አንዳንድ ሰዎች የአፋር ህዝብ ሰላማዊ ቅረታን ወደ ራሳቸው አላማ ለመቀየር እየሞከሩ እንደሆነ ይታያል

በአካደር ኢብራሂም

በእርግጥኘት የአፋር ህዝብ አሁንም በሙሉ ልቡ ከልውጡና ከልውጥ አማራሮች ጎን ነው።

የአፋር ህዝብ ቅረታዉን መንገድ በመዝጋት አድማ (Strike) ስላሰማ ዶ/ር አብይን ተቃዉመዋል ማለት ሳይሆን ለዶ /ር አብይ ጥያቄ አቅርቧል በማለት ቢተሮገም ጥሩ ነው !

አንዳንድ የህወሓት ህልመኞችና የቀድሞ አንባገነኖች ለህዝቡ ጥያቄ ሌላ ትርጓመ ለመስጠት ‘’The end of Aby’s Regime’’ በማለት የትግሉ አቅጣጫ ለማስቀየር ስሞክሩ ይታያሉ።

ሲጀመርም ይህንን ችግር እንዲፈጠር ለላፉት 28 አመታት የሶማሌ ኢሳዎች ጋር በኮንትሮባንድ በመደራጀት የአፋር መሬት የሸጡት ህወሓቶች ናቸው።

አቶ አባይ ጸሃዬ ለዚህ ዋነኛ ተጠያቂ ሲሆኑ የኢሳ ኮንትሮባንድስቶች የገርቷን ኢኮኖሚ በማዳከም መግድሃንቶች ሳይቀሩ ከጀቡቲ በግመሎች እያስገቡ ከከፍተኛ የመከላኪያ ጀኔራሎች ጋር ሲሰሩ የቆዩሰዎች ናቸው።

አሁንም የአፋር ክልል የህወሓት ሹማምንቶች በተሰናበቱ በሁለኛው ቀን የአብዲ ኢሌ ደገፊዎች የሆኑ ቦዘነዎች የአፋር ክልልን ባንዲራ በማቃጠል አከባቢው በፈጠሩት ችግር  የህወሓቶች ርጃጅም እጆችአሉበት።

በሌላ በኩል በግልጽ የጀቡቲ መንግስት ጣልቃ ገብነት እንዳለበት እየታወቀ የኢትዮጲያ መንግስት ለወደብ ጥቅሙ የዜጎቹን ጥቅም መሸጥ የለበትም ነው የአፋር ህዝብ ዋናው ጥያቄ።

ሌላው ደግሞ ጉዳዩን በቅርበት የማይውቁ ሰዎች የአፋርና ኢሳ ግጭት ተራ የግጦሽና የዉሃ ግጭት ነው በማለት ያምናሉ።

አሁን ያለው ግጭት ግን በፉጹም ከዚህ ጋር የተገናኘ አይደልም።

ጉዳዩ የፖለቲካ ግጭት ሲሆን በኢትዮ ሶማሌ ክልል አንዳንድ መሪዎች፣ በጀቡቲ መንግስት፣ በኦጋደን ነጻ አውጪ ግንባርና በኢሳ ኡጋሽ በስትራተጂ የሚመራ የኢሳ ሶማሌ ግዛት የማስፋፋት ዕቅድ ነው።

በጉዳዩ ላይ የአፋር ክልል መንግስት በሰጠው መግለጫ እንደተገለጸው የአፋር ክልል ባንዲራን በማቃጠል የሶማሌ ክልልን ባንዲራ እንዲሰቀል የተደረገው በሶማሌ ክልል አንዳንድ መሪዎች ግፍት ነውተብሏል።

የሶማሌ  ክልል ባለስልጣናት ወደ እኛ ክልል ከተካለላችሁ ቀበሌ ሳይሆን ወርደ እንስጣችኃለን በማለት ህዝብን ያነሳሳሉ ሲል የአፋር ክልል ከሷል።

ይሁን እንጂ አሁን በአፋር ክልል ስር የሚተዳደሩ የኢሳ ጎሳዎች በቀበሌ ሲደራጁ የአፋር ህዝብ ሳይስማማበት፣ ለአፋር ክልል ፓርላማ ሳይቀርብ በአዋሽ በሚገኘው የመከላኪያ ሰራዊት ካምፕ ውስጥበድብቅ የተፈራረሙት ሰነድ ስለሆነ በምንም አይነት መለኪያ ተቀባይነት የለዉም።

መፍትሄው በእነ አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘጋጀው የአፋር ህዝብ እውቅና የለለው ስምምነት ፈርሶ በአከባቢው ሁሉም ኢትዮጲያዊ እንደ ሌሎች የአፋር ክልል አከባቢ መኖር የሚችልበት ሰላም መፍጠር ብቻነው።

ዛሬ ከተሰሙት መፈከሮች አንዱ የአፋር ህዝብ በፍቅር አብሮ መኖር ያውቅበታል ግን በመሬቱና በምስቱ አይደራደርም የሚል ነበረ።

መንግስት ጉዳዩን ቀለል አድርጎ ማየቱ ችግሩ እንዲባባስ ያደረገው ሲሆን በዛ አከባቢ የአፋር ህዝብና ጸጥታ ሃይሎችን እያጠቁ ያሉት በህግ የማይገዙ ከተለያዩ አከባቢ የተሰባሰቡ ኮንትሮባንድስቶችናቸው።

ስለዚህ መንግስት ከህዝብ ጋር በመወያየት ትክክለኛዉን እርምጃ ካልወሰደ በአከባቢው ልፈጠር የሚችለው የጸጥታ መደፍርስ አደገኛ ይሆናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.