ጠ/ሚ ዐቢይ ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ከፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር በዘርፉ እየተካሄዱ ባሉ የለውጥ ሂደቶች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የዘርፉ ማሻሻያ የፋይናንስ ተቋማቱን አቅም በመገንባት የበለጠ ተፎካካሪና ብቁ ሆነው ምጣኔ ኃብትን ለማሳደግ ያላቸውን ሚና በማጠናከር ላይ ያተኩራል።

በውይይቱ እስካሁን ድረስ በፋይናንስ ዘርፍ የተደረጉት ለውጦች የተዳሰሱ ሲሆን በዘርፉ ያሉ የፖሊሲ፣ የአሠራር ሂደትና የአስተዳደር ማነቆዎችን ተለይተዋል፡፡

የፋይናንስ ዘርፉ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር እንዲሁም የመንግስት ፕሮጀክቶችን ለመደገፍ የሚኖሩት ሚናዎችና ኃላፊነቶችም በውይይቱ ተለይተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የፋይናንስ ተቋማት ኃላፊዎችና ተወካዮች ለአገር አቀፍ የመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

ምንጭ፡- የጠ/ሚ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.