ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በስውስዘርላንድ ዳቮስ የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በስውስዘርላንድ ዳቮስ የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ያደረጉት ንግግር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በስውስዘርላንድ ዳቮስ የአለም ኢኮኖሚ ፎረም ላይ ያደረጉት ንግግር

Posted by Solomon Gadissa on Wednesday, January 23, 2019


ዳቮስ
በየአመቱ በዚህ ወቅት ስለ አለም ኢኮኖሚ ሁኔታ ለመምከር በስዊዘርላንድ ዳቮስ ከተማ ስብሰባ ይደረጋል፡፡ ባለሃብቶች፤ የሀገር መሪዎች፣ የቢዝነስ መሪዎች፤ የአካዳሚክ ሰወች እና ታዋቂ ሰወች ይታደማሉ፡፡ ባብዛኛዉ የግሎባል ኢኮኖሚዉን ሁኔታ ለመመርመር እና ለፖሊሲ አቅጣጫ የሚሆኑ ሃሳቦችን ለማዋጣት ነዉ፡፡ በዘንድሮዉ ስብሰባ ዋና ዋና ተጫዋቾች የእነ አሜሪካ፤ ፈረንሳይ እና እንግሊዝ መሪወች አልተገኙም ( በዉስጥ ጉዳያቸዉ ምክንያት)፡፡

ዶ/ር አብይ በዚህ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እና ፖለቲካል ሁኔታ አቅርቧል፡፡ ይሄ መደመር የሚሉት ነገር አፍ እና ቂጡ አልያዝ ብሎን ከርሞ I think ለመጀመሪያ ጊዜ ይመስለኛል በትቂቱ በፖለቲካል ኢኮኖሚ terms ለማስረዳት ሞክሯል (vibrant democracy, economic vitality, and regional integration). እነዚህ ተርሞች በደንብ የሚታወቁ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን በጣም ጥቅል በመሆናቸዉ ወደ ዝርዝር የፖሊሲ እና ስትራቴጅ አቅጣጫ መዉረድ ወይም unpack መደረግ አለባቸዉ፡፡ ከዛም በተጨማሪ እነዚህ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ተርሞች በሊበራል ማህበረሰብ ዉስጥ የታወቁ ናቸዉ፡፡ የአብይ መደመር ፍልስፍና በዚህ ዉስጥ ምን አይነት የራሱ የሆነ unique perspective ወይም አዲስ ነገር ይዞ መጥቷል ሚለዉ እራሱ መታየት አለበት፡፡

ያደረገዉ ኢንተርቪዉም ጥሩ ነዉ፡፡ ቢያንስ የሚናገሩዉን ነገር የሚያዉቅ እና ሃገሪቱ ዉስጥ እየተካሄደ ያለዉን ነገር በደንብ ይገነዘባል፡፡ የሃይለማሪያም ችግሩ የነበረዉ ሀገሪቱ ዉስጥ የሚካሄዉን አለማወቅ እና የሚናገረዉንም ነገር ባግባቡ አለመረዳት ነበር፡፡ልምድ እያገኘ ሲሄድ ከዚህም በላይ articulate ማድረግ ይችላል፡፡ እንግዲህ ሀ ብሎ ፖሊሲ እና ኢኮኖመክስ መማር ነዉ፡፡ የሀገር መሪ ስትሆን በየምትሄድበት ሁሉ ከፖሊሲ፤ ከኢኮኖሚክስና ፖለቲክስ የተለየ ጥያቄ አይቀርብልህም፡፡ በነገራችን ላይ የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ጆ. ኬነዲ ፕሬዝደንት እንደሆነ ያደረገዉ ነገር ቢኖር ሁለት የሃርቫርድ የኢኮኖሚክስ አስተማሪወች ቀጥሮ ማታ ማታ ለ 3 ሰአት ያህል ቁጭ ብሎ ይማር ነበር፡፡ በኋላም አስተማሪወቹን የኢኮኖሚ አድቫይዘሩ አደረጋቸዉ፡፡

ከመለስ ዜናዊ በላይ ሰዉ የለም የሚል ካድሬ ተፈጥሮብን ሲያበሳጨን ኖሯል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ዶ/ር አብይን በመርህ ከመደገፍ እና ከመንቀፍ ይልቅ ጭፍን ድጋፍ የሚሰጥ ነፍ ካድሬ እየመጣ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ዶ/ር አብይ የዳቮሱን ስብሰባ አዲስ አበባ እንዲሆን አደረጉ ብለዉ ሲያጮሁት ነበር ትናንት ሙሉ ቀን፡፡ የአለም የኢኮኖሚ ፎረም ወደ አምስት አካባቢወች ላይ በአመት ስብሰባ ያካሂዳል፡፡ አንዱ የአፍሪካ ክፍል ነዉ፡፡ ይህ አዲስ አበባ እንዲካሄድ ዶ/ር አብይ ተስማምቷል፡፡ የዳቮሱን አዲስ ለማካሄድ ግን አይደለም፡፡

በዚህ ስብሰባ ላይ ያየሁት ትልቁ ችግር ይዞት የሄደዉ የሉእካን ቡድን ነዉ፡፡ ስብሰባዉ በዋነኛነት ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ላይ የሚያተኩር እንደመሆኑ መጠን የፖሊስ ኦፊሰር የነበረ ሰዉ (ወርቅነህ) ይዘህ አትሄድም፡፡ ይልቁን የማክሮ ኢኮኖሚ አማካሪወችን፤ የቢዝነስ ሰወችን እና የባንክ ሰወችን ነበር፡፡ በጠቅላላዉ ግን ስለሀገሪቱ አቅጣጫ የቀረበዉ ነገር ጥሩ ነበር፡፡

ሚክይ ዓምሃራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.