ቬሮኒካ መላኩን ሆኖ ለረጅም ጊዜያት ሲተውን የነበረው ሟቹ ጋዜጠኛ ደምስ በለጠ ነበር

በሞቀ ምጣድ ለመጋገር የቋመጠው ሃይሉ ቢታንያ ቬሮኒካ አይደለም ።

ቬሮኒካ በሚል የፌስቡክ ስም ስለ አማራ ብሄርተኝነት ምክንያታዊና ሳቢ በሆነ መልኩ ስታስነብበን የኖረችው ቬሮኒካ መላኩን ሆኖ ለረጅም ጊዜያት ሲተውን የነበረው እውቁ ጋዜጠኛና ምሁር ደምስ በለጠ ነበር ። ይህን ሁኔታ የሚያውቁት ተስፋዬ ገ/አብን የመሳሰሉ ወዳጆቹም አቶ ደምስ ከማለፉ በፊት ሲናገሩት የቆየ ነገር ነው ።

እናም ቬሮኒካ መላኩ በሚል ስም ስናነበው የቆየነው ደምስ በለጠ ከረጅም አመት ስደት በኋላ ወደ ሃገሩ ኢትዮጵያ መጥቶ ብዙም ሳይቆይ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም በሞት ተለየ ። ቬሮኒካ መላኩ ዳግም ላትመጣ ይህችን አለም ተሰናበተች ። ከዚያን እለት ጀምሮ እንደ ሃይሉ ቢታንያ አይነት የደምስ በለጠን ቬሮኒካ መሆን የሚያውቁ ሚስጥር አዋቂዎች ይህን የተለመደ ስም ለመውሰድ ሽሚያ ጀመሩ በመጨረሻም ዛሬ ሃይሉ ቬሮኒካ ማለት እኔ ነኝ ብሎ አይኑን በጨው ታጥቦ መጥቷል ። ነገርየው በሞቀ ምጣድ ላይ ለመጋገር መሆኑ ነው ። አትልፋ ፈፅሞ ቬሮኒካን ልትመስል አትችልም ።

በመጨረሻም በድንገተኛ ህመም ህይወቱ ላለፈው ደምስ በለጠ ወይም በፌስቡክ ስሙ ቬሮኒካ መላኩ አምላክ ነብሱን እንዲያስባት እንመኛለን ። ሞቷል ብሎ የሰው ታሪክ መስረቅ ያስነውራል ።

ሳተናው
ዋሲሁን ተስፋየ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.