ቢያጠፋም ልጆቻችን ናቸው! እንደምንም መፍትሄ እንፈልግ (አሰፋ በድሉ)

ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ሞትን ሸሽተው ባ/ዳር ስለሚገኙት ተማሪወች መፍትሄ ለማዋጣት ነው፡፡ጊዜው መላ በቀላሉ የሚገኝበት አልሆነም፡፡አጣብቂኝ ውስጥ ስላለን ነው፡፡ይህም አጣብቂኝ ደግሞ የሚታወቅ ተደጋግሞ የተወሳ 27 ዓመት የዘራነው በቅሎ፤አብቦ፤ ዕየተሰበሰበ እና የአገር ህልውና መፈተን ላይ የሚገኝ ነው፡፡ለዚህም ነው የተማሪወችን ጉዳይ የተሜ ነገር ብቻ ሳይሆን ሁላችንም የጉዳዩን እንድምታ በዚህ ደረጃ ማየትና መረዳት የአለብን፡፡ልጆቹ የአዩትን እኛ አላየንም፡፡መሄድ ሲያስቡ የሚሰማቸውን ስሜት እነሱ ናቸው የሚያውቁት፡፡የመንግስትም ችግር በእጅጉ ይገባኛል፡፡ይሄ ውሳኔ ማለትም የዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን በየክልላቸው መመደብ፤አገር የማፍረስን ፕሮጄክት ቀጥታ ወደ ተግባር መለወጥ ነው የሚሆነው፡፡ሁሉም ለእኔ የማትመች ኢትዮጵያ ባይ ሆኗል፡፡ግን ኢትዮጵያ ሲመቸን፤ሲመቸን ብቻ የምንወዳት ሳይሆን ሳይመቸንም የምንኖርባት በዋጋ እዚህ የደረሰች አገር እንጂ ራሷ ለእኛ ጉቦ እየሰጠች ህልውናውን የምታስቀጥል አይደለችም፡፡በዚህ ተለማኝም ለማኝም የለም፡፡ የትግራይ ተማሪወች ገና በፍራቻ ቢሆንም ዪኒቨርሲቲ ሲከፈት በክልላቸው እንዲመደቡ በሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀው ነበር፡፡መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ከፊትም ከኋላም አብረው ነበሩ፡፡መንግስት በወቅቱ ጆሮ አለኝ አላለም፡፡ትክክል ነው፡፡የእነዚህ ግን ይለያል፡፡በተግባር ችግር የደረሰባቸው ናቸው፡፡ለልጆቻችንም፤ለመንግስትም ዕና ሌሎች አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ለሚችሉ አካላት የማቀርበው የመፍትሄ ሃሳብ፡፡

1ኛ፡ ልጆቹ በተደጋጋሚ ተጠይቀው በእምቢታ የጸኑት ችግሩ ጽኑ ስለሆነ መሆን አለበት፡፡ስለዚህ ከቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ውጪ ባሉ የዚ ክልል፤የዚያ ክልል ሳይባል በሁሉም የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲወች በዕጣ መመደብ የተሻለ ይመስለኛል፡፡

2ኛ፡ የተገለጸው መፍትሄ ተመራጭ ካልሆነ ከልጆቹ ጋር፤ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተመካክሮ፤የተወሰኑ ተወካዮች ከአስፈላጊው ጥበቃ ጋር መጀመሪያ ሄደው የራሳቸውን ምልከታ አድርገው እንዲመለሱ መላክ፡፡ተወካዮችም ተመልሰው ከጓደኞቻቸው ውይይት ቢያደርጉ፤ ከዚያ በኋላ መንግስት በሚሰጣቸው ጥበቃ ዙሪያ ድርድር ተደርጎ፤ይህም ስምምነት ለህዝብ ይፋ ቢደረግና ነገሩ በዚህ ቢቋጭ ጥሩ ይመስለኛል፡፡

በመጨረሻ ያለኝ መልክት

ለልጆቻችን– ተስፋ መቁረጥና ከወገናችሁ ጋር ግጭት ውስጥ መግባት ትክክል አይደለም፡፡ጥያቄአችሁ ሁሉ ስርዐትንና ህግን የተከተለ መሆን አለበት፡፡ ከአስፈለገ እኮ መንግሰትን ጠበቃ ቀጥራችሁ መክሰስ ትችላላችሁ፡፡ማህበር በከተለያየ ቦታ ህይወት አገናችሁ እናም በዚሁ አጋጣሚ ማህበር መመስረት መብታችሁ ነው፤ማስረጃወቻችሁን አደራጅታችሁ፤ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ እንድንማር ተገደናል በሚል መንግሰትን መክስስ ይቻላል፡፡የህጉን ጎዳና በትይዩ ለማንሳት ነው፡፡መንግስት ዋስትና መስጠት ግዴታው ስለሆነ፡፡ከዚህ ውጭ ሌሎች ሰላማዊና ሞራላዊ ጫናወችን መጠቀም ይቻላል፡፡ ከሁሉ በላይ ግን ከአባቶቻችሁ ምክር አትውጡ፡፡ ያሳዘነኝ ስድብ የጠፋ ይመስል፤ ህወሃት ሁመራ ላይ ጠቅላያችንና ገዱን ለማሰደብ ያሰለፋቸውን ተሳዳቢወች ስድብ ተውሳችሁ ሌባ ሌባ ማለታችሁ አሳፋሪ ነው፡፡ይህ የህወታችሁ ወሳኝ ምዕራፍ ስለሆነ በምትወስኑት ውሳኔ ድጋሜ እንዳትጸጸቱ እርግጠኛ መሆን አለባችሁ፡፡

ለመንግስት – አገርን የማይጎዱ ሌሎች መፍትሄወች ሊኖሩ ስለሚችሉ አሁንም ጥረት ቢደረግ፡፡ ከዚህ ውጪ «ከተማችንን ለቃችሁ ውጡ» ያሉ ሃላፊወች እንዳሉ ከአብን መግለጫ አንብቤአለሁ፡፡ይህ ሃላፊ በአስቸኳይ መነሳት አለበት፡፡በይፋም ይቅርታ መጠየቅ አለበት፡፡ይህ ለተማሪወች ተብሎ አይደለም፡፡ባ/ዳር የሚኖርና መኖር የማይችለውን ዜጋ ፈቃጅና ከልካይነት ሰልጣን ማን ሰጠው? ኢህአዴግ ሃላፊወቹ ስለ ሰነ መንግስት ስር የሰደደ የግንዛቤም ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡ህወሃት ያስተማራቸው የሚያውቀውን ግምገማና ተንኮል ነው፡፡መንግስት ከተሾሙ በኋላም ሆነ በፊት ስልጠና ቢሰጣቸው ይረዳል ዕላለሁ፡፡ፖሊስ መንገድ ላይ አንዴ ሳይዠልጥ ስራ መስራት መቻሉን አሁንም እርግጠኛ አይደለሁም፡፡የድርጅትና መንግሰትን ሚና አለመለየትም ሌላው ችግር ነው፡፡በ24 ሰዓት ውስጥ ለቀህ ውጣ የሚባል የውጪ ዜጋ ነው፡፡የዚህ ተናጋሪ ስልጣን ልጆቹ ከአጠፋ አጥፊውን፤ በጅምላም አይደለም አጥፊውን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ነው፡፡ከዚያ ፍ/ቤት የሚወስነው ተግባራዊ ይሆናል፡፡እነዚህ ልጆች በገጠማቸው ችግር ከትምህርት ገበታ ገለል ያሉ እንጂ የግል ህይወታቸውን እንኳንስ ባ/ዳር የትም፤የትም፤መኖር መብታቸው ነው፡፡በዚህ ጉዳይ ከአንድ አፍቃሪ ኦነግ ጓደኛየ ጋር ከደቡብ ከጉራፈርዳ ስለተፈናቀሉት ሰወች በነበረን ውይይት ያልሁት ትዝ ይለኛል፡፡ ባካችሁ ውጣልኝ የሚባል የውጭ ዜጋ ነው፡፡እሱም ከአጠፋ! ይህ ተላላፊ በሽታ ስር እየሰደደ መሆኑን ይህ ሃላፊ ማሳያ ነው፡፡አሁንማ አባወራም ቤተሰቡን ውጡልኝ ማለት ነው የቀረው! ዜጋ ከአጠፋ በቦታው ለህግ ማቅረብ ነው፡፡አባት ሲያጠፋ፤ለምን ሚስት? ለምን ልጅ? ለምን? ለምን ? ስለሆነም ይህ ሃላፊ መነሳት አለበት!!! በነገራችን ላይ የአቶ ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው በዋስ መፈታት ከእስሩ በላይ በጣም አስደስቶኛል፡፡ለምን ካላችሁኝ ፍ/ቤታችችን ነጻ ሆነው ስራ መስራት መጀመራቸውን ስላየሁ ነው፡፡ብርቱካን የከፈለችውን ዋጋ የአሁኖቹ አይከፍሉምና፡፡ብራቮ ጠቅላያችን! ህወሃት ስላልሰረቀ አይደለም፤ ያንን የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቃል፡፡ግን ዳኛ እጁ ላይ ባለው ማስረጃ እንጂ በሌላ በምንም መዳኘት ስሌለበት ነው፡፡የሚዲያ ነጻነት ተጠብቆ መቀጠል አለበት፡፡መቼስ ከዚህ በላይ አንቃጠል፡፡የህግ ማውጣት ዳር ዳርታ አለ! ይሄ ምልክት ግን…ምቾት አልሰጠኝም፡፡ይቺኑ የምንቀባጥራትን…

ለአማራ ህዝብ – ይህ ህዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተረጋግቶ መሪውን መለየት ያለበት ውቅት ላይ ይገኛል፡፡የትግራይን ህዝብ ህወሃት ምን አይነት ችግር ውስጥ እንደከተተው እየታየ ያለ ሃቅ ነው፡፡ አለዘመድ ነው ያስቀረው ባጭሩ፡፡እንዳያማርጥ እንኳን አማራጭ በክልሉ እንዳይኖር ብቻ ሳይሆን እንዳይታሰብ ነው ያደረገው፡፡የህዝቡ ምርጫ ራሱ ብቻ እንዲሆን ወስኖ ሰርቷል፡፡አይገርምም፤ዴሞክራሲና ህወሃት አይተዋወቁምና፡፡ከዚህ የአማራ ህዝብ ትምህርት መውሰድ አለበት፡፡ህወሃት የአማራ ህዝብ  ለፍትህ ፤ለርትዕ ያለውን አቋም ስለሚያውቅ (“በውል ከሄደች በቅሎየ፤ያለ ውል የተበላች ቆሎየ” ነዋ የሚለው) ያሰበውን ዘላለማዊ ስልጣን፤ውንብድና፤ስርቆት፤ክህደት ወዘተ…አንዳይሰራ ይከላከለኛል ብሎ ስለፈረጀው ጠላቴ ብሎ ሰነድ ሰነዶ፤ቢሮ አቋቁሞ፤ሰድቦ ለሰዳቢ ሰጥቶ፤ ከሶ አስከስሶ፤ገድሎ አስገድሎ ዛሬ  ደርሷል፡፡የትግራይን ህዝብ ማንኘውንም ችግር የአመጣብህ ነፍጠኛ ነው በማለት በሃሰት አጥምቋል፤ዛሬ ድረስ ዘልቋል፡፡ነፍጠኛ የሚለው ስምም የሰማዕታት ሃውልታቸው ላይ በጉልህ ተጽፎ ይገኛል፡፡ይህ ድርጅት ወገኔ ፤ወንድሜ ብሎ የሚወደውን የትግራይ ህዝብ ላይ ምንም ሳይደርስበት ቀርቶ ባላሰበበት ሁኔታ በጠላትነት ፈርጆ ተበቅሎታል፤ዛሬም ቀጥሎበታል፡፡ይህንን ጥልቀት ያለው ፤ ፖለቲካ የራቀው ጠንካራ ዕርቅ ቢፈታው ደስ ይለኛል፡፡ዋና ጸባችን የሚታወቅ ነው፡፡1ኛ፤ህወሃት በአሜሪካና በአረብ፤እንዲሁም በራሳችን ታግዞ፤ ለምን ቢባል በወቅቱ የደርግን ጭካኔ እንጂ የእነሱን ባህሪ ብዙወቻችን አናውቅም ነበርና ብቻ በእነዚህና በሌሎች አስቻይ ምክንያቶች ታግዞ ሳንፈቅድ መሬታችንን ቆርሶ ወስዷል፡፡ይህ ለአማራ ሽንፈት ነው፡፡የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ አይደለም ዋናው የክብር ጉዳይ ነው፡፡2ኛ፤ ይህንን ህዝብ በራሱ በትግራይ ህዝብና በሌሎች ኢትዮጵያውያን ጠልቶ በማስጠላት የዘረኝነት ቅስቀሳ በማድረግ እንዲሳደድና እንዲሞት አድርጓል፡፡እነዚህ ከተፈቱ እርቁ መሠረት ይኖረዋል፡፡አለበለዚያ የገዱና የአባይ ወልዱ የግጨው እርቅ ነው የሚሆነው፡፡ህወሃት በዕርቅም ሸር ይሰራል፤ እናም የማያፈናፍን አሰታራቂ ያሻል፡፡ዝንጀሮ የሌላው እንጂ የራሷ ጠባሳ አይታያትም እንዲሉ፤ 42 ዓመት ምን እንደሰሩ ረስተውት ዛሬም ተበዳይ ሆነው ሲቀርቡ አይተናል፡፡ህወሃት ከሃዲነትን፤ሃላፊት አለመውሰድን ከደደቢት ጀምሮ እስከ አሁን ከራሱ አልፎ ለእሱን መስል ድርጅቶች አውርሷል፡፡ ከኋላ እያሰገደሉ፤ በአደባባይ ደግሞ አይ እኛ እኮ ሰላማዊ ትግል ነው የምንከተለው….ከሃዲ…

ወደ ጉዳየ ስመለስ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ የአማራ ህዝብ ተጎድቷል ብለን የምናምን ሁሉ የህወሃት ትግል መቼ ተቋጭቶ ነው ልጆቻችንን የምንታገለው? የህወሃትን የቅማንት ፕሮጄክት የምናስፈጽመው? ዛሬስ ህወሃት ባሉት ድርጅቶች ክልሉን እየዘረፈ እያለ ለምንድን ነው እኛ ክልሉ ውስጥ ጦርነት የምንጭረው?የአማራ ህዝብ እኔ ሳውቀው አስተባባሪ፤መሪ፤አካታች፤አገር ወዳድ፤ ለትልቁ እንጂ ለትንሹ ሃሳብ ቁብ የሌላው፤ ለዕለት ጉርስ ሳይሆን ለቅርስ ፤ለውርስ የሚጨነቅ፤ የአባቶቹን አደራ የማይበላ ነው፡፡ምንም ቢርበው፤ቢቸግረው እንኳን ያልቸገረውን ገዳም አያርስም፡፡ይሄ ዕርም ነው፡፡እናም በዚህ ህዝብ ዙሪያ ያለን ፖለቲከኞችና ተቆርቋሪወች ህወሃትን መታገል ያለቀ ይመስል ስለራሳችንና ስለ ድርጅት አመሰራረት ማውራት ትተን ህወሃትን ከነ ክፋቱ ሸኝተን ህግና ዴሞክራሲን መትከል የሚያስችሉንን አቅጣጫወች ብንከተል አገርም እናድናለን ህዝብም እንጠቅማለን፡፡ጦርነቱን ራሳችን ቤት ጀመርነው እኮ ፡፡ለምሳሌ በሱር ጦስ የደረሰብን የትናትና የዛሬም ቁስላችን ነው፡፡ሱርን በህግ ቢያንስ በክልሉ እንዳይሰራ፤ውሎች እንዲሰረዙ…ወዘተ ማድረግ ይቻላል፡፡ይቆንጠጥ የሚል እንኳን አልሰማሁም፡፡ሌላ የሚሰራው መንገድ እንዳለ እንኳን የሰማሁት ከአቶ ገዱ የሰሞኑ መግለጫ ነው፡፡እያሰቡ መርሳት ማለት ይቺ ናት፡፡በ2010 ዓ.ም ከኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የወሰደውን የመ/ቤቱን ግማሽ በጀት አቻምየለህ ታምሩ መረጃውን ከራሱ ከመ/ቤቱ ምንጭ ጠቅሶ አጋርቶን ነበር፡፡ አልተጠቀምንበትም፡፡የለውጡ ሃይል አሁን ህወሃት ላይ ዕርምጃ ለመውሰድ ያለው አፒታይት ዝቅተኛ ነው፡፡በተግባር መፈተን፤መፈተሸና ለህዝብ ፍርድ ማቅረብ ተገቢ ነው፡፡የኢፈርትን ትልቅ ውንብድናና ወንጀል ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ መረጃወችን ማሰባሰብ፤ታዋቂ ባለሞያወችን ማማከር..ወዘተ..በአጭር ጊዜ ሊሰሩ የሚችሉ ናቸው፡፡የህወሃት ጉድ ያለው እዚህ ድርጅት ውስጥ ነው፡፡ለምሳሌ ሱር ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ይላል፡፡በነማን ስም ነው የተመዘገበው? ህዝብ የማወቅ መብት አለው፡፡ንግድ ሚ/ር..ለካ ወ/ሮ..ናቸው ያሉት፡፡ይቅርታ፡፡እነዚህ ስማቸውን የሰጡ ግለሰቦች ይህን ሃብት ከየት አመጡት ? በዚያውም ዴሞክራሲያዊና ህጋዊ ስርዐት መጀመሩን መፈተኛ ይሆናል፡፡ህወሃትን  በዘር ማጥፋት ወንጀል፤ ወይም በአሸባሪነት ፍ/ቤት መገተር ይቻላል፡፡ምን የሚከለክል ነገር አለ፡፡ሌሎች መናገር የማልፈልጋቸው ማስረጃ ሊሰባሰብባቸው የሚገቡ አፋጣኝ ስራወች መስራት አለብን! ስለሆነም ቀልብን ሰብሰብ፤ንዴትን ቀነስ፤ቁም ነገርን ጨመር ማድረግ ይገባል፡፡የዚህ ህዝብ ታሪክ አስለቃሽዋ እንዳለችው “አሞራና ዶሮ አይ እኛ (ሰው) ና ሞት ሲመጣ መንጫጫት፤ሲሄድ መረሳት” አይደለም፡፡ታሪክ ሰሪ ነው፡፡ሙያ በልቡ ነው፡፡እንዲያው ሁሉም እኮ አይነገርም፡፡ቦታ ቦታ አለው!

ለህግና ለዴሞክራሲ እተባበራለሁ!

2 COMMENTS

 1. ተባረው የመጡት በባህርዳር የሚገኙት የአማራ ዘር ተማሪዎች ፣የደረሰባቸውን ችግር እነርሱ ብቻ ናቸው በደንብ የሚያውቁት። ምንም ፀሐፊው በበጎ ሐሳብ ምክርን ቢለግስም ፣አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ምክሩ በፍፁም አብሮ አይሄድም ።
  ተማሪዎቹ ጠበቃ ቀጥረው መንግስትን እንዲከሱ ይላል። ለመሆኑ የትኛውን መንግስት? የፌደራል መንግስትን ፣ተማሪዎች በተመደቡበት በሰላም መማር ባልቻሉበት ሁኔታ፣ መጤ ተብለው ሲባረሩ ፣የትኛውን የደህንነት ከለላ አድርጎላቸዋል።የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ መብትንና የአካለተ ጥበቃ በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት የመጀመሪያና መሠረታዊ ስራ ነው። ይሄ ደሞ በተለይ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በተለያየ ክልል በደረሰባቸው መባረር ብቻ ሳይሆን ግድያና ለደረሰባቸው ጉዳት የፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ የለም። እንግዲህ ባለመቻል ወይም በግዴለሽነት መንግሥት ያሳለፈውን ሁኔታ ከራሱ ማለት ፣ተከሳሹ የፌደራሉ ይሁን የክልሉ ውሉ ባልታወቀበት የአሁን ጊዜ ፣ይሄን አይነት ምክር እንደፌዝ ይቆጠራል ። በመጀመሪያ ሕግና ፍትህ ባለበት ቦታ ነው ክስ የሚመሠረተው ። የፌደራሉም የክልሎችም ጥርስ አልባነት ለዚህ አይነትሁኔታን ኢትዮጵያን ዳርጓታል ። የዚህ ሁሉ መነሻና መድረሻ ይሄው እኩዩ ሕገመንግሥት መሆኑ የተገነዘብነው አይመስለኝም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ግዛት የመኖር የመንቀሳቀስ መብቱ ህልም የሆነበት ጊዜ ነው።
  በአፋጣኝ ግን የአማራ ክልል መንግስት ለተማሪዎቹ የማያወላውል መልስ መስጠት ይገባዋል። ይሄውም በክልሉ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲ) ማደላደል ነው። ምነው የሌላው ክልል መንግስታት ተባረርን ያሉትን ወገኖቻቸውን በክልላቸው መድበዋል ። የትኛዎቹንስ ነው ወደመጣችሁበት ተመለሱ የተባሉት።
  የአማራ ክልል መንግሥት የበፊት ሎሌነቱን አሁንም አልተላቀቀውም። ቢሆንና የባህርዳር ከንቲባው ይሄን አይነት ወራዳ ውሳኔ ሲሰጥ የክልሉ መንግሥት ምክር አይለግስም ነበር። ጭሰኛ የገባርነት መብት እንደሌለው እያሳዩን ነው።
  የትምህርት ጥራቱ በወደቀበት ዘመን በተጨማሪ ታዳጊውን ከትምህርት ገበታ ማስተጓጎል የሃገርን ኤኮኖሚም እንደሚጎዳ ሃላፊዎቹ የተገነዘቡት አይመስልም ። የስብእና የህሊና ጉዳዩን በግዴለሽነት ቢተላለፍም እንኳን ።ይህ የተማሪዎቹ ተቃውሞ የሁሉም አማራ ተቃውሞ መሆኑ መረሳት የለበትም።ችግር ፈጣሪዎች ተማሪዎቹ ሳይሆኑ ያባረራቸው ክልሎች ናቸው ፣ ብሎም ለደረሰባቸው ጥቃት ምንም አይነት ከለላ አለመስጠት የችግሩ መንስዔ ነው።

 2. ተባረው የመጡት በባህርዳር የሚገኙት የአማራ ዘር ተማሪዎች ፣የደረሰባቸውን ችግር እነርሱ ብቻ ናቸው በደንብ የሚያውቁት። ምንም ፀሐፊው በበጎ ሐሳብ ምክርን ቢለግስም ፣አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ምክሩ በፍፁም አብሮ አይሄድም ።
  ተማሪዎቹ ጠበቃ ቀጥረው መንግስትን እንዲከሱ ይላል። ለመሆኑ የትኛውን መንግስት? የፌደራል መንግስትን ፣ተማሪዎች በተመደቡበት በሰላም መማር ባልቻሉበት ሁኔታ፣ መጤ ተብለው ሲባረሩ ፣የትኛውን የደህንነት ከለላ አድርጎላቸዋል።የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ መብትንና የአካለተ ጥበቃ በመጀመሪያ ደረጃ የመንግሥት የመጀመሪያና መሠረታዊ ስራ ነው። ይሄ ደሞ በተለይ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች በተለያየ ክልል በደረሰባቸው መባረር ብቻ ሳይሆን ግድያና ለደረሰባቸው ጉዳት የፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ የለም። እንግዲህ ባለመቻል ወይም በግዴለሽነት መንግሥት ያሳለፈውን ሁኔታ ከራሱ ማለት ፣ተከሳሹ የፌደራሉ ይሁን የክልሉ ውሉ ባልታወቀበት የአሁን ጊዜ ፣ይሄን አይነት ምክር እንደፌዝ ይቆጠራል ። በመጀመሪያ ሕግና ፍትህ ባለበት ቦታ ነው ክስ የሚመሠረተው ። የፌደራሉም የክልሎችም ጥርስ አልባነት ለዚህ አይነትሁኔታን ኢትዮጵያን ዳርጓታል ። የዚህ ሁሉ መነሻና መድረሻ ይሄው እኩዩ ሕገመንግሥት መሆኑ የተገነዘብነው አይመስለኝም። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያ ግዛት የመኖር የመንቀሳቀስ መብቱ ህልም የሆነበት ጊዜ ነው።
  በአፋጣኝ ግን የአማራ ክልል መንግስት ለተማሪዎቹ የማያወላውል መልስ መስጠት ይገባዋል። ይሄውም በክልሉ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት(ዩኒቨርሲቲ) ማደላደል ነው። ምነው የሌላው ክልል መንግስታት ተባረርን ያሉትን ወገኖቻቸውን በክልላቸው መድበዋል ። የትኛዎቹንስ ነው ወደመጣችሁበት ተመለሱ የተባሉት።
  የአማራ ክልል መንግሥት የበፊት ሎሌነቱን አሁንም አልተላቀቀውም። ቢሆንና የባህርዳር ከንቲባው ይሄን አይነት ወራዳ ውሳኔ ሲሰጥ የክልሉ መንግሥት ምክር አይለግስም ነበር። ጭሰኛ የገባርነት መብት እንደሌለው እያሳዩን ነው።
  የትምህርት ጥራቱ በወደቀበት ዘመን በተጨማሪ ታዳጊውን ከትምህርት ገበታ ማስተጓጎል የሃገርን ኤኮኖሚም እንደሚጎዳ ሃላፊዎቹ የተገነዘቡት አይመስልም ። የስብእና የህሊና ጉዳዩን በግዴለሽነት ቢተላለፍም እንኳን ።ይህ የተማሪዎቹ ተቃውሞ የሁሉም አማራ ተቃውሞ መሆኑ መረሳት የለበትም።ችግር ፈጣሪዎች ተማሪዎቹ ሳይሆኑ ያባረራቸው ክልሎች ናቸው ፣ ብሎም ለደረሰባቸው ጥቃት ምንም አይነት ከለላ አለመስጠት የችግሩ መንስዔ ነው።
  ልጆቻችን አላጠፉም።መፍትሄ መፈለግ ግን ግዳጅ ነው

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.