ህወሓት የዓረና ኣባላት ለማሸበር፤ከመቶ አስር ሺ በላይ ምልሻዎች ኣስታጠቀ

ህወሓት የዓረና ኣባላት ለማሸበር፤ ለማሰርና ለማሰቃየት ከ 110,000(ከመቶ አስር ሺ በላይ) ምልሻዎች ኣስታጥቋል፡፡ ዛሬ የኛ ኣባላት በደቡባዊ ትግራይ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በምልሻዎችና በካድሬዎች እየተሰደቡ…እየተንገላቱና መብታቸው እየተነፈጉ ነው የዋሉት፡፡ ዓረና ወረቀት ይዞ ህወሓት ብረት ታጥቆ!

ህወሓት በትግራይ ከዚህ በፊት በተለያዩ ድራማዎች የታጀበ የይምሰል ምርጫዎች ያደርግ ነበር…ዘንድሮ ግን እውነተኛ ምርጫ ይቅርና የይምሰል ምርጫውም ከነአካቴው ያስቀረው ይመስላል፡፡

ዓረና-መድረክ እጩ አድርጎ ያቀረባቸው ተወዳዳሪዎች የመወዳደርያ መታወቅያ ከተሰጣቸው በሁዋላ በህውሓት ውንብድና ታስረዋል…ከመሬታቸው ተነጥቀዋልም፡፡ ትግራይ ውስጥ ያለን የህዝብ ተቀባይነት ከመቼውም ጊዜ በላይ እየሰፋ ነው፡፡ በህዝባችን ሞራልና ሁለንተናዊ ድጋፍ በጣም ኮርተናል፡፡ ህወሓት ወደ ተራ ስድብና ወደ ከፍተኛ ድንጋጤ ገብቶ ህግ በጠራራ ፀሃይ እየጣስ ከኣንድ መንግስት የማጠይጠበቅ ተራ ውንብድና የሚሰራዉም ከዚህ የተነሳ እንደሆነ በደንብ እንገነዘባለን፡፡

በክልላችን ምንም ምርጫ ለማካሄድ የሚያስችል ዳኛም መጫወቻም የለም፡፡ ነባራዊ ሁኔታው ኣባላቶቻችን ከማስደንበርና ከማስፈራራት አልፈው በርካታ አስረውብናል፡፡ እኛ ሁሉ ችለን ዝምበለን ፅዋቸው እየተጎነጨን ነው…ለህዝባችን መስዋእት መክፈል እንዳለብን አምነንበት ስለተነሳንና ከዚህ በላይ የሚያስደስተን ነገር ስለሌለ ትግሉ መቼም አይቆምም…መጨረሻ ድሉ የኛ ነውና፡፡

ህወሓት ሰላማዊ ትግሉ ወደ ጦርነት አውድማ ቀይሮታል…ትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ ሁሉ ነገር በብረት የታጠረ ነው፡፡ የኛ አባላት ሃሳብና ወረቀት ብቻ ይዘው..ህወሓት ከነ ትጥቁ ነው ያለው፡፡ ይሄ ምርጫ ነው ወይስ ጦርነት? ስለሆነም ህወሓት በህግ ይገዛ …ያፀደቀውን ህግ ያክብር…ትጥቁም ይፍታልን፡፡

በአሰግድ ታመነ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.