የአማራ ወጣት የሰነፍ ወታደር ኢላማ መለማመጃ አይደለም !! (ከተሾመ ሞገሴ)

1. በመከላከያው ውስጥ ተሃድሶ አድርገናል እየተባለ ዛሬም የአማራ ህዝብ የማርያም ጠላት ተደርጎ በመከላከያ ተብዬው ከተረሸነ የጉዞችን መንገድ ጠቧል መድረሻውም ቅርብ ሆኗል ማለት ነው::

2. ዶ/ር አብይ አንተ አንድ ኢትይጵያዊ ነህ አንዳንድ የመከላከያ አባላት አንተን በተንኮል ሊገሉህ ቢመጡ ተንኮለኞቹም ንዝ ህላሎቹም ወንጀላቸው በጦር ፍርድ ቤት ተጣርቶ የሚገባቸውን ቅጣት አግኝተዋል:: ይሄ ጥሩ እና ተገቢ ነው:: ሁሉም ኢትዮጵያዊ እኩል ነው ብለህ የምታምን ከሆነ አንተን ሊተናኮሉ የነበሩ ሰዎች ጎዳያቸው ተጣርቶ ከላይ እስከታች ቅጣት እንደተቀበሉ ሁሉ አሁንም የአማራን ወጣት ለይተው የሚጨፈጭፉ ነብሰባላ ውሾችም ወታደራዊ ፍርድ ቤት መቆም የሚገባችውንም ፍርድ መቀበል አለባቸው::

3. የአማራ ክልል ባለስልጣናት በእውነትም ለአማራ ህዝብ የቆማችሁ ከሆነ እነዚህ ነብሰ በላ ታጣቂዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የምትችሉትን ሁሉ ማድረግ አለባችሁ:: የአማራ ህዝብ ባለፉት 27 አመታት አምስት በማይሞሉ ህዝቦች ሰው ሊሸከመው ከሚችለው መከራ የበለጠ አስተናግዷል አሁን ግን ይበቃል:: በሌላ የኢትዮጵያ ክፍል የሚሞቱ ብዙ ሰዎች አሉ ሁሉም ግን የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተብዬው ታጣቂ የሚገላቸው ሳይሆን በአሸባሪዎች በእርስ በእርስ ጦርነት በወንጀሎኞች የሚሞቱ ናችው:: ይሄ የተለየ ነው::

4. ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሰው ግን ህግን ማክበር አለበት:: የሱር ኮንስትራክሽን ወንጀል ከሰራ ለህግ አስከባሪ አካል መጠቆም እንጂ አትወጣም ወይም ይፈተሽ ብሎ በጅምላ ስራን ማስትጓጎል በምንም አይነት መንገድ ተገቢ አደለም፥፥ ወጣቱ ዝም ብሎ በጅምላ መነዳቱን ማቆም አለበት::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.