የሁለት ዜጎች ወግ – በቀሲስ መላኩ ተረፈ

መንገድ ዘጋችሁ ተብለው ፣ በጥይት ስለተደበደቡት ወገኖቼ ሰማሁ። በዚህ በአሜሪካ ፣ በነጮችና በጥቁሮች መካከል ያለው ፣ የዘር መድልዎ በስፋት የተጻፈበት ነው። ነጩ አሜሪካዊ ፣ መሣሪያውን በፖሊስ ላይ ቢወድር እንኳ ፣ በትዕግሥት ይታለፋል። ጥቁሩ አሜሪካዊ ግን ፣ ከፖሊስ ሮጠ ተብሎ ፣ ከጀርባው በጥይት ይደበደባል።

በኢትዮጵያም እየሰማን ያለነው ፣ ሁለት ዜጎች እንዳሉ ነው። በአንድ በኩል ፣ መከላከያን አገዱ ሲባል ፣ « እነርሱን ቅር ከሚላቸው እኛ ቅር ይበለን» ብለው ፣ ጄኔራሉ የሚናገሩላቸው አሉ። ራሳቸው መንግሥት መስለው ፣ « ማን ትጥቅ አስፈቺ ማን ትጥቅ ፈቺ» እያሉ፣ ሕዝብ እየፈጁ ፣ በአዲስ አበባ ጽ/ቤት የተሰጣቸው አሉ። አንዳች ሳይነኩ !! በሌላ በኩል ግን ፣ ሌሎች ዜጎች አሉ። ኢላማ መለማመጃ የሆኑ ፣ ተራ መንገድ ዘጋችሁ ተብለው ፣ በጥይት የሚደበደቡ።

ይህ ማንም እየተነሣ ፣ ቂሙን መወጫ ያደረገው ሕዝብ ፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለቱ የተዘለፈ ፣ የተሰደበ ፣ አንገቱን ለመስበር ፣ ብዙ የተሞከረበት ሕዝብ ነው። ነገር ግን ፣ በማተቡ የጸና ነው። ያ ሕዝብ ፣ ሁሌም እየተገደለ ነው። አሁን ልቤን ያደማው ፣ ም/ኤታማዦሩ በተወካዮች ምክር ቤት ፣ ያቀረቡትን ማብራሪያ ከሰማሁ በኋላ ፣ የተደረገ መሆኑ ነው። ” ሕዝብን አንገድልም ፣ ወደ ሕዝብ አንተኩስም ” ነበር ያሉት? ወይስ በጎንደር የተገደሉት ፣ ሕዝብም ሰውም አይደሉም?

1 COMMENT

  1. ከዚህ የባሰም አለ። ከዘመናት ጀምሮ የኦሮሞን ደም በከንቱ ማፍሰስ ፍፁም ስለተለመደ አሁንማ መዘገቡም ተሰለቸ መሰለኝ። በጭናቅሰን፣ ሞያሌ፣ ጉጂ፣ወሎ፣ ሌላም ጋ ዛሬም “የመንግስት” ጦር ኣበጋዞች ያለ ሃይ ባይ ይገድላሉ፣ አካል ያጎድላሉ፣ ያስራሉ፣ ይሰዉራሉ። ወለጋ፣ በኦነግ ጦር ሰበብ ኦነግ በሌለበት ሁሉ ህዝቡ OPDOን ስላልደገፈ ብቻ ከአየር ሳይቀር ቦምብ እየዘነበበት ነው! ኦሮምኛ የሚናገር ጠ/ሚ ኦሮሞን እያስፈጀ ነው። ሶስተኛ ዜግነት ማለት እንዲህ ነው!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.