በረከት ስምኦን ከቤተሰብ ጋር ቁጭ ብሎ ሲወያይ

መንበረ ካሳየ

በረከት ስምኦን ከቤተሰብ ጋር እንዲህ ቁጭ ብሎ ያዩ አንድአንድ ወገኖቼ ይረብሻል ሲሉ አየሁ ። የተረበሹት የበረከት ልጆች አባታቸውን ሲጠይቁ በዚህ መልክ ማየታቸው ይመስለኛል ። የአባት ዕዳ ለልጅ ያለም ወንድሜ አለ ። እኔ ግን ጥያቄ አለኝ ። እነዚህ ፎቶዎች ምና ቸው ይረብሻል ? በርግጥ አብሬ ፖስት ያደረኩት ፎቶ አይደለም እኛን እራሱን በረከትን ሊረብሸው ይገባ ነበር ።

በነበረከት ዘመን የዐይኑ ቀለም ያላማራቸው ሁሉ ይታሰር ወይንም ከሀገር ይባረር ነበር ። ቤተሰብ ያልጠየቃቸውስ ስንቶቹ ነበሩ ? ሲፈልጋቸው ደግሞ ቤተሰብ ሊጠይቅ ሲመጣ እኛ ጋር የለም ብለው ይመልሳሉ ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለ11 ቀን ከ ኬተሰብ ተለይቶ ነበር ። ይህ የሆነው እብሪተኞች ተመስገን እዚህ የለም በማለታቸው ነው። ቤተሰብ እየተመላለሰ ቢጠይቅም እነሱ የለም በማለት ሲመልሱ ከርመዋል ። ቤተሰብ እንዳይገባ መከልከል እና ምግብ ማስመለስ አንድአንዴም እስከመድፋት ይደርሱ ነበር።

እስኪ በነበረከት መንግስት የታሰረውን ልጅ ተመልከቱት ። በካቴና የታሰረውን እጁን ሰርቃ ምታየውን ህፃን ታዳጊ ተመልከቱ ። ከጀርባው የቆሙት ሁለቱን ወጣቶች ተመልከቱ ። ከነሱ ፊት ብዙ ማንበብ ይቻላል ።

ዛሬ በረከት ታሰረ ። ቤተሰብ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ እወራው ነው ። አጠገቡ አንድም ፌደራል ፖሊስ ሲያንዣብብ ወይንም ሚያወሩትን ለመስማት ተጠግቶ ቆሞ አይታይም ። ቢታሰርም በነፃነት ከቤተሰቡ ጋር እያወራ ነው ። ምናልባት የተቀመጠበት ወንበር አልተመቸው ይሆናል ። ልጆቹ የያዙት መጽሀፍ ይታያችኋላ አይደል ? በነበረከት ዘመን የትኛው ታሳሪ ነው በታሰረ በንጋታው መጽሀፍ የገባለት ? የትኛው ታሳሪ ነው ሙሉ ቤተሰቡ የገባለት ?

እነ በረከት በወገኖቻችን ላይ የፈፀሙት ግፍ ሴጣን ያደርገዋል ተብሎ ከሚታሰብ የበለጠ በላይ ነው ። ሴጣንን ባላውቀውም የሰው ልጅ ላይ እንዲህ ዓይነት ግፍ ሌላ የሰው ፍጡር ይፈጽመዋል ብዬ ስለማላስብ ነው ። እነሱ ያንን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ ለልጆቻቸው ለቤተሰቦቻቸው አላሰቡም ። ያንን ሁሉ ግፍ ሲፈጽሙ ነገ በነሱ ላይ የሚደርስ አልመሰላቸውም ነበር ። ነገ እነሱ ታስረው የነሱ ልጆች ሊጠይቋቸው እንደሚመጡ አልታያቸውም ነበር ። እና ምን ለማለት ነው …… ይህን ፎቶ ማየት ምንም የሚረብሽ ነገር የለውም ።

1 COMMENT

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.