ድምጽ አልባው የአንድነት ሃይል በችግር ጊዜ አብረውት ያልቆሙትን ህዝብ እንዴት በምርጫ ጊዜ ድምጽህን ስጠኝ ማለት ይቻላል? (አሰፋ በድሉ)

ይህንን ጥያቄ እናደነሳ ያደረገኝ፤ጥር 1/2011 ዓ.ም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ድምጽ በረከተብኝ፡፡2፡00 ሰዓት ኢቲቪ ዜና እንዲሁም ቪኦኤ  “ጥር 09, 2019   ምዕራብ ጎንደር ገንደ ውሃና ኮኪት መከላለያ ሰወችን ተኩሶ መግደሉን ነዋሪወች ገለጹ” በማለት የዘገበውን አደመጥሁ፡፡ ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለቪኦኤ የሰጡትን አመንክዮ አደመጥሁ፡፡ መከላከያ ስለተተኮሰበት ነው፤እንዲሁም ወደ ሰማይ ነው የተኮሰው የሚልና ራሱን መከላከል እንደሚችል ገለጹ፡፡ትግራይ ቢታገትም ተኩስ አልተከፈተበትም የሚል አሳዛኝ ምላሻቸውን ሰማሁ፡፡የአብንም መግለጫ አነበብሁ፡፡የአማራ ክልልንም ኮሚኒኬሽን ዋና ዳይሬክተር ለኢቲቪ በስልክ ከሰጡት መግለጫ ተኩስ በሁለቱም ወገን እንደነበር ገለጹ፡፡ትንሽ ጥያቄ ብቻ አንስቶ ወደ ዕውነቱ መጠጋ ት ይቻላል፡፡

1ኛ፡ መቀሌ ላይ መከላከያ በቃል ቆመ፡፡ምስጢራዊ የሆነው የመከላከያ ንብረት ላይ ወጥተው ሲጨፍሩ ምስሉን አይተናል፡፡ንብረቱን እንኳን አትንኩብኝ አላለም፡፡ጎንደር ላይ ግን መንገድ የዘጋውን ህዝብ በተኩስ ሰብሮ ለማለፍ ሰው መግደል ነበረበት፡፡መከላከያ ቁም ሲባል ከቆመ እኮ በምን ምክንያት ከነዋሪው ጋር ግጭት ውስጥ ገባ? ነዋሪው የጠየቀው ቀላል ጥያቄ ነው፡፡ይፈተሸ! አስፈትሾ ለምን መሄድ አልፈለገም? ይፈተሸ የተባለው የራሱ የመከላከያ ቢሆን ከሚስጥራዊነቱ አንጻር ተገቢ በሆነ ግን ይፈተሸ የተባለው የንግድ ድርጅት፤የሱር ኮንስትራክሽን ነው፡፡ከጫነም አሸዋ ነው፤ሲሚንቶ ነው፤ችግሩ ምንድን ነው? ወይንስ ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ ነበር?

2ኛ፡ከነዋሪወች ጋር በመካሄድ ላይ ያለው ውይይት ሳይጠናቀቅ ለምን እንቅስቃሴ ተጀመረ? ነዋሪወች ዕውነት አላቸው፡፡

የእኔ ዕያታ

1.ይህ የህወሃት የቅማንት ፕሮጄክት ፍሬ እንዳፈራ እናያለን፡፡ስለሆነም ህወሃትን ከአራት ኪሎ ማስለቀቅ ብቻ የተሟላ ሰላም እንደማያስገኝ እስከ ኤርትራ የዘለቀው ችግር ማሳያ ነው፡፡ሶስቱ እህት ድርጅቶች ና ሁሉም አጋር ድርጅቶች ወደ ለውጥ ሲገቡ ህወሃት እንዳለ አለ፡፡እንዲያውም ጌታቸው አሰፋን አማካሪ አድርጎ ተቀምጠዋል፡፡ አማራ ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ያለቅሳል እንዲሉ እንግዲህ ህወሃት እስከ አለ ሰላም አያገኝም፡፡ እነዚህ ዘራፊ የኢፈርት ድርጅቶች ገንዘቡን ብቻ ሳይሆን ህይወቱን እየነጠቁት ነው፡፡ነገርም ልክ አለው፡፡በዛ!

2ኛ፡ ለለውጡ ሃይል ያለኝ ጥያቄ-   አስተዋይነት ነው ወይንስ ፍርሃት? ህወሃት ቀደም ሲል 42 የፌደራል ፖሊስ 18 ቀን ከህግ ውጭ ሲያግት ምንም አላላችሁም፡፡ወንጀለኛ ለምን ተነካ የሚለውን ሰልፋን ልተወው፡፡አንድ እናቱ ቀሚስ ውስጥ የተደበቀ ጌታቸው አሰፋን ወንድ የሆንህ ናና ውሰድ ሲል ህወሃትን ጠንካራ ቃል እንኳን አልተናገራችሁም፡፡መከላከያን ሲያግቱ ድምጽ የለም፡፡ጠዋት አሰማርቶ ከሰዐት መግለጫ ይሰጣል ደብሬ.፡፡እናቱ ቀሚስ ውስጥ እየሮጠ በመደበቅ ላይ የነበረውን ህወሃት፤ብሔር ጫካ ውስጥ ስለተደበቀ ምን እናድርግ መባሉ፤ጭራሽ ነፍስ ዘርቶ ለአገሪቱ ህልውና ፈተና ሆኖ አረፈው፡፡ላቡን የሚጠርግበት ደህና ጊዜ አገኘ፡፡የመሸናነፍ ባህል ይቅር የተባለውን ዕድል አፌዘበት፡፡ዛሬ ደግሞ እንደለመደው ለውንብድና ስራው የፋይናንስ ምንጭ በሆነው በሱር አማካኝነት ያሸብራል፡፡እናም የለውጡን ሃይል የምለው”የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ“ነው፡፡ አገራችን አይናችን እያየ እየሟሟች ነው፡፡ሁሉም ወደ በረቱ ሲሰበሰብ አይታያችሁም እንዴ? በቃ ጌታቸው አሰፋ በቁጥጥር ስር መዋል አለበት!!!!!! ህወሃትም በሌላ ሃይል መተካት አለበት፡፡የትግራይ ዝህብ የሚበጀውን መምረጥ ይችላል፡፡እኛን የሚያተራምስ ወንዴ ዋሻ ሆኖ ግን አብሮም ሆነ ተለያይቶ መኖር አይቻልም፡፡ይህ ግልጽ መሆን አለበት፡፡እናንተ በገሃነም እኛን በገነት ተውን ብሎ ፖለቲካ ካለ አላውቅም፡፡

3ኛ፡ ለአንድነት ሃይሉና ለዜግነት ፖለቲካ አቀንቃኞች፡ ራሴም እዚህ በርት ውስጥ ነኝ፤እኖራለሁም፡፡የገረመኝ ነገር አንድነት ሃይሉን የበላው ጅብ አልጮህ አለ፡፡የእነሱ ህዝብ የት ነው ያለው? መግለጫ እንኳን ውድ ሲሆን? ህዝቡንስ ከአክራሪ ብሄርተኞች መንጋጋ ማውጣት፤አገርንስ ማዳን የሚቻለው፤ በችግሩ ጊዜ አብሮ በመቆም አይደለም እንዴ? ብሄርተኛው እኮ ሰልፍ እየወጣለት፤ህይወቱን እየገበረለት ነው፤እንዳነንዱ ደግሞ በትጥቅም አልሁ እያለው ነው፡፡ታዲያ ለዚህ የሚመጥን እንቅስቃሴ ቀርቶ ትንፋሽም አልሰማንም፡፡አገር አብራ ተቦክታ፤አብራ ተጋግራ፤አብራ ነው ሲሳይ የምትሆነው፡፡አባቶቻችን አብረው የጋገሩት እንጀራ ከመሶቡ እያለቀ ነው፡፡በምትኩ ብሄርተኞች ለየብቻቸው እያጋገሩ ነው፡፡ይህ ደግሞ ጉዞው ግልጽ ነው፡፡ እናም ሲፈናቀል ዝም፤ሲሞት ዝም፤ዝም ዝም ዝም….የእናንተ ህዝብ የት ነው ያለው? ለውጡን ማገዝ በዚህ መልክ ነው? በዚህ ጎንደር በተከሰተው  ጉዳይ አክቲቪስቶችን ምን አሉ ብዩ አለፍ አለፍ ብዩ ለማየት ሞከርሁ፡፡በሚገርም ሁኔታ ለወትሮው ኮሽ ባለ ቁጥር የባጥ የቆጡን የሚዘላብዱት ሁሉ ትንፍሽ አላሉም፡፡የሚንጫጩት ያው የክልሉ ሰወች ናቸው፡፡እናም ብቻችንን ሃዘን እንደተቀመጥን ባወቅሁ ጊዜ የባሰ አዘንሁ፡፡ህወሃትን ከመሃል አገር ወደ ዳር የገፋው አንድ ላይ መቆማችን ነበር፡፡

ለማንኛውም ሁላችንም ደጋግመን እናስብ!!! እድሜ ልክ ህወሃት እያልን ልኖር አንችልም፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.