ዶ/ር አብይ ለኢትዮጵያ አንድነት ካሰበ የሸዋ ሁኔታ ሊያጤነው ይገባል – ተስፋዬ መኮንን

በሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር መሪዎች ፊታውራሪነት የተዘጋጀውና የፀደቀው የሽግግር ቻርተርም ሆነ አሁን በሥራ ላይ ያለው ሕገ መንግሥት ተቀዳሚ ዓላማ፣ በ1960ዎቹ ሲቀነቀን የነበረውን ታሪካዊ መሠረት የሌለው የብሔር ብሔረሰብ ትርክት መሠረት በማድረግ፣ ጨቋኝ ተብሎ የተፈረጀውን አማራ ማሳነስ ነው፡፡ የሕወሓትና ኦነግ መሪዎችና ሌሎች የኢትዮጵያን የአገረ መንግሥት ግንባታ ታሪክ በቅጡ ያልመረመሩ ኀይሎች እንደያወሩለት የዚህ ሕገ መንግሥት ዋና ዓላማ የሕዝቦችን እኩልነት ማረጋገጥና ዲሞክራሲያዊ አንድነትን አይደለም፤ አማራውን በሕዝብ ቁጥር (ዲሞግራፊ) እና በግዛት (ጆግራፊ) ማሳነስ ነው፡፡

ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የታየው እውነታ እንዳረጋገጠው ይህ በመሠረተ-ቢስ ትርክት ላይ የተመሠረተ ሕገ መንግሥት በኢትዮጵያ ነገዶች መካከል እጅግ አደገኛ መጠራጠርና ግጭት ፈጥሯል፤ ሕዝብ በነጻነት መክሮና ዘክሮ ያፀደቀው ሕገ መንግሥት እስከሌለ ድረስ አሁን በተያዘው መንገድ ከቀጠልን አገራችን ወደከፋ መከራና የእርስ በርስ ጦርነት ልትገባ የምትችልበት ዕድልም በጣም ሰፊ ነው፡፡ ሦስት ዐሥርት ለሚጠጉ ዓመታት እንዳነው ከዚህ ሕገ መንግሥት ያተረፍነው የኢትዮጵያዊያንን መፈናቀልና መሳደድ ነው፤ የምንታዘበው የማያባራ ግጭት ነው፡፡

ይህ ሕገ መንግሥት በሥራ ላይ እስካለ ድረስ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ይቀጥላል፡፡ በመሬት ይገባኛል ምክንያት እየተከሰተ ያለው የዜጎች ስደትና ሞት አይቆምም፤ እንዲያውም በግልጽ እንደሚታየው እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ዘላቂው መፍትሔ በውሸት ትርክትና በቋንቋ ላይ የተመሠረተውን ግጭት ፈልፋይ አወቃቀር ከሥረ መሠረቱ መቀየር ነው፡፡ ከዚያ መለስ ያለው እርምጃ ሁሉ ጊዜያዊ ማስታገሻ ካልሆነ በስተቀር ሀገርና ሕዝብ በዘላቂነት የሚጠቀሙበት መፍትሔ አይደለም፡፡

እንደሚታወቀው መቶ በመቶ በኢሕአዴግና አጋሮቹ የተያዘው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ የማንነትና አስተዳደራዊ ኮሚሽንን በአዋጅ አቋቁሟል፡፡ ኮሚሽኑ በየአካባቢው በማንነትና ወሰን ጉዳዮች የሚነሱ ጥያቄዎችን እያጠና የመፍትሔ ምክረ-ሐሳብ የሚያቀርባና ከሚመለከታቸው መንግሥታዊ አካላት ጋር በመሆን የሚያስፈፅም ነው ተብሏል፡፡ በእኔ አስተያየት በተሳሳተ ትርክት በቋንቋ ላይ የተመሠረተው ፌደራላዊ ሥርዓት ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮች በዚህ ኮሚሽን አማካይነት ሊፈቱ ባይችሉም፣ ዘላቂ መፍትሔዎችን በመጠቆም ረገድ የራሱ አስተዋጽዖ ይኖረዋል፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ፣ ይህ ኮሚሽን ሕዝበ-ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውንና ሕዝበ-ውሳኔ ሳያስፈልግ መታጠፍ ያለባቸውን አካባቢዎች በግልጽ ለይቶ ማስቀመጥ ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ ያህል የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ መሪዎች የወልቃይት ጠገዴን መሬት ነባሩን ሕዝብ በመመንጠርና የራሳቸውን ታጋይና የቀን ሠራተኞች እንዳሰፈሩበት በግልጽ ይታወቃል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው የሚገባ ሐቅ አለ፤ ወልቃይት ጠገዴ ላይ ከየትኛውም የአገራችን አካባቢ በከፋ መልኩ በመንግሥት የተቀነባበረ ዘር መንጠራ ተካሂዷል፡፡ ነባሩ ሕዝብ ተመንጥሯል፡፡ ለዚህ አስከፊ ወንጀል ኀላፊነት የሚወስዱት ደግሞ ከሕወሓት የለቀቁትም ይሁኑ አሁንም ድርጅቱን የሚመሩት ግፈኛ የድርጅቱ መሪዎች፣ እንዲሁም የእነሱን ጉዳይ ሲያስፈፅሙ የነበሩት እንደ አዲሱ ለገሰና በረከት ስምኦን ያሉ የብአዴን መሪዎች ናቸው፡፡ ስለሆነም ይህ ኮሚሽን ወልቃይት ጠገዴ ላይ የተከሰተውን ዘግናኝ ወንጀል በሚገባ መርምሮ ይህን ወንጀል የፈፀሙና ያስፈፀሙ አካላት ተጠያቂ የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት ይገባዋል፡፡ በአገራችን በየትኛውም አካባቢ፣ በየትኛውም ሕዝብ ላይ ግፍ ሊፈፀም አይገባም የሚል እምነት ያለው የመንግሥት ባለሥልጣን፣ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፣ ምሁር፣ የሃይማኖት አባትና የአገር ሽማግሌ ሁሉ ወልቃይት ጠገዴ ላይ በሕወሓት መሪዎች ፊታውራሪነት የተፈፀመውን ኢሰብአዊ ድርጊትና የሕዝብ ምንጠራ በማያሻማ ቃል ማውገዝ ይጠበቅበታል፡፡

በሌላ በኩል ከወንጀለኞች በቀር ሁሉም ኢትዮጵያዊ ወልቃይት ጠገዴ የጎንደር/አማራ ታሪካዊ ግዛት መሆኑን ጠንቅቆ ስለሚያውቀውና ሐቁም እሱ ስለሆነ፣ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ወደ ነባር ማንነቱ እንዲመለስ ያስፈልጋል፡፡ ወልቃይት ጠገዴ ሳይመለስ በትግራይና በአማራ ሕዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም ይፈጠራል ማለት ዘበት ነው፡፡ ወደ ቀልባቸው ከተመለሱ ይህን ሐቅ የሕወሓት መሪዎችም ሊስቱት አይችሉም፡፡

በተመሳሳይ መልኩ አማራውን በመሬትም በሕዝብ ቁጥርም ለማሳነስ በተቀየሰው በሕገ መንግሥት በተደገፈ እርምጃ ምክንያት የተወሰዱት ራያና መተከልም ወደ ነባር ይዞታቸው መመለስ ይገባቸዋል፡፡ ራያና መተከል ላይ ሕዝበ-ውሳኔ ብሎ ነገር ቀልድ ነው፡፡ ስለ ሕዝበ ውሳኔ መወራት ያለበት አናሳውን መብት ለማስከበር ሲባል ብዙሃኑ በርስቱ በአስከፊ ጭቆና ውስጥ እንዲገባ ስለተደረገበት ኬሚሴ ነው፡፡ የነገዶችን በቋንቋቸው የመጠቀም መበት አስከብራለሁ የሚለው ሕወሓትና ኦነግ ሥርዓት ለአማሮች ሲሆን አይሠራም፡፡ ኬሚሴ ላይ ያለውን እጅግ አሳዛኝና በምንም ዓይነት መልኩ ተቀባይነት የሌለው ሁኔታ መመልከት በቂ ነው፡፡ ስለሆነም የተቋቋመው ኮሚሽን ኬሚሴ ላይ ሕዝበ-ውሳኔ የሚደረግበትን መንገድ ማመቻቸት ይጠበቅበታል፡፡

ሸዋ እና ኢትዮጵያ
****
ባዕዳን የኢትዮጵያ ጠላቶችም፣ የኢትዮጵያ የትንሽነት ኀይሎችም ሸዋን በሚመለከት የሚጋሩት ነገር አለ፡፡ ሁሉም ሸዋን በከፍተኛ ጥርጣሬና ጥላቻ ነው የሚያዩት፡፡ ሁሉም ሰንድ አዘጋጅተው ዘምተውበታል፡፡ ስለ “አንኮበርና አንጎለላ ሥነ-ልቦና” ብዙ ጽፈዋል፤ ሸዋ ስለሚዳከምበት ሁኔታ የተቀናጀ ዘመቻ አድርገዋል፡፡ አሁንም አልቆመም፡፡
የዚህ ሁሉ ውርጅብኝ ምክንያቱ በሚገባ ይታወቃል፤ ሸዋ የመካከለኛውና የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ እምበርት ስለሆነች ነው፡፡ የዘመናዊት ኢትዮጵያ አርክቴክቶች የዚህ አካባቢ መሪዎች ስለሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ምክንያቱ ይህ ብቻ አይደለም፤ ከዚህም በእጅጉ ይሰፋል፡፡ ሸዋ አማራው፣ የጉራጌው፣ የኦሮሞው፣ የሃድያው፣ የከምባታው፣ የየሙና የሌላውም ነገድ ውሕድና ኅብር ስለሆነች ትንሿ ኢትዮጵያ ናት፡፡ በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያን ማሳነስና ማዳከም የሚፈልግ ማንኛውም ኀይል ሸዋን ማሳነስና ማዳከም ይፈልጋል፡፡

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ባለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ሰነድ አዘጋጅተው ከተማሪ እስከ ፕሮፌሰር፣ ከመንግሥት ሠራተኛ እስከ ጥቃቅንና አነስተኛ ማኅበር አባላት ስለ ሸዋ እኩይነት አሰልጥነዋል፡፡ ከፍ ብሎ እንደተጠቀሰው የዚህ ሁሉ የጥፋት ተግባር ዋና ዓላመው ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የኢትዮጵያ ምልክት የሆነችውን ሸዋን ማሳነስና ማዳከም አስፈላጊ ነው የሚል ስትራቴጅ ስላላቸው ነው፡፡

ከኢትዮጵያ ፍርስራሽ ኦሮሚያን እንመሠርታለን የሚለው ኦነግና የእሱን ዓላማ የሚያስፈጽሙ ኀይሎችም ሸዋን ለማሳነስና ለማዳከም የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ የእነሱን አካሄድ ለየት የሚያደርገው የማሳነስና የማዳከሙ ሥራ መልኩን ቀይሮና የሸዋን ኅብር አጥፍቶ ኦሮሞ በማድረግ የሚገለጽ መሆኑ ነው፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት፣ ሁለንተናዊ ልማትና ሰላም የሚጨነቅ ከሆነ፣ የሸዋን ጉዳይ በልዩ ሁኔታ ሊያጤነውና መፍትሔ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ሸዋ ውስጥ የማይኖር ነገድ ስለሌለ፣ በዚህና ለአገረ መንግሥት ግንባታ ባደረገችው ግንባር ቀደም አስተዋጽዖ ምክንያት፣ ሸዋ የኢትዮጵያ ቀንዲል ስለሆነች፣ በልዩ ሁኔታ ታይታ የራሷ አስተዳደራዊ ግዛት እንዲኖራት ማድረግ ይገባል፡፡

3 COMMENTS

 1. This mentally slave guy is one of those who grew up and shaped with the self denial behaviors. Anti-unity and toxic are those like him and his mentors like Getachew Haile and others who are mentally retarded. They don’t believe in unity with diversity.

  This guy is politically infant and a very  simple minded Debterist like his friend in crimes Girma Kassa! Even his ghost father, Menilik (the Hitler of Africa) was more diplomatic than this guy by far. My advice for this guy is to take a basic political science courses before he open again his filthy mouth. His poor discourse has nothing to do with the reality at hands in Ethiopia today.

  His dreams will never be realized. The politics of one language, one culture  and a single nation is dangerous and cannot be accepted. If anyone may try against the Oromo people, will have no chance. But now temporally anyone can make noises. That is all what he can do right now.

  The main problems within the Ethiopian politics are those like this guy who don’t believe in unity with diversity.  They are anti-unity and toxic. They are dreaming their own nightmare. This shows that they are at the state of desperation and hopelessness.  Now this guy his colleagues try to sell themself as a Tiger and hero. But it is futile. The changes in Ethiopia came with the bitter struggles of the beloved Oromo children. Don’t worry they will also protect it bravely.

  The so called Befakadu Degefe is for example the mentor of such ifant politicians. Befekadu is an economist by training, but still he behaves as an ignorant Debtera and thinks with his Debtera mentality. He said shamefull Amaharaism is spirit. The main burden of Ethiopia is such poor individuals with backward and uncivilized mentalities

  No one knows better than Befekadu Degefe and  his disciples how the life hard is in their birth places for the ordinary families in general. The people from Wallo, Gojam and Gonder were misused by the greedy Neftengas of Shewa during the eras of Menilik, Haile Selasien and Mengistu who promoted their objectives  in the name of those innocent human beings. Thus, don’t forget that your families having been still suffering a lot as Walloye, Gojames and Gonderes under those inhuma systems of that empire state. From all these systems you have inherited only pseudo prides, bad mentality and cultures under which you are still in custody. I wish that you will become free from that mentality as a good and cultured human being. 

  Finally, we say no to the Oromo phobia! Ethiopia cannot go back to the old era. Nobody can impose it’s hagemoy any more in Oromia. The integrity of Oromia including Finfinnee will be untouchable. The Oromo nation has been fighting injustice and subjugation in it’s  homeland, Oromia in order to regain it’s human dignity as one of the great nations of East Africa. 

 2. “ሸዋ … የራሷ አስተዳደራዊ ግዛት እንዲኖራት ማድረግ ይገባል” ይላል ተስፋዬ መኮንን። ተስፈኛ ነህ ልበል? ወይስ የራስ መስፍን ስለሺ ጠቅላይ ገዥነት ስልጣን እንድሰጥህ ፈለግህ?! ወይ ድንቁርና! በ1960ዎቹ ላይ ቆሞ የቀረ ጭንቅላት! እስቲ መጀመርያ ምኒሊክ ከአንኮበር ሳይወጣ በፊት ሸዋ የሚለው ስም የዬት አካባቢ አጠራር እንደነበር ጠይቅና ተረዳ።
  Your hypocrisy is also boundless! ወልቃይት ጥንት የአማራ ስለነበረ ይመለስ እያልክ የኦሮሞ መሬት ወደ ሸዋ (አማራ) ይጠቃለል ዘንድ ትመኛለህ! አማራ የረገጠው (በጠብመንጃ ሃይልም የሰፈረበት) ሁሉ የአማራ “ርስት” ነው ብለህ መቃዠትህ ለኢትዮጵያ አንድነት ፍቱን እንደሆነ ታምናለህ! ኢትዮጵያን የምታዉቃት በአማራ ርስትነት ነው? ሌላውስ መብት የለዉም ወይስ አሁንም በ1870ቹ የህልም አለም ዉስጥ ነህ?? ከእንዳንተ አይነቱ ጋር ከመጨማለቅ “ኦነግ ከኢትዮጵያ ፍርስራሽ ኦሮሚያን እንመሠርታለን” ቢል ደግሞ ይገርምሃል?

 3. የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ሃይሎችና አክቲቪስቶች ዴሞክራሲ የሚሰራው እነሱ እንታገልለታለን ለሚሉት ህዝብ ብቻ ነው፡፡ ሌላው ህዝብ በጭቆና በአፈና በመፈናቀል ውስጥ ሲኖር ለነሱ ስኬት ነው፡፡ በክልላቸው ያለ ሌላ ህዝብ ውክልና የለውም፤ የክልል መንግስት ተቐም ውስጥ መስራት እድል የለውም ቢኖርም በጣም ጥቂት ነው፡፡ የእነዚህ የአድልዖ ማሽኖች ምን መቼ እንደሚፈጽሙ አቅደው ይሰራሉ፡፡ ከነዚህ ዴሞክራሲ መጠበቅ ከዝንብ ማር እድደመጠበቅ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.