ፍትሕ ለገንደ-ውሐ ጎንደሬ ኢትዮጵያዊያን አሁኑኑ!

በገንደ-ውሐ ጎንደሬ ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ ላይ የደረሠውን ህልፈተ-ህይወት በመስማቴ በጣሙን ተረብሻለሁ። ይህ የመከላከያ እርምጃ በመግለጫ ሣይሆን በመረጃና ማስረጃ ድጋፍ በማያሻማ መልኩተጣርቶ ውጤቱ በአፋጣኝ ለሕዝብ መቅረብ ይኖርበታል። ጥፋተኞች ሆነው በሕዝብ ላይ ግድያ እንዲፈፀም ትዕዛዝ የሠጡ ሁሉ ሕግ ፊት መቅረብ አለባቸው።

በአንፃሩ ይህን የወገን ሞት በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እንደመጠየቅና ጉዳዩ ከመጣራቱ በፊት ለፓለቲካ ትርፍ ሲሉ የዜግነት ፓለቲካን ማውገዝ፣ መንግስታዊና ክልላዊ ባለስልጣኖችን መጣቆሱ አግባብ አይሆንም። “አቶ ገዱ በአብን ይተኩ” የሚል መፈክርም በጎጠኞች እጅ አይቻለሁ።

ይህ ለወገን መቆርቆር ሣይሆን በወገን ሞት ለሥልጣን መቋመጥም ነው። ጠ/ሚ አቢይ ላይም የተርከፈከፈ የነዚሁ ድፍኖችን ፁህፍ አንብቤያለሁ። ጠ/ሚ አቢይ ትግራይም ላይም በሌቦቹ “ሌባ” ተብለው ሲወገዙ ነበር። የኛ ጎጠኞችም ትግራይ ላይ ሲዘንብ ዣንጥላ መያዛቸው ይሆን? አለቆቻቸውን እየመሰሉም ይሆን? ይህም ነውር ነው። በጎጠኝነት ተሠልፎና ጎጠኛ ሆኖ ኢትዮጵያን ከፍ ያደረጉ መሪን መዋጋቱ የሚያመጣው ትርፍ አልገባኝም። ጎጠኞቹ “ቆመንልሃል” የሚሉትን ሕዝብ ላይ ቆመው በአራቱም አቅጣጫ በዋልጌ ዘለፋቸው በየቀኑ የሚገዙለት ጠላት በርክቷል። ይህም የአማራ ሕዝብን ከቀሪው ወገኑ ለመለየትና የፓለቲካ ግብ ለማሣካት የተተለመ የጎጠኞች ሴራም ይመስላል።

ይህንን ክስተት አግዝፎ ማራገብ የሚጠቅመውና እጅ ሥራው የሚመስለው ህወሃትን በመሆኑ ለዚህ እልቂትን እንደ የሃውዜኑን ጭፍጨፋ በተመሳሳይ መልኩ ያቀናበረውን ወያኔ ከማገዝ ውጭ ለሟች ወገኖቻችን ፍትሕን ለማምጣት አይበጅም።

ዛሬም እደግመዋለሁ። ማንኛውም ኢ-ፍትሐዊነትና የወገን ጉስቁልና እንዲሁም ፓለቲካዊ ጭቆና የሚያበቃው በጎጠኞች ድንፋታና ዋልጌነት ሣይሆን በኢትዮጵያውያን ሕብረትና ትግል የሚከበር የዜጎች መብትና ነፃነት እንዲሁም የሕግ የበላይነት የሠፈነበት ዴሞክራሲያዊ ሥርዐትን በማነፅ ብቻ ነው። ለዚህም ከጎጥ ባሻገር ኢትዮጵያዊነትን በማጥበቅና ወያኔ ሠራሹ የጎጥ ፓለቲካ ባለመጨማለቅ ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው የችግሩ ብቸኛ ፈውስ የሆነውን ነፃነትና የዴሞክራሲ እንጂ የጎጠኞቹን ወያኔ ሠራሽ መርዝ የሆነውን “የህመም ማስታገሻ” ወይም ጎጠኝነት አይደለም።

Hailu T

#EBC በምዕራብ ጎንደር ዞን በተፈጠረው የፅጥታ ችግር ምክንያት በጠፋው የሰው ህይወት የክልሉ መንግስት ማዘኑን የአማራ ክልል ርዕሰ መሰተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ፡፡

Posted by Solomon Gadissa on Thursday, January 10, 2019

1 COMMENT

  1. በምእራብ ጎንደር በደረሰው እልቂት የተለኣዩ መግለጫዎች እየወጡ ቢሆንም የተረጋገጠውን ለማወቅ የኣጣሪ ኮሚቴውን ሪፖርት ጠብቆ መስማት ይበጃል።
    ኣንድ የተረጋገጠ ነገር ቢኖር ያካባቢው ህዝብ በሱር ኮንስትራክሽን ድርጅት ላይ ያለው ጥርጣሬ ነው።የህዝብን ኣመኔታ ያጣን እንቅስቃሴ መንግስት በቀዳሚነት ማጣራት እና ህጋዊ ያልሆነ ድርጊት ካለ ለሚመለከተው የፍርድ ቤት ኣካል ማቅረብ ግዴታው ነው።
    ከላይ ከተጠቀሰው ድርጅት ባለቤት የሆነው ኤፈርት ድርጅት በሚያስተዳድራቸው ሌሎች ድርጅቶችም ውስጥ ኢፍታዊነት አና ጸረ ህግ ተግባራት በሰፊው በህዝቡ ዘንድ ሲነሳ በተደጋጋሚ ይሰማል።
    ስለዚህ መንግስት የሱር ኮንስትራክሽን ድርጅትን መነሻ በማድረግ በህብረተሰቡ ዘንድ በሰፊው የሚነሳውን ጥርጣሬ ለማጥራት በ ኤፌርት ያሉ ድርጅቶችን ከመነሻቸው ጀምሮ ያለውን ሂደታቸውን ተኣማኝነት እና ገለልተኛ በሆኑ ባለሞያዎች ኦዲት ኣስደርጎ ጥፋትም ካለ ልማት ለህብረሰሰቡ እንዲያቀርብ ቢያረግ የህዝቡን ጥርጣሬ ሊያረጋግጥ ወይም ሊያስወግድ ይችላል ብዬ ኣስባለሁ።
    እንኩዋን የህዝብ የኣንድ ግለሰብም ጥርጣሬ መናቅ ኣይገባውምና።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.