በድሬዳዋ እኩልነት በመጠየቅ ነዋሪዎች ተቃዉሞ አሰሙ

ከጥምቀት በዓል በኋላ ታቦት ሊገባ ሲል በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ድሬዳዋ ከተማ አሁንም መረጋጋት እንደማይታይባት ተዘገበ። በተለይም የኦሮሞና ሶማሌ ያልሆኑ ነዋሪዎች በከተማዋ መብታቸው ተነፍጎ እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንደሚታዩ ይታወቃል። በከተማዋ «40/40/20» የተባለው አፓርታይዳዊ ሲስተም፣ የከተማዋን ድርሻ ፣ ዘር በመለየት፣ አርባ በመቶ ለኦሮሞ፣ አርባ በመቶ ለሶማሌ በመስጠት ሌሎች ኢትዮጵያዉያን ሃያ በመቶ ብቻ ድርሻ እንዲኖራቸው በማድረግ በከተማ አስተዳደር በሌሎች ላይ ከፍተኛ የሆነ አድልዎ ይፍጸም እንደነበረ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

ታቦት ሲያስገቡ፣ በአንዳንድ አክራሪዎች ትንኩሳ የተነሳው ተቃዉሞ፣ በነዚህ ነዋሪዎች ላይ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት ሲደርስ የነበረው መድልዎና ብሶት ከመንገፈሉም የተሳ እንደሆነ የሚናገሩት ብዙዎች ናችው።

ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል በድሪዳዋ ጉዳይ የሚከተለውን አስፍሯል፡

——–

ሰኞ የእግዜርአብ ታቦት ገብቶ ሲመለስ ፖሊስ መሬት በሚባል አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የጀመረው የድሬዳዋ ውጥረት ዛሬም ቀጥሏል።

ደውለን ያነጋገርናቸው የድሬዳዋ ነዋሪዎች እንደነገሩን ከሆነ ዛሬም ከማለዳ ጀምሮ ወጣቶች ሰልፍ ሲያካሄዱ፣ የተቃሞው ድምጾችን ሲያሰሙ፣ አልፎ አልፎም ድንጋይ ሲወራወሩ ነበር።

የወጣቶች ጥያቄ እየሰፋ መጥቶ የሥራ አጥነት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትህና የእኩልነት ጥያቄዎች ጎልተው መውጣት ጀምረዋል። በተለይም የድሬዳዋን ፍቅር አታደፍርሱ፣ በብሔር አትከፋፍሉን፣ «40/40/20» የተሰኘው የአስተዳደር ቀመር ይውደም፣ የሚሉ ተቃውሞዎች ሲሰሙ ነበር።

ረፋድ ላይ ድሬዳዋ ራስ ሼል አካባቢ «ከንቲባው ይውረድ! ድምጻችን ይሰማ!» የሚሉ ድምጾችም ከፍ ብለው ይሰሙ ነበር። በዚያ ያልፉ የነበሩ ሦስት መቶ የሚገመቱ ወጣቶች ባንዲራዎችን ከመያዝ ውጭ ተቃውሟቸውን በሰላማዊ መንገድ ያቀርቡ እንደነበር አቶ ሰለሞን ኃይሌ የተባሉ የድሬዳዋ ነዋሪ ነግረውናል።

ትናንትናና ከትናንት በስቲያ ረቡዕ ባንኮች ተዘግተው መዋላቸውንና የከተማዋ እንቅስቃሴ በአመዛኙ ታውኮ እንደነበረም ሰምተናል። ተቃውሞው ሙሉ ከተማውን ያካለለ ባይሆንም ተቃውሞወቹ ዋና ዋና የንግድ እንቅስቃሴዎች በከፊል እንደተስተጓጎለም ነዋሪዎች ነግረውናል።

«ወጣቶቹ ሆ ብለው ሲመጡ ሱቆች ይዘጋሉ፣ በረድ ሲል ደግሞ መልሰው ይከፈታሉ ብለዋል» አቶ ሰለሞን ለቢቢሲ።

ዛሬ ከዚራ፣ በዋናነት ደግሞ «ጂቲዜድ» የሚባል ሰፈር፣ እንዲሁም ድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የሚገኝበት አካባቢ ፖሊስና ወጣቶች ተፋጠው ማርፈዳቸውን የዓይን እማኞች ነግረውናል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.