የኦነግ ጦር እጁን እየሰጠ ነው -ናኦሚን በጋሻው

የደቡባዊ ዞን የኦነግ ጦር መሪ የሆኑት ጃል ኤሊያስ ጋምቤላ የአባገዳዎችን ጥር በመቀበል ጦራቸውን አስቀምጠው በሰላማዊ መልክ ለመታገል ወስነው ትጥቃቸውን  እንዳስረከቡ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። በዳዎድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ፣ በጉጂ፣ ቦረና፣ ምእራብ ፣ ሆሮ ጉድሩ፣ ቄሌም ወለጋ ዞኖች በመንቀሳቀስ አካባቢዉን የጦርነት ቀጠና ማድረጉ ይታወሳል። ኦነጎች በመቶ ሺሆች ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል፣ ለብዙዎች መሞት ምክንያት ምክንያት የህፖኑ ሲሆን፣ ደቡብና መራብ የኦሮሞ ክልል የጦርነት፣ የሽብርና የሁከት ቀጠና አድርገዋት ቆይተዋል።

በቅርቡ በወለጋ ከአስራ ሰባት በላይ ባንኮች የተዘረፉ ሲሆን ፣ የመከላከያ ሰራዎት የኦነግ ምሽጎች ለመደምሰስ ሔሊኮፕተር እስከመጠጥቀም እድረሱን መረዎችይ ይጠቁናሉ።

በኦሮሞ ክልልው ውስጥ በኦነጎችና ጽንፈኛ የኦሮሞ አክራሪዎች የሚፈጸᎁትን ወንጀሎችና ግፎች እየደበቀና እየሸፋፈነ ፣ የኦነግ አመራሮች የመለማመጥና የማባባል ፖለቲካ ያራምድ የነበረው በዶ/ር አብይ አህመድ የሚመራው ኦዴፓ/ኦህዴድ በኦሮሞ ክልል ያለውን ቀውስ መደበቅ ባለመቻሉ ጉዳዩን ለሕዝብ ይፋ በማድረግ፣ የመከላከያ ሰራዊት በክልሉ እንዲገባ ፈቅዷል። ከዚህም የተነሳ፣  በርካታ የኦነግ ታጣቂዎች የተገደሉን ካምፓቸውን የተደመሰሰ ሲሆን፣ በቦረና ጉጂ ይንቀሳቀስ የነበረው የኦነግ ጦር አዛዥ ኤሊያስ ግምቤሳና አብረዉት ያሉ ታጣቂዎች እንዳደረጉት ብዙዎችንም የሃይል ሚዛኑን በማየት ትጥቃቸውን በመፍታት እጃቸዉን እየሰጡ ነው።

1 COMMENT

  1. Fake news/propaganda! Your ጃል ኤሊያስ ጋምቤላ is not and never been a leader of any WBO unit, and has run away from the front a year ago!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.