ስለ ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት አመስራረትና የትግል ጎዳና ማብራሪያ

 1. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተሰኘ የሲቪክ ድርጅት ለምን እንደተመሰረተ ያውቃሉ? ካላወቁ እናስተዋውቅዎ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ከመስከረም ፳፮ እስከ ፳፯ ቀን ፪ሺህ፭ ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለሁለት ቀናት በተደረገ መሥራች ጉባዔ የተመሠረተ የሲቪክ ድርጅት ነው።

የድርጅቱ መሥራች ጉባዔ ተሣታፊዎች ፺፫(ዘጠና ሦሥት) ናቸው። መሥራቾቹ በሁለት ቀን ጉባኤያቸው የድርጅቱን መርኃግብር እና የመተዳደሪያ ደንብ አፅድቀዋል። የድርጅቱን መርኃግብር በግንባር ቀደምትነት የሚያስፈፅሙ ፴፪(ሠላሣ ሁለት) አባላት ያሉት ማዕከላዊ ምክር ቤት፣ አምሥት አባላትን የሚያካትት የቁጥጥርና ፍተሻ ኮሚቴ፣ እንዲሁም ከማዕከላዊ ምክር ቤቱ አባላት መካከል በተመረጡ አሥር ሰዎች የሚንቀሳቀስ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አዋቅረዋል። የጠቅላላ ጉባኤው አባሎች ድርጅቱ በሁለት ዓመት ሊያከናውናቸው የሚገባቸውን የሥራ መርኃ-ግብር አጽድቀዋል።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከምሥረታው ወቅት አንስቶ በአከናወነው ዓላማውን የማስፋፋት ተግባር፣ የዐማራው ነገድ ተወላጆች በሚኖሩባቸው ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ አገሮች እና ከተሞች አባላትን መልምሎና አደራጅቶ፣ መዋቅሩን በሥፋት እየዘረጋ ይገኛል። በዚህም መሠረት፦ በአውስትራሊያ፣ በአውሮፓ እና በካናዳ ከከተማ እስከ አኅጉራዊ-አቀፍ ቅርንጫፍ ኮሚቴዎችን አዋቅሯል። በዩ.ኤስ አሜሪካ በ፲፪ ከተማ-አቀፍ ቅርንጫፎች አባላቱን አደራጅቷል። ለወደፊቱም አብዛኛው የነገዱ ተወላጆች በድርጅቱ ዓላማ ጥላ ሥር እስኪሰባሰቡ ድረስ የማደራጀት ተግባሩን ይቀጥላል።

ሞረሽ ወገኔ ዐማራው ፍፁም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሕዝብ እንደሆነ ያምናል፣ የመደራጀቱም ምክንያት ኢትዮጵያ ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እና በተባባሪዎቻቸው ድርጊቶች ምክንያት «ባለቤት አልባ» አገር በመሆኗ ወደ ፈፅሞ መጥፋት ጫፍ በመገፋቷ ነው። ስለሆነም ሞረሽ ወገኔ የተመሠረተው ይህ አገር የሚያጠፋ ድርጊት ባስቆጫቸው ኢትዮጵያውያን ዐማሮች መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። እኒህ ከዐማራው አብራክ የፈለቁ ኢትዮጵያውያን፣ በተከታታይ ዘመናት በወገናቸው ላይ የደረሰውን እና በመድረስ ላይ ያለውን ሠቆቃ እና በደል ስለተገነዘቡ ይህንን ለወገን ጥሪ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት የተዘጋጀ ድርጅት መሥርተዋል። ድርጅቱ ማንኛውንም ዓይነት የፖለቲካ አመለካከት፣ የኃይማኖት ተከታይነት፣ ፆታ እና ዕድሜ ሣይለይ ለሁሉም የዐማራው ነገድ ተወላጆች ኅልውና የቆመ፣ እንዲሁም ለዐማራው ነገድ ድምፅ እና መከታ ለመሆን የሚንቀሳቀስ ነው።

 • ሞረሽ ማለት ምን ማለት ነው?

ሞረሽ ማለት የአደጋ ጊዜ የድረሱልኝ (የድረሱልን) መጥሪያ ቃል ወይም የስም ምትክ ነው። ቃሉ ሥራ ላይ የሚውለው፦

አንደኛ፡- አንድ የቤተሰብ አባል ወደ አንድ የታወቀ ቦታ ተልኮ መመለስ በሚገባው ሰዓት ሳይመለስ ቀርቶ ፀሐይ ብርሃኗን ስትነሳ፣ ቤተሰቡ መመለስበሚገባው ሰዓት ያልተመለሰውን ሰው ሁኔታ ለማወቅ፣ ይመጣበታል ተብሎ በሚገመተው አቅጣጫ ከፍ ካለ ቦታ ላይ በመሆን «ሞረሽ» እያሉ ይጣራሉ። በስሙ ቢጠሩት፣ አንድም ጠላት ብቻውን መሆኑን አውቆ ያጠቃዋል ከሚል ሥጋት፣ ሁለትም ስሙ ሲጠራ ስሙን ተከትሎ ርኩስ መንፈስ (ሠይጣን) ይወጋዋል ተብሎ ስለሚታመን፣ በደፈናው «ሞረሽ» ተብሎ ይጠራል። እንግዲህ «ሞረሽ» የጠፋን ወይም በወቅቱ ሳይመጣ የቀረን ሰው «ምን አገኝቶት ይሆን?» በማለት የሚደረግ የጥሪ ቃል ነው፡፡

ሁለተኛ፦ የሞረሽ ጥሪ ተግባራዊ የሚሆነው አንድን አካባቢ የሚያጠቃ ጠላት በድንገት ወይም በታወቀ ምክንያት ሲነሣ፣ የጥቃቱ የመጀመሪያ ሠለባየሆነው ወገን፣ ወገኖቹ እንዲደርሱለትና እራሱንና መላውን የአካባቢው ሰው ከጥፋት ማዳን እንዲቻል የድረሱልን፣ የተጠቃን፣ የተጎዳን የመከራ ጥሪ

ወይም ደወል ነው።

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅትም ይህን መጠሪያ የመረጠው ባለፉት ፷(ስድሣ) እና ፸(ሰባ) ዓመታት፣ በተለይም ባለፉት ፵(አርባ) ዓመታት፣ የዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ አገዛዝ ዐማራውን፦ በነፍጠኝነት፣ በትምክህተኛነት፣ በገዥ መደብነት እና ጨቋኝ ብሔርተኛነት ፈርጆ፤ የኢትዮጵያ አውራ ጠላት አድርጎ መጠነ ሠፊ የሆነ፣ ግድያ፣ እስራት፣ ድብደባ፣ ከሥራ ማባረር፣ ማሰደድ እና ቤት ንብረት ቀምቶ ከተለያዩ አካባቢዎች የማፈናቀል ወንጀል የፈጸመበት በመሆኑ ነው። ይህን የተቀነባበረ የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ተግባር ፈጽሞ ለማስቆም በተናጠል በሚደረግ እርምጃ የማይቻል ብቻ ሳይሆን፣ ጥፋቱ ያነጣጠረው በሁሉም የነገዱ አባላት ላይ በመሆኑ፣ ነገዱ ተባብሮ ጥቃቱን መቋቋም እንዲችል የቀረበ የድረሱልን ጥሪ ነው። ሞረሽ የሚለው መጠሪያ ስሙ በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰው ጥቃትና ጥቃቱን ለመቋቋም የመላውን ነገድ ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ብቻ ሳይሆን፣ የዐማራው የአደጋ ጊዜ መሰባሰቢያ መጠራሪያ በመሆኑ ባህላዊና ታሪካዊ ትርጉም የያዘ ስለሆነ ተመራጭ ሆኗል።

 • ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለምን ተመሠረተ?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተመሠረተው፦

፩ኛበዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለዘመናት ከኖሩበት ከደቡብ፣ ከምሥራቅ፣ ከምዕራብ፣ ከደቡብ ምዕራብ እናከመሐል ኢትዮጵያ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዐማሮች አቅም በፈቀደ መጠን ከዕለት ደራሽ እስከ ዘለቄታዊ ማቋቋሚያ የሚደርስ ዕርዳታ ማሰባሰብና ለተጎጂዎቹ ለማድረስ፤

፪ኛበዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በአውራ ጠላትነት ተፈርጆ የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው የዐማራ ነገድ ድምፅለመሆን፤

፫ኛኢትዮጵያውያን ዐማሮች ዐማሮች በመሆናቸው ብቻ፣ የሚደርስባቸውን እና የደረሰባቸውን የዘር ማጥፋት፣ የኢኮኖሚ ኅልውና ነጠቃ፣ የመብትገፈፋ እና የሰብአዊ መብቶች ረገጣ ለዓለም ኅብረተሰብ ለማሰማት፤

፬ኛየዐማራው ነገድ ተወላጆች በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ ሕይወት እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተገቢ ቦታቸውን እንዲይዙሁለንተናዊ አቅማቸውን ለማጎልበት ናቸው።

 • ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እንዴት ተመሠረተ?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የተመሠረተው፣ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ከየካቲት እስከ መጋቢት ፪ሺህ፬ ዓ.ም. በደቡብ ብሔር/ብሔረሰቦች ክልል በሚባለው፣ በማጂ ዞን፣ በጉራ ፈርዳ ወረዳ ለረዥም ዘመናት ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን፣ «አገራችሁ አይደለም» ብሎ በዘራቸው ብቻ ከሌሎች ነገዶች ነጥሎ፣ ቁጥራቸው ከ፳፪ሺ(22 000) በላይ የሆኑትን በአንድ ጊዜ ቤት ንብረታቸውን ነጥቆ በማባረሩ እና ከዚሁ ዞን ሌሎችን ፸፰ሺ(78 000) ያህሉን እንደሚያባርር በዓለም የብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች በመደመጡ ነበር። ቀደም ሲልም «ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና አፋር» ከሚባሉት ክልሎች ዐማራ የሆኑት

እየተመረጡ ተባርረዋል። እንዲያውም «የዐማራ ክልል» ተብሎ ከተከለለውም ጭምር በልዩ ልዩ ምክንያቶች ዐማራው ሲፈናቀል ኖሯል። ስለዚህ ዐማራው ከመላው ኢትዮጵያ የሚባረር መሆኑን በውጭ አገሮች የሚኖሩት የዐማራው ነገድ ልጆች ቢዘገዩም፣ በመገንዘባቸው እና «ይህን ለመቋቋም የዐማራው ነገድ መደራጀት አለበት» ብለው ቁርጠኛ ውሣኔ ለመድረስ ችለዋል።

ለዚህ ድርጅት ጥንስስ የሆነው በቅድሚያ ቁጥራቸው ፲፫(አሥራ ሦሥት) የሆኑ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ወገኖች፣ ከፍ ሲል የተጠቀሰውን አሣዛኝ፣ አስደንጋጭ እና አሳፋሪ ዜና እንደሰሙ፣ በሚያዝያ ፪ሺህ፬ ዓ.ም. የመሠረቱት የሞረሽ ወገኔ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ነው። ከዚያም እኒህ የቆረጡ ወገኖች እስከ መስከረም ፪ሺህ፭ ዓ.ም. ድረስ ለስድስት ወራት ያህል ባደረጉት ውይይትና የኃሣብ ፍጭት «ዐማራውን ከፈጽሞ ጥፋት ለመታደግ የሚቻለው የዐማራው ድምፅ ለመሆን የሚችል የሲቪክ ድርጅት በመመሥረት ነው፤» ብለው መተማመን ላይ ደረሱ። በዚህም መሠረት የዚህን ድርጅት መርኃግብር ቀረፁ። በመርኃግብሩ መካተት ያለባቸውን፦ ራዕዩን፣ ተልዕኮውን፣ ዓላማዎቹን እና ግቦቹን በግልጽ የሚያብራራ ሠነድ አዘጋጁ። ለዚህ መርኃግብር ማስፈጸሚያ የሚሆነውን የአባላቱ የተግባር መመሪያ የሆነ የመተዳደሪያ ደንብ አረቀቁ። የድርጅቱን ኅልውና (መመሥረት) ይፋ የሚያደርግ መሥራች ጉባዔ እንዲጠራ አስፈላጊውን ዝግጅት አደረጉ። ለመሥራች ጉባዔው ተሣታፊ የሚሆኑ የነገዱ አባሎችና በዓላማው የሚያምኑ እንዲመለመሉ አደረጉ። በዚህም መሠረት፦ ከአውስትራሊያ፣ ከካናዳ፣ ከአውሮፓ እና ከዩ.ኤስ. አሜሪካ በተውጣጡ ፺፫(ዘጠና

ሦሥት) መሥራች አባላት መስከረም ፳፯ ቀን ፪ሺህ፭ ዓ.ም. ድርጅቱ በይፋ ሊመሠረት ችሏል።

 • ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት እንዲመሠረት ያደረጉት አስገዳጅ ምክንያቶች ምንድን ናቸው?

ለማናቸውም ድርጅት መመሥረት መነሻ ምክንያቶቹ የችግሮች መፈጠርና የችግሮቹ መኖር በሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ማግኘት ናቸው። ከዚህ አንፃር ለሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መመሥረት መሠረታዊ ምክንያቶቹ ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ነገድ ላይ በታቀደ፣ በተጠና እና በተቀነባበረ መንገድ ያደረሰውና እያደረሰ ያለው የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ተግባር ነው። እነዚህም፡-

፩ኛዐማራው በነፍጠኝነት፣ በትምክህተኝነት፣ በገዥ መደብነት እና በጨቋኝ ብሔርነት፣ እና በኢትዮጵያ ብሔርተኝነት አቀንቃኝነት (ጠበቃነት) ተፈርጆ፣በኢትዮጵያ ተፈጠሩ ለተባሉ ችግሮች ሁሉ ተጠያቂ በመደረጉ።

፪ኛበኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ሁሉም ነገዶች እና ጎሣዎች ዐማራውን አውራ ደመኛ ጠላት አድርገው እንዲያዩት፣ እና የጥፋት እጃቸውንእንዲያነሱበት በመቀስቀሱ።

፫ኛበዐማራው ላይ በተቀነባበረ ሁኔታ ሠፊ ሥነ-ልቦናዊ እና አካላዊ ጥቃት እንዲደርስበት በመደረጉ። ፬ኛ፦ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች ተዘዋውሮ የመሥራትና የመኖር መብቱን በኃይል በመነጠቁ።

፭ኛ«የክልሉን ቋንቋ መናገር አትችልም» ተብሎ «የዐማራው ክልል» ተብሎ ከተከለለው አካባቢ ውጭ ባሉ አካባቢያዊ የጎሣ አገዛዞች ከመንግሥት ሥራበመባረሩ።

፮ኛዐማራውን ከማዕከላዊ መንግሥት ቢሮክራሲ ለማጽዳት «፵፭(አርባ አምሥት) ዓመት ዕድሜ እና የ፳(ሃያ) ዓመት አገልግሎት ያለው ጡረታ መውጣትአለበት» የሚል ቀመር በማውጣት፣ «የዐማራ ክልል» ከተሰኘው ጨምሮ ከመንግሥት መዋቅር በመባረሩ።

፯ኛበአሶሳ፣ በበደኖ፣ የአሰቦት ገዳምን ጨምሮ በወተር እና በሐረርጌ ልዩ ልዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች፣ በአርሲ አርባ ጉጉ፣ በወላይታ በአረካ፣ ፣ በወለጋ፣በኢሉባቡር እና በከፋ የተለያዩ ወረዳዎች ይኖሩ በነበሩ የዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈፀሙ። ዐማሮች በዘር ተነጥለው በእሳት በመቃጠላቸው፣ በጥይት በመደብደባቸው፣ ወንዶች የመራቢያ አካላቸውን በመሰለባቸው፣ እንዲሁም ነፍሰጡር እናቶች ሆዳቸው በሳንጃ ተቀዶ ሽል በመሰለቡ፣ ማየት የተሳናቸው አዛውንቶች ታርደው በመሰለባቸው።

፰ኛከሶማሌ፣ ከአፋር፣ ከደቡብ ብሔር/ብሔረሰቦች፣ ከኦሮሚያ እና ከቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልሎች ዐማራው ቤት ንብረቱን ተነጥቆ፣ የመኖርና የመሥራትኢትዮጵያዊ መብቱን ተገፎ በግፍ በመባረሩ፤

፱ኛዐማራው በገፍ መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መገረፉ፣ መሰደዱና በራሱ ማንነት እንዲያፍር፣ ትውልዱን አንገት ለማስደፋት ተዋራጅ ለማድረግ የተያዘው በማንነት

ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ተከታታይ በመሆኑ፤

፲ኛየዐማራውን እምነት፣ ባህል እና ቋንቋ የሚያጠፉ ድርጊቶች በየግዜው በመፈጸማቸው፤ ለምሣሌ፦ በቅርቡ በዋልድባ ገዳም ላይ የደረሰው ድፍረት፣ማፍረስና በገዳሙ መነኮሳት ላይ የደረሰው ስደት፣ ግርፋትና እሥራት፤

፲፩ኛየዐማራን ዘሩን የማጥፋት ብቻ ሣይሆን «የዐማራ ክልል» ተብሎ ከተከለለው ግዛት ውጪ ከዐማራ የፀዳ ግዛት መመስረት፤ በታላላቅ ከተሞች ያለውንየሕዝብ አሠፋፈር ቅጥ ለመቀየር «ዐማራው በብዛት ይኖርባቸዋል» ተብሎ በሚታመንባቸው ከተሞች፣ ማለትም፦ በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በሐረር፣ በጎባ፣ በጎሬ፣ በደብረማርቆስ፣ በደሴ፣ በደብረታቦር፣ በደብረብርሃን፣ በጎንደር፣ ወዘተርፈ ዐማሮችን እየለዩ ማፈናቀል ወይም የከተሞችን ጤናማ ዕድገት ማቀጨጭ፤

፲፪ኛየኢትዮጵያን የማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ ሂደት ታሪክ በመካድ የታሪኩን ባለቤት ዳግማዊ አፄ ምኒልክን በናዚነት መፈረጅ እና «ኃውልታቸውይፍረስ» የሚል ተቃውሞ በኦሮሞ ልሂቃን ስም ማነሣሣት፣ እንዲሁም በፀረ-ፋሽስት ትግል ሠማዕት የሆኑትን አርበኞች የእነ አቡነ ጴጥሮስን ኃውልት ማፍረስ ይጠቀሣሉ።

 • ዐማራው በዘር ተለይቶ በጠላትነት ተፈርጆ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበት ለመሆኑ ማሣያ ተጨባጭ መረጃዎቹ ምንድን ናቸው?

የትግሬ ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸመበት መሆኑ በተጨባጭ የሚያሳዩት ማስረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

አንደኛ፡- የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) የፖለቲካ መርኃግብር፣ በዚህ መርኃግብር የትግራይ ሕዝብ ደመኛ ጠላት “ዐማራ” እንደሆነናየትግራይ ሕዝብ ዐማራን ማጥፋት እንዳለበት በማያሻማ መንገድ የተገለጸ በመሆኑ፦

ሁለተኛ፡- በመለስ ዜናዊ የተጻፈው “የኤርትራ ሕዝብ ትግል ከየት ወዴት? ግምገማ 1979” የሚለው መጽሐፍ የትግራይ አውራ ጠላት ዐማራው መሆኑንእና ይህንን ብሔረሰብ ታግለው መጣል እንዳለባቸው የተገለጸው ዘረኛ አቋም፤

ሦስተኛ፡- ሕወሓት-ወያኔን ጨምሮ ሁሉም ብሔረሰባዊ ድርጅቶች “የኢትዮጵያ አውራ ችግር ብሔራዊ ጭቆና ነው፣ ጨቋኙም የዐማራው ነገድ ነው”ብለው የሚያምኑ እና ይህንን ነገድ ታግለው መጣል እንዳለባቸው በፖለቲካ መርኃግብሮቻቸው ያሠፈሩት በመሆኑ፤

አራተኛ፡- ሁሉም ብሔርተኛ ድርጅቶች በመርኃግብሮቻቸው መሠረት ዐማራውን ከሥነ-ልቦና እስከ አካለዊ ጥቃት የደረሰ መጠነ ሠፊ ጥቃትአድርሰውበታል። በመሆኑም በ1980 ዓ.ም. በሻዕቢያ እና በኦነግ ጥምረት በአሶሳ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን ሰብስበው ቤት ውስጥ በመዝጋት በእሳት አቃጥለው ጨርሰዋቸዋል። በአሰቦት ገዳም ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች እና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ላይ በኦሕዴድ/ሕወሓት፣ በአነግ እና በእስላማዊ የኦሮሞ ንቅናቄ ጥምረት አያሌ ዐማሮች ተጨፍጭፈዋል፣ ከነነፍሳቸው ገደል ተጥለዋል፤ በበደኖ ፣አርባ ጉጉ፣ ወተር፣ አረካ፣ ወለጋ፣ ከፋ፣ እና አርማጭሆ ዐማሮች በዘራቸው ብቻ እየተመረጡ ተገድለዋል፣ ታስረዋል፣ አካባቢውን እንዲለቁ ተደርገዋል፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቅዋል፣ ከሥራ ተባረዋል፤ ተሰድደዋል፤

አምስተኛ፡-መለስ ዜናዊ ኼርማ ኮኸን የተባለው የአሜሪካ ዲፕሎማት “መሬት ለምን በግል አይያዝም?” ብሎ ላቀረበለት ጥያቄ የሰጠው መልስ፦”መሬት ለግል ቢሰጥ ተጠቃሚ የሚሆነው ዐማራው ስለሚሆን፣ ይህ እንዳይሆን ስለማይፈለግና ዐማራውን ከመሬት ለመንቀል፣ መሬት በመንግሥት እጅ መያዝ እንዳለበት” የሰጠው መልስ፣ ኼርማን ኮኸን ከኢሣት ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ የሰጠው መልስ ያረጋግጣል፤

ስድስተኛ፡-የመለስ አማካሪና የሲ.አይ.ኤ ሰው የሆነው ሟቹ ፖል ሄንዝ በጻፈው ዘገባ ላይ “ወያኔ ፀረ-ዐማራ መሆኑንና ዐማራን ለማጥፋት የተደራጀ

እንደሆነ” የገለፀ በመሆኑ፤

ሰባተኛ፡- የሽግግር መንግሥቱ ሲዋቀር የሁሉም ነገዶች ተወካይ ተብየዎች እንዲገኙ ሲደረግ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ እና በማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታብቻ ሳይሆን፣ ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች መክቶ ያቆየ፣ በቁጥሩ ከሁሉም ነገዶች የላቀ ድርሻ ያለው የዐማራው ነገድ ያለመወከሉ መሠረታዊ ምክንያት በጠላትነት የተፈረጀ መሆኑን ነቃሽ በመሆኑ፤

ስምንተኛ፡- ወያኔ ዐማራን፣ አማርኛንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት የተደራጀና ይህንንም ሲሠራ የኖረ መሆኑን አቶ ገብረመድኅን አርኣያየተባሉ የቀድሞ የወያኔ አባል “መጽሐፍ ቅዱስን ያቃጥሉ የነበሩ እነማን ናቸው?” በሚል ርዕስ ያቀረቡት እና በድረ-ገጾች ያሠሰራጩት የምስክርነት ማስረጃ ሠነድ እና እኒህ ግለሰብ በተከታታይ ስለወያኔ ማንነትና ዓላማ ያቀረቧቸው መረጃዎች፤

ዘጠነኛ፡- የዐማራውን እምነት፣ ባህልና ቋንቋ የሚያጠፉ ድርጊቶች በየግዜው በመፈጸማቸዉ፦ ለምስሌ በቅርቡ በዋልድባ ገዳም ላይ የደረሰው ድፍረት፣ማፍረስና በገዳሙ መነኮሳት ላይ የደረሰው ስደት፣ ግርፋትና እስራት፤

አሥረኛ፡- ከደቡብ፤ ከኦሮሚያ፣ ከሶማሌ፣ ከአፋር፣ ከቤንሻንጉል-ጉምዝ እና ከራሱ ከዐማራ ክልል ከወልቃይት፣ ከጠገዴ፣ ከጠለምት፣ ከሰቲት ሁመራ፣እና ከአርማጨሆ የተባረሩ አያሌ ዐማሮች በመኖራቸው፤

አሥራ አንደኛ፡- አቶ ገሠሠው እንግዳ፣ አቶ አስገደ ገብረሥለሴ፣ አቶ ብሥራት አማረ፣ አቶ አስራት አብርሃ የተባሉ የሕወሓት አባላት የነበሩ በተከታታይ“ታሪክ አጉዳፊው የአልባኒያ ደብተራ” “ገሐዲ ቁ.1”፣ “ፍኖተ ገድል” እና “ከአገር በስተጀርባ”፣ በተሰኙ መጽሐፎቻቸው ወያኔ ዐማራን በጠላትነት ፈርጆ እርሱን ለማጥፋት መንቀሳቀሱንና ያጠፋውንም ሕዝብ በዝርዝር ስላረጋገጡ፤

አሥራ ሁለተኛ፡- የወያኔ መሪዎች ስብሐት ነጋ፣ ሣሞራ የኑስ፣ ዐባይ ፀሐዬ፣ ወዘተርፈ በተደጋጋሚ በተለያዩ ጊዜያት “ዐማራን እና የኦርቶዶክስኃይማኖትን ላይነሳ ቀብረነዋል” በማለት የሰጧቸው ቃለ ምልሶች፤

አሥራ ሦስተኛ፡- “፵፭(አርባ አምሥት) ዓመት ዕድሜ የሞላው እና ፳(ሃያ) ዓመት አገልግሎት ያለው ጡረታ ይውጣ፤” በማለት ከመንግሥት ቢሮክራሲየተባረረው ዐማራ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከተባረሩት ነባርና በሳል አስተማሪዎች መካከል ፺፰በመቶ የሚሆኑት ዐማሮች መሆን፣ የመባረራቸው ምክንያት በሥራ ድክመት ሳይሆን፣ በዘር መሆኑን በተጨባጭ የሚያሣይ መሆኑ፤

አሥራ አራተኛ፦ በ፪ሺህ፩ ዓ.ም. በ፬ኛው ዓመት የሥራ ዘመኑ በ፲፫ኛው ዓመት መደበኛው የወያኔ የይስሙላ ፓርላማ ስብሰባ ላይ የስታትስቲክስባለሥልጣን ኃላፊ የሆነችው ወይዘሮ ሣሚያ ዘካሪያ ባቀረበችው ዘገባ መሠረት ከ፲፱፻፹፱-፲፱፻፺፱ ዓ.ም. በነበሩት ፲(አሥር) ዓመታት ውስጥ ብቻ “ከ2.5 ሚሊዮን የማያንሱ ዐማራዎች ‘systematic’ በሆነ መንገድ የቁጥር ቅነሣ ታይቷል፣ ከቆጠራው ጠፍተዋል፤” ስትል ያረጋገጠቸው ምስክርነት፣ ዐማራው በጠላትነት ተፈርጆ በሰከነ መንገድ በግፍ መገደሉን የሚያረጋግጥ መረጃ በመሆኑ፣

አሥራ አምስተኛ፡- በ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. ከምሥራቅ ወለጋ ፳፭ሺህ፣ በ፪ሺህ፬ ዓ.ም. ከጉራፈርዳ ፸፰ሺህ፣ በ፪ሺህ፭ እና በ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ከቤንሻንጉል-ጉሙዝ

 • ከምዕራብ ሸዋ ዳና ወረዳ፣ ከምሥራቅ ወለጋ ፣ የዐማራ ተወላጆች ኃብት ንብረታቸውን ተነጥቀው ተባርረዋል። ያህል ሰዎች በአሠቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል።

አሥራ ስድስተኛ፦ በዘንድሮው ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ብቻ የትግሬ-ወያኔ ካድሬዎች «ሕገ-ወጥ ግንባታ አካሂዳችኋል» እና «ቦታችሁ ለልማት ይፈለጋል» የሚሉሠንካላ ምክንያቶችን በመደርደር፦ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህርዳር፣ በደብረማርቆስ፣ በደሴ፣ በሐረር እና በሌሎችም ከተሞች በሺህዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን በግሬደር እና በሰው ኃይል አፍርሰዋል። የትግሬ-ወያኔዎች በየዓመቱ ይህን አረመኔያዊ ድርጊት የሚፈፅሙት ሆን ብለው ዘወትር ክረምትን

ታክከው ነው። የዚህ ድርጊት ቀዳሚ ተጠቂዎች ዐማሮች መሆናቸው ይታወቃል።

አሥራ ሰባተኛበአገር የመኖርና የመሥራት መብቱን ተገፎ በስደት ላይ ከሚገኘው ኢትዮጵያዊ የዐማራው ነገድ ቁጥር የበዛ በመሆኑ፤ ይህንን ሃቅየወያኔው የዩናይትድ ስቴት ኦፍ አሜሪካ አምባሳደር የነበረው አቶ ካሣሁን አየለ ኅዳር ፲፫ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. በቁጥር ዋሽ/209/98 በአድራሻ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ካቢኔ ጽሕፈት ቤት በጻፈው ሪፖርት ሁኔታውን እንዲህ ሲል ገልጾታል፣ «….በአጠቃላይ በአሜሪካን አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና

የኢትዮጵያ ተወላጆች መካከል ወደ ፷(ስድሣ) በመቶ የሚደርሱት የአማራ ብሔረሰብ ተወላጆች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ መካከል ምዕራባዊ የአሜሪካን ክልል ጨምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የጎንደር አካባቢ ተወላጆች ናቸው።» በማለት ለአለቆቹ ባቀረበው ሪፖርት ያረጋገጠ በመሆኑ።

አሥራ ስምንተኛ«ዐማራ» ብለው የከለሉትን ግዛት ዐማሮች ማስተዳደር ሲገባቸው፣ ነገር ግን ዐማራው በጠላትነት ተፈርጆ እንዲጠፋ የተወሠነበትበመሆኑ በሌሎች ነገዶች እና ጎሣዎች ተወላጆች እንዲገዛ ተበይኖበታል። ይህንንም የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሆን ተብሎ በዐማራው ላይ ለሚፈፅመው የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል፣ ፈፃሚዎቹ ለወደፊቱ እንዳይጋለጡ ለማድረግ የታለመ እንደሆነ ያረጋግጣል።

 • 7.     የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ራዕይ ምንድነው?

የድርጅቱ ራዕይ የሚከተሉት ናቸው፦

፩ኛዐማራው በኢትዮጵያ የግዛት ክልል ውስጥ እንደሌሎቹ ነገዶች ሁሉ፣ ኅልውናው ተጠብቆ፣ እየደረሰበት ያለው መገደል፣ መሳደድ፣ መዋረድ፣አንገት መድፋት፣ ከቀየው መፈናቀል ቆሞ፤ በፈለገው ቦታ፣ ባሻው የሥራ መስክ የመኖር እና ተንቀሳቅሶ መሥራት ሁለንተናዊ መብትና ክብሩ ተጠብቆ ማየት፤

፪ኛየሕዝባዊ የዜግነት መርሆዎች (ሲቪክ ናሽናሊዝም) የተሰኙት የወል የዜግነት መገለጫ የሆኑ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እና የሕግ የበላይነት ሠፍኖማየት፤

 • የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ተልዕኮ ምንድን ነው?

ሞረሽ ወገኔ አራት ተደጋጋፊ ተልዕኮዎች አሉት፤ እነርሱም፦

፩ኛየአንድ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ የሆኑት ነባር የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵዊነት መገለጫ የሆኑ ዕሴቶችና ተቋሞች ተጠብቀው እና ዳብረው፣እንዲሁም ሁሉም የኢትዮጵያ ነገዶችና ጎሣዎች፣ ኃይማኖቶችና አመለካከቶች በእኩልነት የሚታዩበት፤ መቻቻል፣ መከባበርና መደጋገፍ የሰፈነባት ኢትዮጵያን ዕውን ማድረግ፤

፪ኛበአክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞችና ድርጅቶች አማካኝነት በዐማራው ነገድ ላይ የተካሄደውንና በመካሄድ ላይ ያለውን የዘር ማጽዳት ዘመቻ ማስቆም፤

፫ኛለዐማራው ነገድ ኅልውና ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች ማለትም፦ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ ሕይወት፣ በትምህርት፣ በጤናና በመሳሰሉት መስኮችሁለንተናዊ ድጋፍ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ማቀነባበር እና ዐማራው ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ፤

፬ኛየኢትዮጵያ ኅልውና ምሰሶ ሆኖ የኖረው የዐማራው ነገድ፣ ለወደፊቱ የአገሪቱ ኅልውና በአስተማማኝነት መቀጠል እንዲችል፣ ተቀራራቢና ተመሳሳይግቦችና ዓላማዎች ካሏቸው ድርጅቶች፣ ቡድኖችና ግለሰቦች ጋር በመሆን ለጋራ ብሔራዊ ዕሴቶች ዳብሮ መቀጠል ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ ናቸው።

 • ለመሆኑ ዐማራ ማነው?

በሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አቋም መሠረት «ዐማራ» ማለት የሚከተሉትን ፱(ዘጠኝ) መሠረታዊ መርሆዎች የተቀበለና ያመነ ነው።

፩ኛዐማራ ነኝ ብሎ የሚያምን፤

፪ኛበኢትዮጵያ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች በተቋቋሙ ልዩ ልዩ ስብስቦች (ድርጅቶች) ወደ አመራር ብቅ እንዳይል የተገለለ (የተገደፈ) መሆኑን የተገነዘበ፤

፫ኛኢትዮጵያ ረጅም የአገራዊ እና የመንግሥትነት ታሪክ ያላት እና በሀወርታዊ ሆና የኖረች አገር መሆኗን፣ በዚህም ሀወርታዊነት መቀጠል አለባት ብሎየሚያምን፤

፬ኛየኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ ሂደት በዓለም ከታዩት የሚለየው በቦታ፣ በጊዜና በአድራጊ ግለሰቦች እንጂ በቀረው በነባራዊ ሁኔታዎችአስገዳጅነት በግድ መታለፍ የነበረበት መሆኑን የሚያምን፤

፭ኛእስከዚህ ወቅት ድረስ ቋንቋን መሠረት አድርጎ «እኔ ዐማራ ነኝ» ብሎ ከሌሎች ተነጥሎ ያልተደራጀ፤ በሰፊዋ ኢትዮጵያ ተሰራጭቶ የሚገኝ መሆኑንያወቀ፤

፮ኛ«የኢትዮጵያ አንድነት እና አገራዊነት ዳብሮ መቀጠል አለበት» የሚል፤

፯ኛበኢትዮጵያ የአገራዊ እና የማዕከላዊ መንግሥት ምሥረታ ሂደት የአያያዥነት (የሙጫነት) ሚና የተጫወተ መሆኑን የተገነዘበ፤

፰ኛበተለያዩ ወቅቶች ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሱ ኃይሎች የጥቃት ቀዳሚ ዒላማ በመሆን ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ መሆኑንያወቀ፤

፱ኛበትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ «ነፍጠኛ፣ ትምህተኛ፣ አድኃሪ፣ ወዘተርፈ» የሚሉ የማጥላያ ስሞች ተሰጥተውት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊመብት እና ጥቅሞቹን የተነጠቀ እና የተገፈፈ ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ መሆኑን ያመነ ነው።

 1. የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ዓላማዎች ምንድን ናቸው?

ድርጅቱ ሦሥት ዓብይ ዓላማዎች አሉት። እነርሱም፦

፩ኛበዘራቸው ምክንያት ከተለያዩ የምሥራቅ፣ የምዕራብ፣ የደቡብና የመሐል ኢትዮጵያ ክፍሎች ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለተፈናቀሉ የዐማራነገድ አባሎች ከዕለት ደራሽ እስከ ዘለቄታ ማቋቋሚያ የሚሆን ዕርዳታ ማሰባሰብና ለተፈናቃዮች ማድረስ፤

፪ኛበዘመነ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በአውራ ጠላትነት ተፈረጆ፣ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ላለው የዐማራ ነገድድምፅ ሆኖ ማገልገል፤

፫ኛየዐማራው ነገድ በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ ተገቢ ቦታውን እንዲይዝ ሁለንተናዊ ዐቅሙን ማጎልበት፤

 1. የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ግቦች ምንድን ነው?

የሞረሽ ወገኔ ግቦች ፮(ስድስት) ናቸው። እነዚህም፦

፩ኛበዐማራው ላይ የተከፈተውን የዘር ማፅዳት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ፈጽሞ ማስቆም፤

፪ኛበዐማራው ነገድ ላይ የዘር ማጽዳት እና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ ቡድኖችን እና ግለሰቦችን ለፍትህ ማቅረብ፤

፫ኛየዐማራው ማንነት ሁለንተናዊ መገለጫ የሆኑ የወል እሴቶችን ከጥፋት መከላከል፣ በወያኔ አገዛዝ እንዲጠፉ የተደረጉትን ወደነበሩበት መመለስናማዳበር፤

፬ኛየኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ጥቅም፣ እንዲሁም ለሕዝቡ ሉዐላዊነት፣ ሰላም፣ ዕኩልነት እና ፍትሕን የሚያረጋግጥ የምልዐተ-ሕዝቡን

ፈቃድ ያገኘ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመገንባት ከሚታገሉ ኢትዮጵያዊ ኃይሎች ጎን በመሰለፍ የበኩሉን ድርሻ ማበርከት፤

፭ኛየትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም እና የግዛት አንድነት፣ እንዲሁም በሕዝቡ መብት እና ነፃነት ላይ ያደረሰውን አገራዊ ክህደትናየፈጸመውን ወንጀል ለዓለም ኅብረተሰብ ማጋለጥ፤

፮ኛአገዛዙ በሕዝባዊ አመጽ እንዲወገድ የሕዝባዊ እምቢተኝነትን ስሜት በሕዝቡ ውስጥ ማስረጽ፣ ሕዝቡ «የእኔ» የሚለው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓትእንዲመሠረት መታገል፤

12.  ሞረሽ ወገኔ ከሌሎች ጋር የሚኖረው ግንኙነት እንዴት ይገለጻል?

የዐማራው ነገድ እየተካሄደ ባለው ዲሞክራሲያዊ ትግል አካል ሆኖ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለሕግ የበላይነት፤ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለሕዝቡ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ከሚታገሉ ኃይሎች፣ እንዲሁም የዐማራውን ነገድ በጠላትነት ከማይመለከቱ ወይም የፖለቲካ ሥልጣን መረማመጃ አድርገው ከማያዩት ከማናቸውም ድርጅቶች ጋር ሁሉንም ኢትዮጵያውያንን የጋራ ጥቅም በሚያስከብሩ ጉዳዮች ዙሪያ የሚጠበቅበትን ሁሉ በብቃት ለመወጣት የበኩሉን ያልተቆጠበ ጥረት ያደርጋል።

13.  ሞረሽ ወገኔ የሚታገለው ለማን ነው? ምንንስ ይቃወማል?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፦

፩ኛበነገድ፣ በጎሣና በኃይማኖት ልዩነቶች ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ አደረጃጀትን አምርሮ ይታገላል። ስለሆነም የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ ቡድን በዚሁአመለካከት በመመራት የዐማራን ነገድ ተወላጆችን፣ የአማርኛ ቋንቋን፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ያደረገውንና እያደረገ ያለውን ተግባር፣ ፖሊሲና መመሪያዎችን አምርሮ ይቃወማል፤

፪ኛበቋንቋ ልዩነት፣ ነገድ እና ጎሣዎችን መነሻና መድረሻ አድርጎ የተዋቀረን የፌደራል የመንግሥት አደረጃጀትን ይቃወማል፤ ፫ኛ፥ በችሎታ እና በዕውቀት ሳይሆን፣ በጎሣ እና በፖለቲካ አቋም የሚሰጡ መንግሥታዊ ኃላፊነቶችን ይቃወማል፤

፬ኛኢትዮጵያውያን በዜግነታቸው በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ተዘዋውረው፣ በፈለጉት አካባቢ የመኖር እና የመሥራትን መብት የሚገድብማናቸውንም እርምጃ ይቃወማል፣ አድራጊዎችንም አምርሮ ይታገላል፤

፭ኛየዜጎችን የመደራጀት፣ ኃሣብን የመግለጽ፣ የመዘዋወር መብቶችን እና ነፃነቶችን የሚገፍ ወይም የሚገድብ ማናቸውንም ዓይነት ድርጊት፣ እንዲሁምያለ ሕግ አግባብ የመያዝ፣ የመፈተሽ፣ የመበርበርን ድርጊቶችን አምርሮ ይታገላል፤

፮ኛፀረ-የኢትዮጵያ አንድነት እና ፀረ-ኢትዮጵያዊነትን ይቃወማል፣ ይህንንም አቋም እና አመለካከት አምርሮ ይታገላል፤

 1. ሞረሽ ወገኔ ህልውናውን ከአገኘ ጀምሮ ምን ተግባሮችን አከናወነ?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከተመሠረተ ከመስከረም ፳፯ ቀን ፪ሺህ፭ ዓ.ም. ጀምሮ የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባሮችን አከናውኗል።

፩ኛድርጅቱ የሚመራባቸውን ማለትም መርኃግብሩን፣ የመተዳደሪያ ደንቡን እና ለደንቡ ተፈጻሚነት ማረጋገጫ የሚሆኑትን የዲሲፕሊንና የአፈጻጸምመመሪያ ተዘጋጅቶ በሥራ እንዲውል ተደርጓል።

፪ኛድርጅቱ ሕጋዊ ሰውነት እንዲያገኝ በተደረገው ጥረት በአሜሪካን አገር፣ በሜሪላንድ ግዛት ተመዝግቦ ሥራውን በሕጋዊ አግባብ እያከናወነ

ይገኛል።

፫ኛየድርጅቱን መመሥረት የዐማራው ነገድ ተወላጆች እንዲያውቁት እና ሁለንተናዊ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉለት በሬዲዮ፣ በፓልቶክ፣ በድረ-ገጾችእና በሕዝባዊ ውይይቶች የማስተዋወቅ ሥራዎች ተሠርተዋል። ሞረሽ ወገኔ ሕዝባዊ መሠረቱን እያሠፋ የመምጣቱን ሂደት የሚያመለክቱት፦ በዩ ኤስ አሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያ እና በእስራኤል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት መሠረታዊ ማኅበራት፣ ብሔራዊ እና አኅጉራዊ ቅርንጫፍ ኮሚቴዎች ተደራጅተው ሥራ መጀመር መቻላቸው ነው።

፬ኛየዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን እና የሠማዕቱን አርበኛ የአቡነ ጴጥሮስን ሐውልቶች ከመፍረስ ለመታደግ ሕዝቡ ተቃውሞን እንዲያሰማ ለማድረግ፻፲፯ኛውን ዓመት የዐድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ምክንያት በማድረግ አምና እሑድ የካቲት ፳፬ ቀን ፪ሺህ፭ ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ ሕዝባዊ ስብሰባ በመጥራት ጉዳዩን የማሳወቅ ሥራ ተሠርቷል። በሕዝባዊ ስብሰባው ወቅት፣ ስለ አድዋ ጦርነት ምክንያትና ውጤት፣ በአድዋ ጦርነት የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ሚና፣ የሰማዕታቱ የአቡነ ጴጥሮስና የአቡነ ሚካኤል የነፃነት ተጋድሎ ታሪክ በባለሙያተኞች ትምህርት እንዲሰጥ ተደርጓል፤ በራሪ ወረቀቶችም ለሕዝብ ታድለዋል። ለሁለቱ ሐውልቶች መታሰቢያዎች ማነቃቂያ እንዲሆኑ አምስት ሺህ በደረት ላይ የሚንጠለጠሉ ሜዳሊያዎች ተሠርተው በመጠነኛ ዋጋ ለሽያጭ እንዲቀርቡ ተደርጓል። ዘንድሮም ተመሣሣይ የሆነ ዝግጅት ቅዳሜ የካቲት ፳፪ ቀን ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ተዘጋጅቶ ሠፊ የቅስቀሣ ሥራ ተሠርቷል።

፭ኛየድርጅቱ ልሣን፣ የዓላማው ማስፋፊያ፣ እንዲሁም ለዐማራው የመገናኛ፣ የመረጃ መለዋወጫ እና የመማማሪያ መድረክ የሆነው «ሞረሽ» የተሠኘጋዜጣ ከጥቅምት ፪ሺህ፮ ዓ.ም. ጀምሮ ሥራ ጀምሯል፤ ኅትመቱም በኤሌክትሮኒክ መልክ በድረገፆች እና በኢሜይል በመሠራጨት ላይ ይገኛል።

፮ኛከ፵፯ (አርባ ሰባት) በላይ በጥናት ላይ የተመሠረቱ ወቅታዊ መግለጫዎች ተዘጋጅተው ለሕዝብ እና ለአባላት በድረገፆች እና በሌሎችም መንገዶችእንዲሠራጩ ተደርጓል።

፰ኛ፥ በዐማራው የመደራጀት አስፈላጊነት፣ በዳግማዊ አፄ ምኒልክ በዘመናዊት ኢትዮጵያ ምሥረታ የመሪነት ሚና፣ በዐድዋ ጦርነት ምክንያት እናውጤቶቹ፣ ፀረ-ፋሽስት የነፃነት ትግል ዋና ተዋናይ በነበሩት አርበኞቻችን ታሪካዊ ተጋድሎ፣ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ዐማራን፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ኃይማኖትን፣ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ወሣኝ ሚና የተጫወቱትን ግለሰቦች እና ድርጅቶች ማንነት የሚያብራሩ ጥናታዊ ጽሑፎች ተዘጋጅተው ለአባላት እና ለድርጅቱ ደጋፊዎች እንዲሠራጩ ተደርጓል።

፱ኛበዐማራው ነገድ ላይ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ለዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አቅርቦ ፍትህ ይገኝዘንድ ፕሮጀክት ተነድፎ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ ይገኛል። በዚህ አጋጣሚ ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ማንነት የምታውቁ፣ ያሏችሁን መረጃዎች ለሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በመጠቆምና በማመላከት እንድትተባበሩን ወንጀል በተፈጸመበት የዐማራው ሕዝብ ስም አበክረን እንጠይቃለን።

፲ኛከደቡብ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከሶማሌ እና ከቤንሻጉል-ጉምዝ ክልሎች እንዲሁም ከወልቃይት፣ ከጠገዴ፣ ከሰቲት፣ እና ከጠለምት ወረዳዎችየተፈናቀሉትን ዐማሮች ማንነት፣ ብዛት፣ የደረሰባቸውን በደል ዓይነት እና ደረጃ፣ እንዲሁም የተነጠቁትን የንብረት መጠን ለማወቅ ጥረቱ ቀጥሏል። በዚህም መሠረት ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከከማሼ ዞን፣ ከያሶ ወረዳ በ፪ሺህ፭ ዓ.ም. ተፈናቀሉትን ዐማሮች ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ችለናል። በበለጠ ዝርዝር መረጃውን በድረ-ገጻችን ላይ ይመልከቱ (http://www.moreshwegenie.org)። እኒህን በከፍተኛ ሥቃይ ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ከዕለት ዕርዳታ እስከ ዘለቄታዊ ማቋቋም በሚደርስ ሁኔታ ለመታደግ፣ አስፈላጊዎቹ የፕሮጀክት ሠነዶች ተዘጋጅተዋል። ለወገን ደራሹ ወገን ነውና በዚህ

ረገድ በዓለም ዙሪያ ተበትኖ የሚኖረው የዐማራ ተወላጅ ሁሉ የወገኑ ሠቆቃ ተሰምቶት የድጋፍ እጁን እንዲዘረጋልን እንጠይቃለን።

፲፩ኛየትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ በዐማራው ነገድ ላይ እየፈጸመ ያለውን የዘር ማፅዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል ዓለም አቀፍና አኅጉራዊ ድርጅቶችአውቀውት በአገዛዙ ላይ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲያደርጉ የሚያስችል የተጠናከረ መረጃ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

 1. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ለወደፊቱ ምን ሊሠራ አቅዷል?

የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የወደፊት የሥራ ዕቅድ በመሥራች ጉባዔው ለሁለት ዓመታት እንዲሠሩ ያፀደቃቸውን ተግባሮች ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር እያጣጣሙ ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ ዝርዝሩን በድረ-ገጹ ይመልከቱ (http://www.moreshwegenie.org)። በዚህም መሠረት በቅርቡ የጀመራቸው የተቀናጁ ሥራዎች የሚከተሉት ናቸው።

ሀ)          የፍትኅ አፈላላጊ ፕሮጀክት

የዚህ ፕሮጀክት ራዕይ ድርጅቱ ለዐማራው ሕዝብ የገባውን ቋሚ ጠበቃ ሆኖ የመገኘት ሚናውን መወጣት ሲሆን ግቦቹም፦

፩ኛ፥ ለዘመናት በተከታታይ በዐማራዉ ሕዝብ ላይ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችንና ድርጅቶችን ለፍትኅ ማቅረብ፤

፪ኛ፥ በዐማራዉ ነገድ ላይ ዳግም የዘር ማጥፋትም ሆነ የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዳይፈጸምበት በሁለንተናዊ አቅጣጫ ራሱን የመከላከል አቅሙንማጎልበት ናቸው።

ለ)          የተፈናቃይ ወገኖች መልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት

የመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ራዕይ ለወገኑ ቤዛ የሚሆን ኢትዮጵያዊ የዐማራ ትውልድ መፍጠር ነው። ግቦችም የፕሮጀክቱ ግቦች፦

፩ኛከተፈናቃይ ዐማሮች መካከል በተለይ ለአደጋ የተጋለጡትን (ሕፃናትን ፣ እናቶችን እና አረጋውያንን) መታደግ፤

፪ኛበተከታታይ ዘመናት በትግሬ-ወያኔ የግፍ አገዛዝ የተፈናቀሉ ዐማሮችን ከተረጂነት ይልቅ ራሣቸውን የቻሉ ዜጎች እንዲሆኑ ማስቻልናቸው።

ሞረሽ ድረሱልን!

ይህንን ፕሮጀክት ከግብ ማድረስ የምንችለው ከላይ በፎቶግራፉ ላይ እንደሚታዩት ወገኖቻችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት ዐማሮች የሚኖሩበትን

ምድራዊ ሲዖል ለመለወጥ ቆርጠን በመነሣት መሆን ይኖርበታል።

 1. ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማንን ይወክላል?


ስሙ እንደሚያመለክተው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የሚወክለው፣ በዘሩ ምክንያት በዘረኛው የትግሬ ወያኔ አገዛዝ የዘር ማጽዳትና የዘር ማጥፋት ወንጀል የተፈጸመበትን የዐማራን ነገድ ተወላጆች ነው።

 1. በዐማራው ላይ ለደረሱ ጭፍጨፋዎች እና በደሎች ማሣያ ነቃሽ አብነቶች

የትግሬ-ወያኔ ናዚያዊ የአገዛዝ ሥርዓት ገና ከተመሠረተበት ከየካቲት ፲፱፻፷፯ ዓ.ም. ጀምሮ «ዋና ጠላቴ ነው» ብሎ በፈረጀው በዐማራው ሕዝብ ላይ የዕልቂት ጦር ሠብቆ መነሣቱ የአደባባይ ምሥጢር ነው። ድርጅቱ ይህንን ዓላማውን በመርኃግብሩ በግልፅ አሥፍሮታል፦

ይህን ዓላማ አንግቦ የተነሣ ሠይጣናዊ ድርጅት ለዐማራ ሕዝብ ትሩፋት ያመጣል ብሎ መጠበቅ «ከዕባብ እንቁላል እርግብ ይፈለፈላል» ብሎ የመነሁለል ያህል ይቆጠራል። ከዚህ በታች ለአብነት ያህል የተጠቀሱት አጫጭር ዘገባዎች፣ የትግሬ-ወያኔ እና አጋሮቹ እነ ኦነግ በዐማራው ሕዝብ ላይ በየጊዜው ከፈፀሟቸው ዘግናኝ ድርጊቶች እጅግ ጥቂቶችን ነው።

አሶሳ

በሻቢያ እና ወያኔ አመራር ሠጪነት፣ ኦነግ በአሶሳ አካባቢ ሁለት ዘግናኝ የጭፍጨፋ ድርጊቶችን ፈፅሟል። በ፲፱፻፹ ዓ.ም. በባምቤሲ ወረዳ፣ ሸርቆሌ ቀበሌ ይኖሩ የነበሩ ዐማሮችን ሰብስቦ፣ በስዊድን ተራድኦ ትምህርት ቤት በማጎር በጅምላ አቃጥሏቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም በ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. በአሶሳ ከተማ ነዋሪ የነበሩትን ዐማሮች በጥይት ረሽኗል፣ በገጀራ ጨፍጭፏል፣ ከእነ ሕይወታቸው በእሣት አቃጥሏል።

ሰሜን ጎንደር

በ፲፱፻፸፪ ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ የተከዜን ድንበር ተሻግሮ በወረራ መልክ ወደ ፀለምት እና ወልቃይት ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የአካባቢውን ነዋሪ በጅምላ በመፍጀት፣ ኃብት፣ ንብረቱን እና መሬቱን በመቀማት፣ ሴቶችን አስገድዶ በመድፈር በአሃዝ ሊገለፅ ከሚችለው በላይ አሠቃቂ ግፍ ፈፅሟል። እስካሁን ከአካባቢው ተወላጆች በተገኙ መረጃዎች መሠረት በአሥር ሺህዎች የሚቆጠሩት በግፍ ተጨፍጭፈዋል፣ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ በኃይል ከርስታቸው ተፈናቅለው በእነርሱ አፅመ-ርስት ትግሬዎች ሠፍረውበታል።

ደቡብ ጎንደር

በ፲፱፻፹፪ ዓ.ም. የትግሬ-ወያኔ ከትግራይ ተስፈንጥሮ መላዋን ኢትዮጵያ ለመውረር ሲንደረደር ከባድ ፈተና የገጠመው በደቡብ ጎንደር አካባቢ እንደነበረ ይታወሣል። በአጠቃላይ ለዐማራ ያለው ጥላቻ እንደተጠበቀ ሆኖ ይህንን ቂም በመያዝ፣ ይህ መሠሪ ቡድን ከ፲፱፻፹፫ እስከ ፲፱፻፹፮ ዓ.ም. በነበሩት አራት ዓመታት ውስጥ ብቻ በደቡብ ጎንደር በሺህዎች የሚቆጠሩትን ገድሏል፣ ፳፪ሺህ ዐማሮችን በ፳፰ (ሃያ ስምንት) ልዩ ልዩ የማሰቃያ እና የማጎሪያ ሥፍራዎች አሥሮ አሠቃይቷል። በአካባቢው የነበሩትን የመሠረተ-ልማት ተቋሞች ሙሉ በሙሉ ዘርፏል፣ መዝረፍ ያልቻለውን አውድሟል።

ሐረርጌ እና አርሲ

በ፲፱፻፹፫-፹፬ ዓ.ም. የኦነግ እና የመሠሉ የኢስላሚክ ኦሮሚያ ቡድኖች ከትግሬ-ወያኔ ጋር በመቀናጀት በምሥራቅ ኢትዮጵያ እጅግ ዘግናኝ ጭፍጨፋዎችን ፈፅመዋል። ለምሣሌም ያህል በበደኖ፣ በወተር፣ በአሰቦት ገዳም፣ በአርባጉጉ፣ ወዘተርፈ ይኖሩ የነበሩት ዐማሮች ከእነ ሕይዎታቸው በገደል አየተወረወሩ ተገድለዋል፣ ነፍሰጡር ማኅፀኗ ተቀድዶ ሽል ተሰልቧል፣ በአጠቃላይ ሰው ሣይሆን አውሬ የማይፈፅመው ግፍ ተፈፅሞባቸዋል።

ወለጋ

ወለጋ ሌላው ኦነግ እና የትግሬ-ወያኔ ዐማሮችን የሚፈጁበት የግድያ ሜዳቸው ነው። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ብቻ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዐማሮች ከወለጋ ተፈናቅለዋል፣ በሺህዎች የሚቆጠሩት በአሠቃቂ ሁኔታ ተጨፍCEፈዋል።

በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች

የትግሬ-ወያኔ በዐማራ ላይ የፍጅት ዘመቻ ያወጀው በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች በመሆኑ «ከዚህ መልስ» ተብሎ ዐማራው በሰላም የሚኖርበት የኢትዮጵያ ክፍል የለም። ባለፉት ፳፫(ሃያ ሦሥት) ዓመታት ብቻ ከ፮ ሚሊዮን የሚበልጥ ቁጥር ያላቸው ዐማሮች በተለያዩ መንገዶች በትግሬ-ወያኔ እና በተባባሪዎቻቸው በጅምላ ተጨፍጭፈዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትም የኅልውናቸው መሠረት ዮሆኑትን፥ መሬትን፣ ሥራን እና በሰላም መኖርን ተነጥቀዋል። ይህንን የግፍ ስንክሣር እየተከታተልን በየጊዜው በዝርዝር እናቀርባለን።

 1. ማስገንዘቢያ፡

ዐማራው ኢትዮጵያዊነቱ ተክዶ ከመገደል፣ ከመታሰር፣ ከሥራ ከመፈናቀል ሌላ በኢትዮጵያ ምድር አትኖርም ተብሎ እንደ ክፉ አውሬ በመሳደድ ላይ ነው፡፡ ይህ ዐማራን፣ አማርኛ ቋንቋና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ለማጥፋት ዘመቻ የከፈተው የትግሬ ወያኔ፣ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ስለሆነም፦

በመጀመሪያ፦ ዐማራው ኅልውናውን ለማስጠበቅ፣ ቀጥሎም ማተቡ፣ እምነቱና እናቱ የሆነችውን ኢትዮጵያን ከብተናና ከጥፋት ለመታደግ መደራጀትምርጫ ሳይሆን፣ ግዴታ መሆኑን ተገንዝቦ ሞረሽ ወገኔን የዐማራ ድርጅትን እንዲቀላቀል ጥሪ እናቀርባለን።

በሁለተኛ ደረጃ፦ «ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት እታገላለሁ» የሚል የየትኛውም ነገድ አባል፣ ዐማራው የማይኖርባት ኢትዮጵያ፣ኢትዮጵያ ልትሆን እንደማትችል ተረድቶ፣ ዐማራው ለኅልውናው መጠበቅ የሚያደርገውን ትግል ከመደገፍ ባሻገር፣ የትግሬ ወያኔ ፀረ-ዐማራ ብቻ ሳይሆን፣ ፀረ-ኢትዮጵያ መሆኑን በማመን፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የሚያደርገውን አገርና ትውልድን ከጥፋት የመታደግ እንቅስቃሴ በሙሉ ልብ ሊደግፈውና ሊያበረታታው ይገባል።

«ዐማራው በዐማራነቱ አይደራጅም» የሚሉት እያዘናጉ ዐማራውን ለፍጅት የመዳረግ ዘይቤ ጊዜው ያለፈበት ፌዝ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ስለሆነም ለሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ዓላማ ስምረት ከዐማራው ነገድ አባላት፣ በኢትዮጵያ አንድነትና ነፃነት ከሚያምኑ ኢትዮጵያውያን የዕውቀት፣ የመረጃ፣ የሐሳብ እና የገንዘብ ድጋፋችሁ እንዳይለየን የትግሬ-ወያኔ የጥቃት ሰለባ በሆነው የዐማራ ነገድ ስም አደራ እንላለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.