በሳይበር ጥቃት በየአመቱ ከ85 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉዳት ይደርሳል

በሳይበር ጥቃት በየአመቱ ከ85 ቢሊዮን ዶላር በላይ ጉዳት እንደሚደርስ የሳይበር አደጋ መከላከል ሪፖርት አመለከተ፡፡

የሳይበር ጥቃቱ በዋናነት የህክምና ተቋማትን፣ አምራች ኩባንያዎችንና ባንኮችን መሰረት ያደረገ ነው ሲል ሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

ከተጠቀሱት ተቋማት ባሻገርም የባለስልጣናትን፣ የባለሃብቶችንና የግለሰቦችን መረጃ በመያዝ ገንዘብ የሚጠይቁ የሳይበር ጥቃት ፈጻሚዎች ዋነኛ ስጋት መሆናቸውም ተጠቅሷል፡፡

በተለይ አሜሪካ እና አውሮፓ በከፍተኛ ደረጃ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ሪፖርቱ ገልጿል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.