15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 15ኛው የኢትዮ-ጅቡቲ የሚኒስትሮች የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ መካሄድ ጀመረ፡፡

በስብሰባው መክፈቻ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ባደረጉት ንግግር የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት እጅግ ጠንካራ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በቋንቋ፣ በባህል እና በኢኮኖሚ የተሳሰሩ በመሆናቸው ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በአንድንድ አካላት ”ሁለት አገራት አንድ ህዝብ” በማለት የሚገልፅበት መንገድ እንደሚያስስማቸው ነው የተናገሩት፡፡

የኢትየጵያ እና ጅቡቲ ፈርጀ ብዙ ግንኙነት በቀጠናው እንደሚመጣ ለሚፈለገው የኢኮኖሚ ትብብር መሰረት መሆኑንም አስታውቀዋል።

ሚኒስትሩ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ጌሌ በቀጠናው ብሎም በአፍሪካ እየተጫወቱት ያለውን ሚና አድንቀዋል።

የጅቡቲው ውጭ ጉዳይእና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ማህሙድ የሱፍ በበኩላቸው ሁለቱ ሀገራት አሁን ላይ ካለው ይበልጥ በመካከላቸው ያለውን የምጣኔ ሀብት ትስስር ለማጠናከር ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ሁለቱ ሀገራት ባለፉት ዓመታት በመሰረተ ልማት ለመተሳሰር ከ15 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወጭ ማድረጋቸው ይታወሳክል፡፡

ኢትዮጵያና ጅቡቲ ዘርፈ ብዙ የሁለትዮሽ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፥ የጅቡቲ ወደብ ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ለኢትዮጵያ ዋነኛ የወጪና የገቢ ንግድ መስመር ሆኖ ማገልገሉ ግንኙነቱ ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው የራሱን ድርሻ አበርክቷል።

ሁለቱ ሀገራት በመሰረተ ልማት የተሳሰሩ ከመሆናቸውም በላይ የጋራ ኮሚሽን አቋቁመው ግንኙነታቸውን በየጊዜው እየገመገሙ ይገኛሉ ።

የጋራ ኮሚሽን መቋቋሙ በትብብር ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በፍጥነት ለመፍታት ያስቻለ መሆኑ ነው የተገለፀው።

በአሁኑ የጋራ ኮሚሽን ስብሰባ ወቅት በዋነኛነት በትራንስፖርት፣ በወደብ፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በጉምሩክና በንግድ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ውይይት የሚደረግ መሆኑ ተጠቁሟል።

ከዚህ ባለፈም የጋራ ኮሚሽኑ በእነዚህ ዘርፎች የሁለቱ አገሮች የትብብር ግንኙነት እንዲጠናከር በመምከር ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን 
ያስቀምጣል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑንከውጭ ጉዳይ ሚኒሲቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በስላባት ማናየ/EBC

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.