በአዲስ አበባ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆች በድሬዳው ያለው 40:40:20 ቀርቶ እኩልነት እንዲኖር ጠየቁ

አዲስ አበባ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆች በአዲስ አበባ በድሬዳዋ ያለው አርባ አርባ ሃያ የሚባለው ዘረኛ አስራር እንዲቀየርና ፍትህና እኩልነት በከተማዋ እንዲሰፍን ጠየቁ።

የድሬዳዋ ከተማ በፍቅር፣ በንግድ የምትታወቅ ከተማ ስትሆን፣ የኦሮሞ ና የሶማሌ ክል የይገባኛል ጥያቂ አንስተው ሲዘዛገቡባት የነበረች ከተማ ናት። ከባዶ ሜዳነት በአጤ ሚኒሊክ ተመስርታ ትልቅ ከተማ የሆንችው የድሬዳዋ ከተማ ለብዙ ጊዜ በፌዴራል ስር የነበረኝ ሲሆን፣ በኋላ በኦሮⶁ በሶማሌ ክልሎች በጋራ እንድትተዳደር በመደረጉ የክልሉን አስተዳደር አርባ በመቶ ሶማሌዎች፣ አርማ በመቶ ኦሮሞዎች ይዘው ሌላው ማህበረሰብ ግን ሃያ በመቶ ብቻ እንዲሰጠው በማድረግ ከተማዋ ከኦሮሞዎችን ከሶማሌዎች ውጭ ያሉ ሌሎች ማህበረሰባት ከፍተኛ አድልዎ እንዲፈጸምባቸው ያደረገ አሰራር ነው።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፡

“40:40:30 ይቁም፤ ድሬዳዋም እንደገና ታልቅ እናድርጋት”፣ “ፍትህ እኩልነት ለሁሉም ድሬዳዉያን”፣ “ድሬዳዋ የነዋሪዎቿ ናት”፣ “ፍቅራችንን እንጠብቅ“፣ “ድሬዳዊነት ለታላቂቷ ኢትዮጵያ መሰረት ነው”፣ ” ሰላም ለኢትዮጵያ፣ ሰላም ለዲሬዳዋ” እያሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

“ድሬዳዋ ለባለቤቷ ለፌዴራል መንግስት ትመለስ ” ያሉት በአዲስ አበባ የሚኖሩ የድሬዳዋ ልጆች የፌዴራል መንግስቱ የድሬዳዋን ጉዳይ ትኩረት ሰጥቶ ከተማ እንደ አዲስ አበባ በፌዴራል ስር እንድትሆን ጠይቀዋል።

3 COMMENTS

 1. The the administrative demands in Dere Dhawa are like that of the Welkait and have nothing to do with Apartheid.

  Ethiopia is a country which is always affected by the backward noises. Ever ignorant can claim overnight as a brilliant politician without understanding what is going in that part of the world.

  Most of those who open their filthy mouths today aren’t in a position to understand who brought the charges in that country. At the same time they don’t want to realize why the change was needed.

  Don’t dream unrealistic wishes! You cannot change certain natural things. For example,  you should have to accept the reality that Finfinne is an integral part of Oromia. No miracle will change this reality. All the residents of Finfinne have to even prepare themselves, in order to pay compensation for the uprooted Oromo from Finfinne in the last 140 years. 

  Oromia will be never abd ever divided. 

  You can keep on your stupidity which will produce nothing. Let me assure you for a record, your attempts will never bring back the inhuman eras of the uprooted and eradicated systems. They have gone for good and will not came back again. Ethiopia cannot go back to the old eras of “golden times”. Nobody can impose again it’s hagemoy more in Oromia. The integrity of Oromia including Finfinnee will be untouchable. The Oromo nation has been fighting injustice and subjugation in it’s  homeland, Oromia in order to regain it’s human dignity as one of the great nations of East Africa. This great nation will also protect it’s political gains. Just wait and watch out!  No more business as usual. Period!

  Anyone or a group of individuals who don’t want to respect the values, norms, culture and language of the Oromo nation can leave Oromia peacefully to a region of his or their choice. We will not entertain any more the offsprings of ex-neftengas those who are not grateful.

  All residents of Oromia will be treated equally. It doesn’t matter which ethnic background one may have. But all residents of Oromia must know their obligations and responsibilities. They must respect all the natural rights of great Oromoo nation unconditionally.

 2. This is nonsense and meaningless saying. Before you open your wide and empty mouth, try to open your closed mind. Try to learn and read, if you can learn and read , how this country is formed. Addis Ababa/shewa is never and ever to Oromo

 3. For the dummy BIZU,

  የፊንፊኔ ጉዳይ የኦሮሞ የአገር ባለቤትነት ጉዳይ ነው

  ብርሃኑ ሁንዴ, Onkoloolessa 5, 2018

  የፊንፊኔ ጉዳይ አብዛኛውን ጊዜ ሲነሳ ቢቆይም ባሁኑ ጊዜ ግን ልዩ ትኩረት ያገኘ ይመስላል። ይህንን ጉዳይ በሚመለከት የተለያዩ ውዥንብሮችም እየተፈጠሩ ናቸው። በተለይም ደግሞ የኦሮሞን ነፃነትና የአገር ባለቤትነትን የማይቀበሉ ኃይሎች በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ የሚችሉትን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠው የተነሱ ይመስላሉ። እነዚህ ኃይሎች ኦሮሞ በፊንፊኔ ላይ ያለውን የአገር ባለቤትነትን የሚቃወሙበት በተለያየ መንገድ ቢገለፅም፣ ዋና ዋና የሆኑትን ምክንያቶች እንደ ምሳሌ ለመግለፅ፥

  እያወቁ ግን የፊንፊኔን ታሪክ ለመደበቅ ብለው ይህቺ ከተማ የአማራ እንደሆነች አድርገው ለመግለፅ ይሞክራሉ። ይህን የሚያደርጉበት ምክንያት ደግሞ እውነት ስላላቸው ሳይሆን አፄ ሚኒሊክ በኦሮም ላይ የፈፀመውን ጥፋት ላለመቀበል ነው። ምክንያቱም ፊንፊኔ ከዚያ ታሪክ ጋር የተያያዘች በመሆኗ ነው።ፊንፊኔ ወደ እናቷ ኦሮሚያ ከተመለሰች ልክ በዚህች ከተማ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች ተገፍተው እንደሚወጡ በማየት ነው። የኦሮሞ ሕዝብ የትኛውንም ብሔርና ብሔረ ሰብ እንደማይነካና እንደማይጎዳ፤ ባዕድን እንኳን ወደ ራሱ አስጠግቶ እንደሚያኖር፤ ሰላም ወዳድ ሕዝብ መሆኑን እያወቁ ግን ካላቸው ጥርጣሬና ፍርሃት የመነጨ በመሆኑ የፊንፊኔን ጉዳይ በሌላ መንገድ ይተረጉማሉ።ፊንፊኔ የስልጣንና የትግል ማዕከል በመሆኗ፣ ሁሉም ፊንፊኔን የፖለቲካና የኢኮኖሚ የእስትራቴጂ ቁልፍ ቦታ እንደሆነች አድርገው ያያሉ። የኦሮሞን የአገር ባለቤትነትን የሚቃወሙት ኃይሎች ፊንፊኔን ማጣት ማለት ኢትዮጵያን እንደ ማጣት አድርገው ስለሚያዩትና ስለምያምኑት፣ ፊንፊኔ በጭራሽ ኦሮሚያ ስር እንዳትገባ መራራ ትግል ማድረግ ይፈልጋሉ።

  የፊንፊኔን ጉዳይ ለመቃወም የፈለጉትን ምክንያት ቢያቀርቡም፣ ቢወደደም ቢጠላም፣ ቢታመንም ባይታመንም፣ ለኦሮሞ ግን የፊንፊኔ ጉዳይ የአገር ባለበትነት ጉዳይ ነው። የኦሮሞ የነፃነት ትግል ዋና ዓላማው የኦሮሞን የአገር ባለቤትነትን ማራጋገጥ በመሆኑ፣ የኦሮሚያ እምብርት የሆነችውን ፊንፊኔን መተው አይችልም። በመሆኑም በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ በኦሮሞ በኩል ኣንዳችም ቅድመ ሁኔታ መወሰድ የለበትም። ፊንፊኔ በታሪክም ሆነ በሕግ በኩል ሲታይ የኦሮሚያ አካል ናት። ኦሮሚያ እምብርቷን ከውስጧ አውጥታ መኖር አትችልም። በመሆኑም ፊንፊኔ ወደ እናቷ መመለስ የግድ ይሆናል።

  እኔ እንደማስበውና እንደማምንው፣ ኦሮሚያ ከፊንፊኔ የምታገኘው ልይ ጥቅም ተብሎ መቀመጡ ራሱ ስህተት ነበር። ኣበት ከልጁ ወይም እናት ከልጇ የሚያገኘው ወይም የምታገኘው ልዩ ጥቅም ምንድነው?? ኦሮሞ ከፊንፊኔ ያለው የአገር ባለቤትነት እንጂ ልዩ ጥቅም የሚባል ነገር የለም ወደፊትም አይኖርም። ልዩ ጥቅም ማግኘት ያለባቸው በከተማይቷ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑ ሰዎች ናቸው። ይህም ማለት እነዚህ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ መብታቸው መከበር የግድ ይሆናል ማለት ነው። ነዋሪዎቹ ልዩ ጥቅም ማግኘት የሚችሉት ደግሞ በመጀመሪያ ፊንፊኔ ወደ ኦሮሚያ መመለስና ከዚያ በኋላ በከተማዋ አስተዳደር ወስጥ ኦሮሞ ያልሆኑት ነዋሪዎች እንደ ቁጥራቸው ውክልና ማግኘት መቻል ማለት ነው።

  በስተመጨረሻ የትኛውም ኃይል ቢፍጨረጨርም፣ ቢፈራገጥም፣ ቢፎክርም፣ ቢሸልልም፣ የፈለገውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጦ ቢነሳም፣ ነፃነትና የአገር ባለቤትነት በነፃ ስለማይገኙ፣ ኦሮሞ ኣንድ ሆኖ፣ ኣንድነቱንና ኃይሉን አጠናክሮ፤ አስፈላጊ በሆነ መንገድ ሁሉ ራሱን አዘጋጅቶ ይህ የፊንፊኔ ጉዳይ የመጨረሻ መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ አለበት እንጂ ወዲያና ወዲህ ማለት፤ ሊደረግብን የሚችለውን ቅደመ ሁኔታ መቀበል ጭራሽ የማይታሰብ ነው። ኦሮሞ ስልጣን አግኝቶ ይህችን አገር እያስተዳደረ ነው በሚባልበት ወቅት በፊንፊኔ ጉዳይ ላይ ድክመት ማሳየት ወደ ሌላ ጥፋት ሊወስደን ይችላል። እየመጣብን ያለውን አደጋ ከሩቁ ማየት መቻል አስፈላጊና ወሳኝም ነው። ኦሮሞ ከፊንፊኔ የሚፈልገው ልዩጥቅም ሳይሆን ሙሉ በሙሉ የአገር ባለቤትነትን ነው።ይህ የኦሮሞ ተፈጥሮኣዊና ታሪካዊ መብቱ ነው። ይህ እውነታ ለጠላትም ለዘመድም ግልፅ መሆን ኣለበት።

  ተመልሰን እስከምንገናኝ ደህና ሁኑ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.