ይድረስ ለሠይጣነ ሠይጣናዊ መለስ ዜናዊ እና አዶልፍ ሂትለር!

ሠይጣነ ሠይጣናዊ አዶልፍ ሂትለር ዛሬ ላይ የምረግምህ ከ50 እስከ 85 ሚሊዮን ለሚሆኑ ለጉዳትና ሞት የዳራካቸው የዓለም ሕዝብ ብቻ አይደለም። የበለጠ የምረግምህ በዚህ ምድር ላይ እንደ ቅሪተ-አካልህ ትተኸው በሄድከው የናዚ ርዕዮትና ይህን የሚከተሉና በዘረኝነት በሽታ የተበከሉ አዲሶቹን ናዚዎች (Neo-Nazi) ስመለክትት ነው::

ሠይጣነ ሠይጣናዊ መለስ ዜናዊ አሁን የምረግምህ ከእራፊ ጨርቆችህ (coat of many colors) ሰብስበህ በደደቢት በረሃ የቀመምከውና ብዙዎችን እንደ በግ በነዳህበት “የጎሣ ፌደራሊዝም” ሥርዐትና “በአቢዮታዊ ዴሞክራሲ” ማደንዘዣህ ብቻ አይደለም። አምርሬ የምረግምህ በጋራ ጭንቅላት የሚያስቡ ደናቁርትን የጎሣ ፓለቲካን አስታጥቀህ በሌለህበት የሚያናፉ ነገረፈጆችህን ሣይ ነው። እንዳንተው ኢትዮጵያን እያራከሱ፤ ኢትዮጵያውያንን የሚጣቆሱ ዋልጌዎችን ያለሰብሳቢ አባትና በረት ውስጥ የሚያስርልን እረኛ በትነህብን በመሄድህም ነው። አንተን “እያወገዙ” በአንተ “ቅዱስ መፅሃፍ” “ብሔረተኛ ነን” እያሉ በሥምህ የሚመፃደቁ የጎጥ ስብስቦችንና የደቦ ፎካሪዎች ምድሯን በአዛባ ሲለቀልቁ በማየቴም ነው። ሃሣብን በጎጥ ሸንሽነው በጎጥና በጎሣ ድጋፍና ተቃውሞ የሚሰጡ ግብዞችን፤ ሃሣብን በምክንያታዊነቱ ሣይሆን የሃሣብን አመንጪውንና የሃሣቡን ጎሣ ጠይቀው እንደ መንጋ የሚነዱ፤ ውይይትን ሣይሆን ንትርክን፣ ስም ማጠልሸትን የተካኑ አለሌዎችን ይዘህ ባለመሄድህም ነው። ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሥራ የጀመሩ ጠባቦችንና በኢትዮጵያ ሥም እየማሉ ኢትዮጵያን እየናዱ ያሉ ጎጠኞችን አርከፍክፈኸብን በመሄድህ ነው። ክፉኛ የምረግምህም በደደቢት መፈልፈያ ያባዛሃቸው ጠባብና ጎጠኞች ለመብት፣ ለነፃነት፣ ለዴሞክራሲና የሕግ የበላይነት እንዲሁም ለኢትዮጵያ ህልውና ሣይሆን ለጎጥ ሥልጣን ተንሰፍስፈውና ተሠልፈው በማይ ጊዜ ነው።

ሃዘኔንና እምባዬን የማብሠው ጀርመናውያን በፋሽስታዊ ብሔረተኝነት እብሪት የተወጠረውን የናዚ ሥርዐት ንደውና ገርስሠው ዴሞክራሲን እንዳነገሱት፤ ኢትዮጵያውያንም ከመለስ ዜናዊ የጎጥ አደረጃጀትና የጎሣ ፓለቲካ ተላቃ ዴሞክራሲያዊና የሕግ የበላይነት የሠፈነባት ሐገረ-ኢትዮጵያን እንደሚያንፁ በመተማመን ነው።

ሠይጣነ ሠይጣናዊ መለስ ዜናዊና አዶልፍ ሂትለር ነብሳችሁ አትማር!

ኢትዮጵያ ሐገሬ እንኳን በመለስ ዜናዊ የጎጥ ፓለቲካ አቀንቃኞች በጠላት ወረራም አልፈረሰችም!

ጎጠኝነትን የማይጠየፍ እራሱ ጎጠኛ ነው!

ኢትዮጵያዊነት አሸናፊነትና ክቡር የሠለጠነ ሕዝብ ማንነት ነው!

Hailu AT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.