የአዳራሽ ጩኸት ወይስ ቁም ነገር ያዘለ ዉይይት ? (ግርማካሳ)

የአብን አመራር ጋሻው መርሻ፣ አብን በዛሬ የ”ተፊካካሪ ፓርቲዎች” ጉባዬ ላይ አብን እንደተገኘ ገልጾ በስብሰባው ግን እዚህ ግባ የሚባል ውይይት እንዳልተደረገ ገልጿል። “የዛሬው ውይይት ላይ እኛም ነበርንበት። እዚህ ግባ የሚባል ውይይት አልተካሄደም።……ተስፈኞች ያዘጋጁት የአዳራሽ ውሥጥ ጩኸት ብቻ ነበር! ” ሲል ነው ስብሰባውን የገለጸው።

አብን ስብሰባው ላይ ከተገኘ ስብሰባው ለምን “ፍሬያማ” ስብሰባ እንዲሆን የድርሻዉን መወጣት አልቻለም የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ያም የሆነበት በርካታ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል፡

አንደኛ – ስብሰባው ቅራቅንቦ ድርጅቶችን እነ አየለ ጫሚሶን የመሳሰሉት ያካተተ ሰሆነ ነው። ያ ሁሉ ሰው በተገኘበት ቁም ነገር ያለው ጉዳይ ላይ መናጋገር አይቻልም።

ሁለተኛ – ቢያንስ በአገር ቤት ትልቅ እንቅስቃሴ የሚያደርገው አብንን ወክለው የሄዱ ተወካዮች፣ ተገፍተው ወደ ኋላ ነው የተቀመጡት። ሁለቱም ሌንጮዎች፣ ዶር አረጋዊ በርሄ፣ ፕሮፌሰር በየነ ፣ አየለ ጫሚሶ፣ አቶ መሳፍንት የመሳሰሉትን ከፊት ስናያቸው፣ የአብን አመራሮችን ግን ፎቶ ላይ አይታዩም። አሁን በምን መስፈርት ነው በስድሳዎቹ ጊዜ ብቻ የነበሩ ፖለቲከኞች ከፊት የሚቀመጡት ?፡በምን መስፈርት ነው ዶ አረጋዊ ወይንም ዶር ብርሃኑ ከፊት ቦታ ሲሰጣቸው የአብን ተወካዮች ወደ ኋላ የተገፉት ??? እንዴት ነው ከዉጭ አገር ስለመጡ ነዉን ???? ስለዚህ አብኖች ከኋላ ተቀምጠው እንዴት ነው አስተያየት ሊሰጡ የሚችሉት።

በነገራችን ላይ አብኖችን ብቻ ሳይሆን ብአዴን/አዴፓዎችን አላየኋቸውም። ለምን እንደሆነ የሚነገረን ሰው ቢኖር ጥሩ ነበር።

በኔ እይታ ስብሰባው ፍሬያማ ሊሆን የሚችል የነበረው፣ ስለ ምርጫ ከማወራት በፊት፣ ሁልት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ ትላልቅ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ቢቻል ነበር፡

– በአገሪቷ ሰላምና መረጋጋትን ማስፈኑ አንዱ ትልቅ ጉዳይ ነው። በአሁኑ ጊዜ፣ ዛሬ የተሰበሰቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከኦሮሞ ድርጅቶች በስተቀር ኦሮሞ ክልል(ከአዳማ በስተቀር) በነጻነት መንቀሳቀስ አይችሉም። ጽንፈኛ ቄሮ፣ ኦነጎችና ኦህዴድ/ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ያልተመደመሩ ዘረኞች አይፈቅዱም። እነ ዶር አብይም በኦህዴድ ውስጥ ድርጅታው ዲሲፕሊን ማስፈን አልቻሉም።፡ኦነጎችና ጽንፈኛው ቄሮዎችንም መለማመጣኝ ማባባል ነው የያዙት።

ከነዶ/ር አረጋዊ በስተቀር ሌሎች ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆን የዶ/ር አብይ አስተዳደር ሃላፊዎችም ሳይቀር ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ አይችሉም። የፌዴራል መንግስቱ ትግራይ ክልል መንቀሳቀስ አልቻለም።፡

እንግዲህ አስቡት፣ ከኦሮሞ ክልል 175 ከትግራይ 38 በአጠቃላይ 213 ወይም 40% የፓርላማ መቀመጫዎች በሚገኙበባቸው የትግራይና የኦሮሞ ክልል ተቃዋሚዎች መንቀሳቀስ ካልቻሉ እንዴት ተደረጎ ነው ምርጫ ሊደረግ የሚችለው ???

– የሕዝብ ቆጠራ ውጤት ከተደረገ አሥራ ሶስት አመታት አልፎታል። ያኔ የአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብና የአማራ ክልል ሕዝብ ቁጥሩ በፖለቲካ ውሳኔ ቁጥሩ እንዲቀንስ ተደርጎ እንደነበረ ብዙዎች ይናገራሉ። አሁን አዲስ አበባ ያኔ ከነበረው ስስት እስጥ ትሆናለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው። አዲስ አበባ ዙሪያ ያለው ማህበረሰብ፣ ሸዋ ባጠቃላይ ሕብረብሄራዊ የሆኑ ዜጎች ከስድሳ በመቶ በላይ እንደሆኑ ነው የሚገመተው። በወረዳዎች የሚኖሩ ዜጎች ቁጥር ይለያያል። አንዳንድ ወረዳዎች በጣም ብዙ ሕዝብ እያላቸው፣ ከነርሱ ግማሽ የሚሆን ሕዝብ ብዛት ካላቸው ወረዳዎች እኩል ነው የፓርላማ መቀመጫ ያላቸው።

ሰለዚህ በትክክል የሕዝብ ቆጠራ ተደርጎ፣ ምርጫ ካልተደረገ፣ ከአስራ ሶስት አመታት በፊት በነበረው ቀመር ለምርጫ መፋጠን ትክክል አለመሆን ብቻ ሳይሆን ኢፍትሃዊና ጸረ0ዼሞክራስያዊ ነው።

#EBC

#EBC ሁሉንም ኢትዮጵያውያን የሚያስተሳስር ሀገራዊ ታሪክን በማጐልበት አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስገነዘቡ፡፡

Posted by Ethiopian Broadcasting Corporation on Saturday, February 2, 2019

3 COMMENTS

  1. ግርማ ካሳ
    ስለ አብን ያነሳኸው ሚዛናዊ ነው:: እነዚህ ወጣት ፖለቲከኞች ወደሗላ መገፋት የለባቸውም:: ፊት ካሉት የበለጠ ተከታይ ህዝብ አላቸው:: ባሁኑ ጊዜ ዶክተር ዐቢይን የምንረዳበት እንጂ የሚወቀስበት ጊዜም አይደለም:: መልካም ለመስራት አየጣረ ነው:: እግዚአብሄር ይርዳው::
    ስለ እዴፓ ያለመወከል ያነሳኸው ትክክል አይደለም:: ዐቢይ እኮ የወከለው ኢህአዴን ነው:: ይህ እዴፓንም ይጨምራል:: ከአዴፓም ስሙን የማላስታውሰው የኢህእዴግ ፅ/ቤት ሀላፊ ( አማራ) በቦታው ነበረ::

  2. የኢትዮጲያ ፖለቲካ ትራፊክ መሆን የሚፈልገው ግርማ ካሳ ዛሬ ደግሞ የአዲሱ ብሄረተኛ ድርጅት ተሟጋች ሆኖ ቀርቧል:: የሃገሪቱን ፖለቲካ ባልደረቦቹ እነልደቱ ያኔ በቀመሩት ከፋፋይ የእድሜ ፖለቲካ ለመከፋፈል ለምን በሳል ፖለቲከኞች ተሳተፉ ወጣቶቹ ወደኋላ መቀመጫ ተሰጣቸው ብሎ ይወቅሳል:: ዋናው ነገር ይህንን ተፈላጊ ውይይት ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓ መሪው የሺዋስ ወጣት ሲሆን የሃገራችን ብርቱ ጉዳይ እድሜ ሳይሆን መፍትሄ ሰጭነት መሆኑን ግርማ ሳይገባው ቀርቶ ሳይሆን ያኔ የፓርላማ አባላቱን የሚዘረጥጥበት መድገሙ ነው:: አየለጫ ሚሶ ለምን ተገኘ ላለው የምርጫው ዘመን ገና ስለሆነ ይመለከተዋል የሰራው በደል ካለም በፓርላማ አጋሩ ስለነበር ማስረጃ በማቅረብ ሊተባበር ይገባል:: ለማጠቃላል የተቃዋሚዎቹ ጋር የወቅቱ ውይይት በታሪካችን ያልታየ ትምህርት ሰጭ መሆኑን ከንጉሱ ፓርላማ ዘውዴ በዳዳን መስማት ከጀመርኩበት ጀምሮ ያልታየ ነው ይልመድባችሁ እላለሁ::

  3. Degome Moretew :- you made a mistake about the writer. The writer is Girma Kassa Not Girma Seifu Maru who was the previous Ethiiopian parliament member.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.