አስረዝመው ቢያስሯት የለቀቋት መሰላት ለፖለቲካው ሳሙኤል ዘሚካኤል ጃዋር (ሰርፀ ደስታ)

ጀዋር መሀመድ የወያኔ ቅጥር እንደሆነ ደጋግመን ተናግረናል፡፡ ለወያኔ ትልልቅ ውለታ ውሏል፡፡ አሁንም ወያኔን ለማዳን ብዙ ሞክሯል፡፡  ይሄ ለተራ ሰው ላይገባው ይችላል፡፡ ጀዋር የኦሮሞን ሕዝብ ለወያኔ እየገበረና እያስገበር ኑሮውን የመሰረተ ሰው ነው፡፡ ቆይቶ ሁሉም ነገር ግልጽ ሲወጣ ታዩታላችሁ፡፡ ብዙዎች የወያኔ ተቃዋሚ የሚመስሉ አይነተኛ ባለውለታ ናቸው፡፡ ከስንት አመት በኋላ ብቅ ብሎ ወያኔ መንገዳገድ ስትጀምር ኦሮሞን ሁሉ በአብይ መንግስት ላይ ጦር ያነሳው ሸኔ ኦነግ ማንም ከወያኔ ጋር እንደሚሰራ አልጠረጠረም አንኳን፡፡ አሁን ራሱ ይሄን ሁሉ አይተን ብዙዎች አልገባቸውም፡፡ የጀዋር ቡድን ሌላው ኦሮሞን ለማስገበር የተደራጀ ሴል ነው፡፡ ሸኔ ኦነግና እንጀዋር የተለያየ ቡድን ናቸው ቀደም ብሎ ምን ያህል ግንኙነት እንዳላቸው አላውቅም፡፡ ከተገኛኙም ሊገናኙ የሚችሉት በወያኔ በኩል ይመስለኛል፡፡ የሆነው ሁሉ ሆኗል፡፡ ይህ ሚስጢር መውጣቱ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ አሁን የቲም ለማቡድን ስልጣን ላይ ሲመጣ እነ ጀዋር አብድ ነበር የሆኑት፡፡ አሁንም የሚያደርጉትን አጥተው ነው እንጂ ብዙ እየሞከሩ ነው፡፡ ለዛም ነው ኦሮሞን ዳግም ለወያኔ ባርነት ለመመለስ ብዙ ሞክረው ሰሞኑን ኦሮሞ ስለነቃ እርቅ ምናምን በሚል አሁንም ዋና ሆነው የተገኙት፡፡ አዝናለሁ የጀዋርና ቡድኑ ኑሮ የተመሠረተው በኦሮሞ ሕዝብ እልቂት ላይ ብቻ ሳይሆን አሁን አገር ብትረጋጋ ሚስጢራቸው እንደሚወጣ ስለተረዱ ነው ዛሬ የሞት ሽረት ያህል የሚኒፈራገጡት፡፡ እስኪ ቢያንስ ጌታቸው አሰፋ ይያዝና ቀጥሎ የሚሆነውን እናያለን፡፡

ጀዋር ቄሮን ለወያኔ ጥሩ ግብአት በሚሆን መልኩና አገርን ለመበታተን ዓላማ አድርጎ ነበር ሲጠቀምበት የነበረው፡፡ ለማ ቀደመው እንጂ፡፡ ቄሮ ለማን ማመስግን ብቻ ሳይሆን እንደ አባት ሊያየው በተገባ፡፡ ቄሮን ከብዙ እልቂትና እስከወዲያኛው የባዘነ ሊያደርገው ከወያኔ ጋር ጥምር ከሚሰራው ጀዋርና ቡድኑ ነበር ለማ አትረፎ ኢትዮጵያዊነት ውስጥ የጨመረው፡፡ ይህ እውነት ነው!!! አንዱንም የሆነውን ሂደት አንረሳም፡፡ ዛሬ አያስታውሱትም በሚል ነው የእነጀዋር እንቅስቃሴ፡፡ ለዛም ነው በየቀኑ እየተጣጠፈ የሚኖረው፡፡ በእነ ለማ ላይ ከፍቶት የነበረውን ዘመቻ እንዲሁ ተድበስብሶ አልፎለታል፡፡ አሁንም እላለሁ ኦሮሞም ሆነ ሌላው አስተውሎ ይጓዝ፡፡ ብርሀነመስቀል አበበ ሰኚ የሆነ ወቅት ግር ያለው በሚስልም አገር ቤት ገብቶ ሁኔታዎችን ከተመለከተ በኋላ የእነ ጀዋርን ሴራ በግንባር ቀደምነት እንዳመከነው አይተናል፡፡ ዳግም ኦሮሞን ለወያኔ መሳሪያ ሊያደርጉት አሰፍስፈው ነበር፡፡ አሁንም አልተኙም፡፡

ሰሞኑን ደግሞ አላሙዲን እንዴት ይፈታሉ መታሰር አለባቸው የሚል ዘመቻ ጀምሯል፡፡ ጀዋር ሆይ የአንተ ጸሐይ እየጠለቀች ነው፡፡ በእነ ሙክታር ጊዜ ስታደርግ እንደነበረው ያለ መንግስት ዛሬ የለም፡፡ የእነ አብይ ወደ ስልጣን መምጣት አብድ ያደረገህን ምክነያት እናውቀዋለን፡፡ አላሙዲንን አንታና ቡድንህ አደሉም የሚፈልጓቸው፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን እንፈልጋቸዋለን፡፡ ለወያኔ ቀኝ እጅ ግራ እጅ ነበሩ በሚል ተራ ዲስኩር ነገሮችን ልታሸበርቅ ትሞክራለህ፡፡ አላሙዲንን ከዚህ በኋላ ታያቸዋለህ፡፡ ምን አልባትም ላታይ ትችል ይሆናል፡፡ ቂሊንጦ ወይም አሜሪካ ከርቸሌ ካልገባህ ነው፡፡ ከጀርባህ ያለው ሲጣራ ይሄው እንዳይሆንብህ ነው እንድህ እብድ የሆንከው፡፡ ግን ተንቀዥቀዠሀልና የሚቀርልህ አልመሰለኝም፡፡ የሆነ ሆኖ የወያኔ “ቀኝ” የሆኑት አላሙዲን  በግልጽ በምናውቀው ደጋፊነታቸው ነበር፡፡ ብዙዎች ደጋፊ የነበሩ ዛሬ ለድርጊታቸው ሳይቀር ተጸጽተው ይቅርታ ጠይቀውናል፡፡ አላሙዲን ለወያኔ መራሹ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ ኢንቨስትመንት በማካሄዳቸው የፖለቲካ ግብዓት ሆነው እንጂ እንደ እውነቱ ለሕዝብ የሚበጁ ብዙ ሥራ ሰርተዋል፡፡ ከዛም በላይ ሊሰሩ ሞክረው አልተሳኩላቸውም፡፡ ያም የሆነው በወያኔ ሴራ ነበር፡፡ አላሙዲን ከ97ቱ ምርጫ በኋላ ምን ያህል ከወያኔ ጋር እንደሚቀራረቡ አናውቅም፡፡ ግን ዝምድናቸው እንደቀዘቀዘ ታዝበናል፡፡ አላሙዲን ሶስት ሜጋ ፕሮጄክት አንድ የምግብ ዘይት፣ አንድ የብረታ ብረት እንደ ደግሞ ሌላ የረሳሁት ወሳኝ ፋብሪካዎችን አስበው ፋብሪካዎቹ የወያኔ ወሮበላውን ኮንትሮባንድ ያስቀራሉ በሚል መሰለኝ እንዳይሰሩ ተደርገዋል፡፡ ከዛም በላይ ፋብሪካዎቹ ታስበው የነበሩት ወያኔ ከሚጠላው የአማራ ክልልና ኦሮሚያ ውስጥ መሰለኝ፡፡

የለገደንቢን ወርቅ አስመልክቶ በአላሙዲን ላይ ጣት መቀሰር ሌላው አደገኛ የሆነ ሴራ ነው፡፡ ምንም አይነት ችግርን ማላከክ ልምዳችሁ ነው፡፡ ለገደንቢ ትልቅ የአገር ገቢ የሚያስገኝ ፕሮጄክት ነው፡፡ ዜጎጅን ደህንነት ማስጠበቅ የመንግስት ኃላፊነት ነበር፡፡ ፕሮጄክቱ ማምረትና ግብር መክፈል በእርግጥም ደረጃውን የጠበቀ የሰራተኞቹን ደህንነት መጠበቅ አለበት፡፡ ሕዝብ ላይ ጎዳት ካደረሰም መንግስት ሊያስቆመው ይችላል፡፡ ሆኖም ሕዝብን አስፈላጊወን ነገር ማሟላት የባለሀብት ሥራ አደለም፡፡ ባለሐብት ሊለግስ ይችላል፡፡ መንግስት ከዚህ ልማት ከሚያገኘው ቀንሶ ለአካባቢው ሰዎች ማፍሰስ ስራው ነው፡፡ በፕሮጄክቱ ደረሰ የተባለው ጉዳት ሁሉ ደርሶ ከሆነም ፕሮጄክቱ አደልም ተጠያቂው፡፡ ፕሮጄክቱ እኮ ከፍተኛ ግብር ከዛም ባላይ የውጭ ምንዛሬ ለመንግስት እያስገባ ነው፡፡ የጤናና ትምርት ተቋም መስራት የመንግስት ድርሻ ነው፡፡ እንደውም ባለሀብቱ ልስራ እንኳን ቢል መንግስት በልዩ ሁኔታ ከአልሆነ መፍቀድ የለበትም፡፡ ይሄ አይነት የወሮበላ አሰራር እኮ ነው ችግር የፈጠረው፡፡

ለማንኛውም አላሙዲንን እኛ እንፈልጋቸዋልን! ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያን መንግስትና ሕዝብ ያገለግላሉ፡፡ የሰቡትንም ሜጋ ፕሮጄክቶች ዛሬ በአሰቡበት ቦታ ይሰራሉ፡፡ ስህተታቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ሳይሆን ወያኔን መተማምናቸው ነበር፡፡ ያን ቀደም ብሎ ገብቷቸዋል፡፡ ከሱማሌ ለተፈናቀሉ ዜጎቻችን የለገሱትን ሕዝብ አዳም ተጠራቅሞ ሊለግስ እንዳልቻለ እናስታውሳለን፡፡ ወያኔን ገሸሽ አድርገው ለማ ቢሮው ድረስ ሄደው ሲለግሱ በአይናችን አይተናል፡፡ ወያኔ አላሙዲንን መቆጣጠር አልቻለችም ገንዘብ ለማሰባሰብ ቴሌን ግን መከልከል ችላለች፡፡ ጀዋር መሀመድ አላሙዲን በየትኛውም መልኩ ኢትዮጵያን በብዙ ነገር ጠቀሙ እንጂ አልጎዱም፡፡ በሕዝብ ደም ላይ እየቆመርክ ለወያኔ እያገለገልክ ያለህውን አንትን ቀኑ ሲደርስ የሚቀርልህ አልመሰለኝም፡፡ የእስከዛሬው ሳያንስህ አሁንም ተንቀዥቀቅዠሀል፡፡ ወያኔ ከመውደቋ በፊት ከሰራህው ከዛ በኋላ የሰራህው በራሱ የት እየወሰደህ እንደሆነ የጠገለጠልህ አይመስለኝም፡፡ በርታ በደንብ ሴራህን አብራራው፡፡ ሚስጢርህ የሚወጣበትን ጊዜ እያፋጠንክ ነው፡፡ ዛሬ አብይና ለማ እንጂ ሙክታር ወይም ጁኔዲን አደሉም ሥልጣን ላይ ያሉት፡፡ ይቺ በዘመቻ አኖሌን በገንባት እንደቻልክበት ጊዜ አደለም፡፡ አሁን ቀጥሮ እያሰሩህ ያሉትን እነ ጌታቸው አሰፋን እየደኑ ያሉ ሰዎች ናቸው ሥልጣኑን የያዙት፡፡ አስረዝመው ቢያስሯት የለቀቋት መሰላት አሉ፡፡ ሴራህን ያውቁታል ግን ብዙ ሕዝብ በወያኔ ድጋፍ ለማጭበርበር ስለቻልክ ሕዝቡ እሰከሚገባው ነው፡፡ በፍጥነት እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ወዴት እንደምትሄድ ብትፈራውም የሚቀርልህ አልመሰለኝም፡፡ ተንቀዝቅዠሀል፡፡ ያዳቆነ … አደል የሚባለው፡፡ እውቀትም ምንም እንደሌለህ እናውቃለን በወያኔ ነው እዚህ የደረስከው፡፡ ሳሙኤል ዘሚካኤል በራሱ ነበር ብዙ ሕዝ የሸወደው አንተ ግን በወያኔ ልዩ ድጋፍ ነው፡፡ ቀን እየጨለመብህ እንደሆነ ይሰማኛል! ተረጋጋ!

ልኡል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ!

አሜን! 

3 COMMENTS

  1. ምኞታችሁማ ብዙ ብዙ ነው::ግን እንደተቃጠልክ ኦሮሞ ነጻነቱን የበለጠ ተጎናጽፍ ሀገሩን ገንብቶ ከጭቁን ህዝቦች ጋር በሠላም ይኖራል::ጀዋርን ደግሞ ጠ/ሚኒስቴር አድርጎ ይመርጣል::እናንተ ውሽታሞችና ምቀኞች ተጠራሪጋችሁ ገደል ግቡ::
    You don’t have any mandate to talk either about Jawar or Oromo.You idiot

  2. ፅሁፉን አላነበብኩትም:: ያሳቀኝ ግን አበራ ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ሹመት ነው ነገር ነው:: ታስቃለህ:: ጀዋር :ጫታም :የወያኔ ካድሬ :እበላ ባይ አወናባጅ ነው:: እኔ የማይገባኝ ” ኦሮሞ ” ከምንድነው ነፃ የሚወጣው? እንዲህ እያላችሁ ምስኪኑን ህዝብ እያስጨረሳችሁት ነው:: ሌላውን ሰላማዊ ህዝብም እያተራመሳችሁት ነው በእናንተው ጦስ:: ገና መቶ አመት ስለ ኦሮሞ ነፃነት ስናወራ ልንኖር ነው:: ያልታደልን!!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.