ኢ/ር ታከለ ኡማ ለጥቂት ወራት በተቀናጣ የኪራይ ቤት መኖራቸውን ስላረጋገጡልኝ  አመሰግናለሁ!!! 

ስዩም ተሾመ

<<በምክትል ከንቲባነት ከተመደብኩ በኋላ ወደ ተፈቀደልኝ ቤት የቀደሞው ከንቲባ ቤት ማለት ነው ልገባ ስል፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከአሜሪካ አቡነ መርቆሪዮስን አግባብተው ተሳክቶ ሲመለሱ ለእሳቸው የሚሆን ቤት በፍጥነት ለማግኘት ተቸግረው ሳለ፣ ለእኔ ተብሎ የታደሰውና እኔም ልገባበት የነበረውን ቤት መልቀቅ እችላለሁ ብዬ ለአቡኑ እንዲሆን አስረከብኩ፡፡ ለእኔ የሚሆን መኖሪያ መንግሥት #እስኪያሰናዳ_ድረስ ለጥቂት ወራት መንግሥት #የኪራይ_ቤትአዘጋጅቶልኝ ወደዚያ ገባሁኝ፡፡ ነገር ግን የተቀናጣና ከእኔ ሰብዕና ወይም መርህ ጋር የማይሄድ፣ መንግሥትም በአጭር ጊዜ ውስጥ ለእኔ ቤት እስኪያዘጋጅ ድረስ  እንጂ ወጪ ለማውጣት አይደለም፡፡ መንግሥት በተከራየው ቤት በጣም  ለአጭር ጊዜ ቆይቼ ለቀቅኩኝ፡፡ አሁን የምኖረው በመንግሥት ቤት ውስጥ ነው፡፡ …እኔ የፕሮቶኮል ሰው አይደለሁም፡፡ በመርህ ያደግኩኝ  የአርሶ አደር ልጅ ነኝ፡፡>>

ከላይ ያለው ፅሁፍ የሪፖርተሩ #ዮሐንስ_አንበርብር ከኢ/ር ታከለ ኡማ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ የተወሰደ ነው! በዚህ ቃለ-ምልልስ ም/ከንቲባው ባለፈው ሳምንት ያወጣሁትን መረጃ ትክክለኝነት በራሳቸው አንደበት አረጋግጠዋል፡፡
1ኛ) ኢ/ር ታከለ ኡማ ለጥቂት ወራት የተቀናጣና ከእሳቸው መርህ ጋር የማይሄድ የኪራይ ቤት ውስጥ እንደኖሩ ተናግረዋል!!!
2ኛ) ልክ እንደ #እኔ ኢ/ር ታከለ ኡማም በመርህ ያደጉ የአርሶ አደር ልጅ ናቸው፡፡ ልክ እንደ እኔ በጎጆ ቤት ውስጥ ያደጉ ናቸው፡፡ አሁንም ልክ እንደ እኔ በጎጆ ቤት ላደገ ሰው በከፍተኛ ወጪ የተቀናጣ መኖሪያ ቤት መከራያት አጉል መቀናጣት ነው!!

በዚህ መሠረት በጎጆ ቤት ውስጥ ላደገ ሰው በ140ሺህ መኖሪያ ቤት መከራየት ትንሽ አይከብድም?” በማለት ያወጣሁት መረጃ ትክክልና አግባብ ነው፡፡ ይሄንን መረጃ ኢ/ር ታከለ ኡማ በራሳቸው አንደበት ከማረጋገጣቸው በተጨማሪ እንዲህ ያለ ነገር ከሚከተሉት መርህ ጋር እንደሚጋጭ ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን ም/ከንቲባው ይህን እውነታ እንዲናገሩ እኔ ላይ ብዙ ስድብና ማስፈራሪያ ደርሶኛል፡፡ እውነታውን በይፋ እንዲናገሩ ለማድረግ ለአራት ተከታታይ ቀናት ስልኬን ዘግቼያለሁ፡፡ በመጨረሻም ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ እውነታውን በይፋ በመናገራቸው ላማሰግናቸው እወዳለሁ፡፡ ምክንያቱም ግልፅነት የሌለው ስልጣን ለህገወጥ ምግባር ይውላል፡፡ በመሆኑም ትክክልና አግባብ በመሰለኝ ነገር ላይ ምክትል ከንቲባውን ጨምሮ በየትኛውም የመንግስት ባለስልጣን ላይ ትችትና ነቀፌታ እሰነዝራለሁ!!! ሌላው ዕዳው ገብስ ነው!!!

አሚጎስ!!!!

2 COMMENTS

  1. I think the problem is not Takele Uma’s problem.It is the lack of defined rules and regulation regarding provision of accomodation to the city administration officials. Had there been standards set, it would have been easy to control what is going on in this regard. I strongly disagree with the opinion that a guy who came from a poor farmer family doesnot deserve to live in a better standard living condition. So our crticism should focus on whether it is in accordance with the rules and regulation of the city administration or not. Hence, lets have a look at the systemic problems in the administration that creates loop holes for such a kind of abuse not only at the top level but also at various levels of the city administration.

  2. Seyoum Teshome used to act as a liberal analyst. But in the last couple of months he became more and more racist like the ultra nationalists Eskinder Nega and Getachew Shiferaw. But my advice for Seyoum is that he has to refrain himself from indulging himself in such cheap and uncivilized campaigns against the Oromo people. If Seyoum is rational, he must consider himself as an Oromo because he born and grew up in Arsi, Oromia. Most of his friends and family members are in one way or another Oromo.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.