011 ዓ/ም የኦሮሚያና ደቡብ ክልሎችን ዋቢ አድርጎ ያወጣው 146ኛ ልዩ መግለጫ ሚዛናዊ ያልሆነ ፣ ወደ አንድ ብሔር ያደላ እና የሲዳማ ልጆችን ሞትና የአካል ጉዳት ያላካተተና የሲዳማን ብሔር ወጣት በሙሉ በጥፋተኝነት የፈረጀ ከመሆኑ የተነሳ ወገንተኝነትን አጉልቶ ያንጸባረቀና ገለልተኛነት የጎደለበት ከመሆኑም ባሻገር ሪፖርቱ እራሱ አቶ ሀ/ማሪያም ባደራጃቸው ካድሬዎች እጅ ተጽፎ በሰመጉ አርማና ጽ/ቤት በኩል የወጣ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል ። ምክንያቱም ሰመጉ የሰው ሀይል ውስንነት አለብኝ ብሎ ሲናዘዝ መግለጫው በራሱ የተዘጋጀ አለመሆኑን ከማስገንዘቡም ባለፈ መግለጫው በጥሞና ሲነበብ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ በ17 ዓመታት ውስጥ በደቡብ ክልል በተለይም በሲዳማ ብሔር ላይ ሲያራምድ የነበረውን ነውረኛ ፖሊሲ የሚሸትት መሆኑ በርሱ ካድሬዎች እጆች የተጻፈ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ። በሌላ በኩል ደግሞ ሰመጉ ቆመለታለሁ ብሎ የሚናገራቸውን የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን እና

የአህጉሩን ኮንቬንሽኖችን ወደ ጎን በመተው የፖለቲካ ወገንተኝነትና ካድሬነት ስራዎች ውስጥ የተዘፈቀ መሆኑን ፍንቱይ አድርጎ የሚያሳይ መግለጫ ወይም ሪፖርት ነው ። ከ2 ሚሊዮን ተኩል በላይ የሆነውን የሲዳማ ወጣት በጅምላ እንደጥፋተኛ መፈረጅ በራሱ ተቋሙ ለአንድ ወገን ብቻ በማድላት እና ለችግሩ ዋና መንስኤ ለነበሩት ለሀ/ማሪያም ወይም ለደኢህዴን ካድሬዎች ከለላ ለመሆን ባለው ክፉ ሀሳብ መነሻ ከ7 ሚሊዮን በሚበልጥ የሲዳማ ህዝብና ብሔር ላይ በይፍ ጦርነት ያወጀ መሆኑን ያመላክታል ። የሲዳማ ህዝብ አሽባሪም ፣ ጦረኛም ፣ ወንጀለኛም አይደለም ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ደግሞ መብቱን ለማስከበር የመከላከል እርምጃ መውሰድ ተፈጥሮአዊ መብት መሆኑ መታመን ይኖርበታል ።

የፊቼ ጫምባላላ ማለትም የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓልን ማክበር ከጥንት ከቅድመ አባቶቹ ተያይዞ የመጣና ለወደ ፊትም የሚኖር የሲዳማ ባህል ነው ። ይህን በዓልና የሲዳማን ህዝብ የጥፋቱ መንስኤዎች አድርጎ መመልከት ፈጽሞ የተሳሳተና ሊታረም የሚገባው ሀሳብ ነው ። ችግሩ ያለው ዓመታዊ በዓሉን ለማክበር የወጣውን ህዝብ የማወክ ተግባር የፈጸመውና ያስፈጸመው አካል ጋር ሲሆን ያ አካል በሰመጉም በግልጽ ሊኮነን ፣ ሊወገዝና ሃላፊነትንም መውሰድ ይኖርበታል ። ይኸውም ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ያደራጀው እነ ፍሰሀ ጋራደውንና ተስፋዬ ቤልጅጌን ያካተተ ወንጀለኛ የካድሬዎች ቡድን ነው ። ሰመጉም መግለጫ ማውጣት ካለበት ይኸው በወንጀለኛ ቡድኑ ላይ እንጂ በደልና ጥቃት ደርሶበት የጉዳቱ ሰለባ በሆነው በሲዳማ ህዝብ ላይ ጣቱን መቀሰሩ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር መሆኑን ያሳያል ።

በመጨረሻም በሰመጉ 146ኛ ልዩ መግለጫ ላይ የታዩ ግድፈቶችንና ጉድለቶችን ከዚህ ቀጥሎ በዝርዝር ማቅረብ አስፈልጓል ።

1ኛ) ሰመጉ ችግሩን ለመሸፋፈን ያቀረበው የሰው ሀይል ውስንነት የመግለጫው ዝግጅት ከወሰደበት (ማለትም ከሚያዝያ 2010 እስከ ታህሳስ 2011 ዓ/ም ያለው 8 ወር) ጊዜ አንጻር ሲታይ ክስተቶቹን በትክክል ላለመዘገብ በቂ ምክንያት አይሆንም ፤

2ኛ) በዚህ ደረጃ የወረደ ሪፖርት ለማዘጋጀት ለአንድ ባለሙያ ከ2 ሳምንት ጊዜ በላይ አይፈጅም ፤

3ኛ) በተለይም በደቡብ ክልል ውስጥ ችግሩ የተፈጠረው ሰኔ ወር በተመሳሳይ ጊዜ በወልቂጤ ፣ በሀዋሳና በወላይታ ሶዶ ከተሞችና አከባቢዎች ሲሆን ሰመጉ የሀዋሳን/ሲዳማን አካባቢ ላይ ብቻ ማነጣጠሩ በሲዳማ ህዝብ ላይ ካለው ጥላቻና የፖለቲካ ካድሬዎች ተልዕኮ መፈጸሚያ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል ፤

4ኛ) በሪፖርቱ ውስጥ ቦታዎች ሲገለጹ በሲዳማ ዞን አስተዳደር ውስጥ የሚገኘውን ሎካ አባያ ወረዳን የወላይታ ዞን አስተዳደር ወረዳ ነው ብሎ ማቅረቡ መግለጫው በባለሙያ የተዘጋጀ አለመሆኑንና በዝግጅቱ ሂደት ከፍተኛ የሆነ እንዝላልነት መኖሩን ያሳያል ፤

5ኛ) መግለጫው የወላይታ ብሔር ተጎጂዎችን እንጂ የሲዳማ ብሔር ተጎጂዎችን አለማካተቱ እና ጉዳት ያደረሱ አካላትን በመሸፋፈን በሲዳማ ወጣቶች ላይ ለማላከክ መሞከሩ ተአማንነት የጎደለውና ላንድ ወገን ብቻ ያደላ መሆኑን ያስረዳል ፤

6ኛ) በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ በሲዳማ ልጆች ላይ በሀዋሳ ማረሚያ ቤቶች ውስጥ ፣ በሀዋሳ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ውስጥ ፣ በሻማና ገበያ ውስጥ እና በወላይታ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ውስጥ ተልዕኮና ስምሪት ከነፍሰሀ ጋራደው በተቀበሉ ታጣቂ የወላይታ ፖሊሶች ጥይትና ድብደባ ፣ በተደራጁ ቡድኖች በተወረወሩ የእጅ ቦንቦች እና በወላይታዎች ከፎቅ ህንጻ ላይ ተወርውረው በደረሰባቸው የሞትና የአካል ጉድለት ጉዳቶች ዙሪያ የሰመጉ መግለጫ መረጃ ለመስጠት አልቻለም ፤ ይህም መግለጫው ለተለየ ዓለማ የተዘጋጀ መሆኑንና የሲዳማን ብሔር ለማጥቃት የተቀነባበረ መሆኑን ያስገነዝባል ። ስለዚህ ሰመጉ የአቅም ውስንነት ብቻ ሳይሆን የሞራል ችግርም ያለበት መሆኑን መረዳትና ተጠያቂነትንም መውሰድ ያለበት አካል ይሆናል ።

ከሰኔ እስከ ሐምሌ 2010 ዓ/ም ድረስ በተደራጁ የወንጀል ፈጻሚ ቡድኖች የሞቱ እና አካል የጎደሉ የሲዳማ ልጆች መረጃ

ተ/ቁ የሟች ስም ብሔር የተገደለበት ቦታ የድርጊቱ ዓይነትና ፈጻሚ አካል
1 ብዙአየሁ ከበደ ሲዳማ ሀዋሳ ማረሚያ ቤት በዎላይታ ፖሊሶች በዱላ ተደብድቦ ተገድሎአል
2 ብዙአየሁ ማርቆስ ሲዳማ ሀዋሳ ማረሚያ ቤት በዎላይታ ፖሊሶች በዱላ ተደብድቦ ተገድሎአል
3 ዳዊት ዳቃሞ ሲዳማ ሀዋሳ መ/ኮሌጅ ግቢ/TTC/ በዎላይታ ፖሊሶች በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
4 ትግሉ ተስፋዬ ጫለ ሲዳማ ሀዋሳ መ/ኮሌጅ ግቢ/TTC/ በዎላይታ ፖሊሶች በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
5 ማቴዎስ ደረጀ ሲዳማ ትንባሆ ሞኖፖል በዎላይታ አጋዚ አባል በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
6 ተሻለ ዬተራ ሲዳማ አዲሱ ገበያ በዎላይታ ፖሊሶች በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
7 ሙሉነህ ሲዳማ ሀዋሳ ከተማ በቤቱ ውስጥ በዎላይታ ፖሊሶች በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
8 ሙሉጌታ ሲዳማ ሀዋሳ ከተማ በቤቱ ውስጥ በዎላይታ ልዩ ሀይል በመሳሪያ ጥይት ተደብድቦ ተገድሎአል
9 እያዩ ባጥሶ ሲዳማ ሶዶ ግብርና ኮሌጅ ግቢ ከኮሌጁ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ላይ በዎላይታዎች ተወርውራ ሞታለች
10 ንጉሴ ጃንጀ ሲዳማ በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ተገድሎአል
11 ሳንጃ ጋማዳ ኦሮሞ በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ተገድሎአል
12 ቡሴ ኢዩኤል ሲዳማ በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ተገድሎአል
13 ሪቂዋ ዩቱራ ሲዳማ በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ተገድሎአል
14 ዲጋ ሲርባሞ ሲዳማ በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች የእጅ ቦንብ ተወርውሮ ተገድሎአል

ከ14ቱ ሟቾች ውስጥ ብዙአየሁ ማርቆስ ፣ ዳዊት ዳቃሞ ፣ እያዩ ባጥሶ ፣ ሙሉነህ ፣ ሙሉጌታ ፣ ማቴዎስ ደረጀ እና ተሻለ ዬተራ ባጠቃላይ የ7 ሰዎች ወይም 54% የሚሆኑ የሲዳማ ልጆች ሞትና የአሟሟታቸው ሁኔታ በሰመጉ ልዩ መግለጫ ወይም ሪፖርት ውስጥ አልተካተቱም ።

በተጨማሪም በሻመና ገበያ ውስጥ በዎላይታ ሚሊሻዎች በተወረወረ የእጅ ቦንብ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሳቸው 61 ሲዳማዎች በሰመጉ ልዩ መግለጫና ምርመራ አልተሸፈኑም ።

ተ/ቁ የአካል ጉዳተኛው ስምና አካባቢ ተ/ቁ የአካል ጉዳተኛው ስምና አካባቢ ተ/ቁ የአካል ጉዳተኛው ስምና አካባቢ
1 እናራ ማርቆስ – ሻማና ሁሩፋ 21 ሌዳሞ ቦንጃ – ቃጂማ ኡምቡሎ 41 ማጦ ተሾመ – ሻማና ሁሩፋ
2 እሳያስ ጴጥሮስ – ቃጂማ ኡምቡሎ 22 ዲንጋሞ ድኪሶ – ቃጂማ ኡምቡሎ 42 ኑሬ ጉታ – ሻማና ሁሩፋ
3 ቀንጣ ቀይቻ – ሻማና ሁሩፋ 23 ካፋሎ ሳሙኤል – ቃጂማ ኡምቡሎ 43 ደሳለኝ ቢኖ – ሻማና ሁሩፋ
4 ባይሶ ባናታ – ቃጂማ ኡምቡሎ 24 አባይነሀ ሄኖክ – ቃጂማ ኡምቡሎ 44 ላንቺቱ ፍላቴ – ሻማና ሁሩፋ
5 ተስፋዬ አብሮ – ቃጂማ ኡምቡሎ 25 እልፍዮስ ጳውሎስ – ቃጂማ ኡምቡሎ 45 ከድጃ ናጣሻ – ሻማና ሁሩፋ
6 ባናታ ባራሳ – ቃጂማ ኡምቡሎ 26 ደምሴ ሪቂዋ – ቃጂማ ኡምቡሎ 46 ምልሻ ሲላሴ – ሻማና ሁሩፋ
7 ቢራጋ ጦሳ – ቃጂማ ኡምቡሎ 27 ላንቼ ሻኖ – ቃጂማ ኡምቡሎ 47 እሳያስ ጥጋ – ሻማና ሁሩፋ
8 ዘለቀ እሳያስ – ቃጂማ ኡምቡሎ 28 ዩሙራ ባቼ – ቃጂማ ኡምቡሎ 48 አድማሱ ቦሾላ – ሻማና ሁሩፋ
9 ዲጋሶ ድርፋቶ – ቃጂማ ኡምቡሎ 29 ዘርሁን ባራሞ – ቃጂማ ኡምቡሎ 49 ብሳሬ ሱንኩሬ – ዶዮ ጫሌ
10 ሆቻ ቡላዶ – ቃጂማ ኡምቡሎ 30 ታከለ ወርባ – ቃጂማ ኡምቡሎ 50 ቱምቡሎ ቱሚቻ – ዶዮ ኦቲልቾ
11 ካፋላ ቡራቆ – ቃጂማ ኡምቡሎ 31 ባራሳ ቃሹራ – ቃጂማ ኡምቡሎ 51 ዳንሳ ያንዶለ – ዶዮ ኦቲልቾ
12 ዘላለም ሙሴ – ቃጂማ ኡምቡሎ 32 ሆሲሶ ጎዋና – ቃጂማ ኡምቡሎ 52 ጋራሙ ማጉያ – ዻንካካ ኡምቡሎ
13 ኖሜ ቦንጃ – ቃጂማ ኡምቡሎ 33 እያሱ ሻናና – ሻማና ሁሩፋ 53 መሰለ ቃዋቶ – ዻንካካ ኡምቡሎ
14 ጴጥሮስ ቦንጃ – ቃጂማ ኡምቡሎ 34 እሳያ ቃቻ – ሻማና ሁሩፋ 54 ብልጣ ፋና – ሩኬሳ ሱኬ
15 ባቄ ባልጉዳ – ቃጂማ ኡምቡሎ 35 ስመኦን ጎሳ – ሻማና ሁሩፋ 55 ማትዎስ ተሾመ – ሻማና ጋርማማ
16 ኢያሱ ኮሸ – ቃጂማ ኡምቡሎ 36 ኖ’ኖራ ጉታ – ሻማና ሁሩፋ 56 ተሻለ ሁሪሶ – ሻማና ጋርማማ
17 ይሳቅ ወንዶ – ቃጂማ ኡምቡሎ 37 ዳራራ ሪቂዋ – ሻማና ሁሩፋ 57 ዳናዎ ታደሰ – ጎኖዋ ቡላኖ
18 ደምሴ ወንዶ – ቃጂማ ኡምቡሎ 38 ናዳሞ ቲቦ – ሻማና ሁሩፋ 58 አበባየሁ ጥሎ – ላቡ ኮሮሞ
19 እሸቱ ጩላ – ቃጂማ ኡምቡሎ 39 አዱለ ክአ – ሻማና ሁሩፋ 59 ደሳሎ ዎ’ማ – ባኬ ላሊማ
20 ተስፋዬ አሸናፊ – ቃጂማ ኡምቡሎ 40 ጃግና ሀጥያ – ሻማና ሁሩፋ 60 እንዳሻ ዱቤ – ዻንካካ ኡምቡሎ
        61 ጩናማ ቦሾላ – ቃጂማ ኡምቡሎ

የሲዳማ ብሔራዊ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ሲብዲን)

ታህሳስ 26 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.