የአፍሪካ መዲና፣ የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን-የህብረ ብሄር ኢትዮጵያዊያን የጋራ የሁላችንም ነች (ነአምን ዘለቀ)

የአፍሪካ መዲና፣ የሁላችንም የኢትዮጵያዊያን-የህብረ ብሄር ኢትዮጵያዊያን፣ የኦሮሞ፣የአማራ፣ የጉራጌው፣ የጋምቤላው’. ወዘተ የጋራ የሁላችንም የሆነች– ርእሰ ከተማችንን አዲስ አበባን የአንድ ብሄር ብቸኛ ርእስት ለማድረግ አሁኑም የሚሯሯጡ ግልሰቦችና ሀይሎች የሚቀሰቅሱት ሰደድ እሳት ሀገርና ራሳቸውንም ሊያቃጥል የሚችል መሆኑን የተገነዘቡ አይመስልም፣

ነገን በሩቁ ማየት የማይችሉ፣ ከረጅሙ የሀገር ሰላም፣ መረጋጋት፣ የሰከነ ዴሞክራሲያዊ ስራአት፣ የህዝብ አብሮነት ይልቅ እለታዊ የፓለቲካ ቁማርና ትርፍ ያሰከራቸው፡ በጎ ራእይም ሁነ እንወክለዋልን ለሚሉት ብሂር እንኳን ሃላፊነት የማይሰማቸው ግልሰቦች እኩይ ድርጊት ህዝብን በመከፋፈል፣ ስጋት እንዲስፋፋ በማድረግ፣ ስላምና መረጋጋት በኢትዮጵያችን እንዳይነግስ ልዩ ተልእኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ይመስላል።

በጣም የሚያሳዝነው ይህ አካሄዳቸው ሰላምና ልማት ለናፈቀው የኦሮሞ ህዝብም ሆነ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ ምንም ሊፈይድ የሚችል አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ለሌላ ዙር ሀገራዊ ቀውስና ክዚያም በላይ ኪሳራ ሊያድርስ እንደሚችል መንግስትም ሆነ ሃላፊነት የሚሰማቸው ወገኖች ሁሉ በቀላሉ ማየት የማይገባቸው እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው።

በዚህ አዲስ አባባ የማን ናት በሚለው በመስከረም ወር የጻፍኩት በድጋሚ አቅርቢአልሁ።

አዲስ አበባ የአዲስ አበባውያን ናት። በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ከሁለት ብሄሮች ወይንም ከዚያ በላይ የተወለዱ የአዲስ አበባ ነዋሪ ኢትዮጵያዊያን የአያት ቅደመ አያቶቻቸው እትብት ጭምር የተቀበረባት ዋና ከተማ ናት። አዲስ አበባ የኦሮሞ፣ የአማራ፡ የጉራጌ፣ የደቡብ ብሄሮች ተወላጅ የሆኑ፣ ወዘተ፣ ኢትዮጵያዊያንም የሚኖሩባት፣ ሁሉም እኩል መብትና ባለቤትነት አላቸው ስንል፣ አይ አይደለም የዚህ ወይንም የዚያ ብሄር የተለየ ባለቤትነት በአዲስ አበባ ላይ አለው የሚሉ የትኛው ዘመን ላይ እንደሚኖሩ ማጠራጠሩ ብቻ ሳይሆን ይህን በብዙ መስዋእትነት የመጣን ለውጥ ከማገዝ ይልቅ እንዲህ አይነት ህዝብን ከስጋት ላይ የሚጥል፣ በማህበረሰቦች መካከል ከአብሮነት ይልቅ መነጣጠልን፡ ከመቀራረብ ይልቅ ጥርጣሬና ቅራኔን የሚያፋፍም ፣ የጋራ መግለጫ ለማውጣት ለምን አስፈልገ የሚል ጥያቄ መጠየቅ የግድ ይላል።

ወቅቱ የሚጠይቀው ስላምን፣ እርቅን፣ ሀገራዊ መግባባትን፣ ብሎም የዶ/ር አብይ መንግስት የጀመረውን ለውጥ ሂደት ማገዝ መሆን ሲገባው፣ እነዚህ ድርጅቶች ይህን መሰል ሰሞኑን የተፈጠረውን አሳዛኝ ሁኔታ የሚያባብስ አቅጣጫ ለመከተል መምረጣቸው በጣም ያሳዝናል። እጅግ አስገራሚም ነው።

የእኛ አቋም ግልጽ ይመስለኛል። በሁሉም አካባቢ ፣ በሁሉም የኢትዮጵያ ማእዘኖች የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ እኩል መብትና ጥቅም እንደ ዜጋ ይኑረው ስንል ኦሮሞ ኢትዮጵያውያን፣ የደቡብ ኢትዮጵያውያን፣ የሶማሌ ኢትዮጵያዊያን፣ የአማራ ኢትዮጵያውያን፣ ከሁለት ወይንም ከዚያ በላይ የተወለዱ ኢትዮጵያውያን ፣ ብሎም ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ሁሉ መብቶች ነጻነቶችና ጥቅም የተረጋገጠባት፣ የክርስቲያን የእስልምና እምነት ተከታዮች የእምነት ነጻነት የተከበረባት፣ አብዛሀነት የተከበረባት፣ የዚህች ምድር ልጆች ሁሉ እንደ ዜጋ እንደ ሰብአዊ ፍጡር፣ ኢትዮጵያዊ በጎንደርም ሆነ በደቡብ፣ በአዲስ አበባም ሆነ በወሎ ፣ በአዋሳም ሆነ፣ በድሬዳዋ እኩል የዜግነት መብቶችና ነጻነቶች የተረጋገጡበት፣ የተከበሩበት ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ማለታችን ነው። ህብረ ብሄራዊ ማንነት ያላቸው (ከሁለት ወይንም ከሁለት በላይ ብሄሮች በላይ ማንነት) ኢትዮጵያውያንም ሆነ ከአንድ ብሄር ወይ ከሌላው ብሄር የተወለዱ ዜጎች በየትኛው አካባቢ እኩል የዜግነት መብቶቻቸው ፣ ጥቅሞቻቸው መከበር፣ መጠበቅ አለበት እያልን ነው።

የብዙ ሚልዮኖች ቤትና ህብረ ብሄራዊ ማንነት ያላትን የሀገሪቱን መዲና አዲስ አበባን የአንድ ብሄር የተለየ ርስት አድርጎ የተለየ የባለቤትነት መብት መስጠት እጅግ ሃላፊነት የጎደለው ነው። ነገ ደግሞ ሌሎች በልዩ ልዩ አካባቢዎች ተንስተው የዛሬ 100 አመት ወይን 500 እመት ይህ የአንተ መሬት አልነበረም፣ “መጤ ነህ፣ ሰፋሪ ነህ” ወዘተ በሚል ህዝቦችን ወደ የማያባራ ትርምስ እንዲያመሩ በለፉት 27 አመታት በየጊዜው የፈነዳውን አሳዛኝና ዘግናኝ የማህበረሰቦች ግጭት የሚያባብስ አካሄድ እንጂ፣ እቺን አሳዛኝ ሀገርና ለመከራ የተፈጠረ ህዝብ በጋራ እንዲኖር፣ መብቱ፣ ነጻነቱና፣ ሰበአዊ ክብሩ የተሟላባት ለሁሉም እኩል ለሆነች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ምስረታ ሂደት የሚረዳ ጤነኛ አስተሳስብ ሊሆን የሚችል አይደለም።

አሁንም የምንለው ከግል ጥቅም፣ ከትናንሽ ድርጅታዊ የፓለቲካ ትርፍ ስሌት ወጥተን ለሁሉም ዜጎችና ማህበረሰቦች አብሮነት፣ ለጋራ ሀገር ፣ ለጋራ የህዝቦች ጥቅም፣ ለሰላም፣ ለመረጋጋት፣ ልዩነቶች በሰለጠነ የዴሞክራሲያዊ ውይይት የምንፈታበት ለተረጋጋ የፓለቲካ ስርአት ምስርታ በጋራ ብንበረታ፣ ብሎም የለውጡ ሃይል የጀመረውን ሂደት ለማገዝ ብንረባረብ የተሻለ ነው በማለት ዳግም ምክር ለመለገስ እወዳለሁ። ይህ አካሄድ ለማንም የማይጠቅም፣ ማንም አትራፊ የማይሆንበት፣ ሁሉ ተያይዞ ወደ ሁለንተናዊ ኪሳራ፣ ብሎም የማያባራ ገሀነም ሊወስደን የሚችል የጥፋት ጎዳና ነው።

ስለዚህ አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን ሁሉ ናት። የአፍሪካም መዲና፣ ኢትዮጵያ የሁላችንም ናት፣ ማንም የበኩር ወይንም የእንጀራ ልጅ የለም።

3 COMMENTS

 1. Why Finfinnee concerns every Oromo?

  1) the first ever Odaa is found to be established in Finfinne (also served as centre right after Odaa Roobaa and Madda Walaabaa reformation)
  2) Because it is at the centre, it did help to forge confederation and unity among hundreds of Gosas of Oromos (it also served as transit location)
  3) the occupation and colonization of Finfinne is the reason why ALL OROMOS have been enslaved (the fall of Finfinne is dark day, and its liberation should mark a new beginning)
  4) there was genocide against Gosas of Finfinnee (there should be an official apology and a day to remember)
  5) thousands of Oromos escaped the genocide and settled in Arsii, Ginda Beret and parts of East Shewa (they have to be resettled in Finfinne).

  Who should be concerned more? An Oromo or some Nafxanyaa settler? Finfinne will be fully liberated.

 2. Sisay Agena sold not only his integrity but also his soul. He became  a historian and an advocate for the rights of the the ex-neftengas overnight, in order to support the ultra nationalists like Eskinder Negaand his colleagues in crimes.  He has sold his integrity and soul for the pieces of bread which he get as leftovers from the ultra nationalists and racists of the Menilik worshippers.

  Sisay Agena gave Finfnne to the Amahara people, the Africans and the whole world, but denied the Oromo people any rights on Finfinne. This is our Ethiopia which treats the Oromo people always racistically. He is one of the main enemies of the Oromo people. But such noises will be helpful fuel for more warming up and strengthening the Oromo people struggles for freedom and emancipation on its own soils.

  A massage to the hooligans of the ESAT tv: 

  The hooligans and pseudo journalists of the ESAT TV claim the savoir of Ethiopia is only G7 and the wise leader are only the arrogant Berehanu Nega and the racist Adergschew Tsege . All other alternatives are nonsense and unacceptable for them.

  ESAT = ENN

  Sisay Agena, the stupid Habtamu Ayalew, the rude and crooked Reyot Alemu, Messay Mekonnen and Ermias Legesse are the worst human being that I have ever confronted. Ermias Legesse is a chameleon who changes his face from time to time. He lives only for his belly. He used to serve the TPLF as a member of OPDO with passion. He was one of the faithful servants of the TPLF.  Since he left the club of the TPLF he has been collecting his daily breads from the Ethiopians around DC. This guy can even sell his souls. Now, such poor individuals without integrity are dreaming that they may influence Abiy Ahmed and Lemma Megerssaa with their poor psychological flattering. This shows how they are desperate und hopeless.

  The campaign of Sisay Agena, Eskinder Nega and their comrades in all fronts is not new. It is just the continuation of their campaigns against the Oromo people in the last 140 years.  They have been attacking Tekle Uma since he swore in as the mayor of Finfinne because he is an Oromo. If someone from Gonder had took the position, we would have never heard such noises. But we need no permission from those mentally retarded like Eskinder to get back Finfinne as an integral part of Oromia. We will get it back by our struggles likewise we librated Eskinder from the bondage the TPLF. Thus, the Oromo people will not strife any more for the special interests. If you don’t want to see the Oromo daughters and sons waking proudly in Finfinne you can leave our city peacefully, otherwise your liberators will teach you soon unforgettable lessons. 

 3. ከወያኔ አገዛዝ በፊት በነበሩት ዘመናት የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይከፋፈል በአንድነት ይኖር እንዳልነበር ሁሉ ዛሬ ግን በጎሳና በጎጥ ተከፋፍሎ እርስ በርሱ በባእድነት እንዲተያይ ስርአቱ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል:: ከዚህ በፊት የአንድ ኢትዮጵያዊን ስም ስንሰማ ከመስማት ያላለፈ ትርጉም እንዳልሰጠነው ሁሉ በአሁኑ ወቅት ግን የሰውን ስም እስከአያት አዳምጠን ከአንዱ ጎሳ ውስጥ መመደብ መቻላችን ራሱ በእያንዳንዳችን ላይ ስርአቱ ተጽእኖ እንዳሳደረብን ያሳያል:: ወያኔ ያጠለቀልን የጎሳ መለዮን አውልቀን በአንድ ኢትዮጵያ ጥላ ስር መሰባሰብ ካልቻልን ውሎአድሮ ለመከፋፈላችን ምስማርና ማገር እያቀበልን መሆናችንን መዘንጋት የለብንም:: በጎሳ መከፋፈላችን ምን አዎንታዊ አስተጽኦ እንዳደረገ ብናስብ ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በስልጣን ኮርቻ ላይ መፈናጠጥ እንዲሁም ለተወሰኑ ግለሰቦች መበልጸጊያና የትምህርት እድል ለማግኘት በር ከፍቶ ሊሆን ይችላል:: ነገር ግን አሉታዊ ጎኑ የበለጠ የከፋ እንደሆነ መገንዘብ አያዳግትም:: የአብዛኛው የሃገሪቱ ህዝብ ህይወት ካለፉት መንግስታት ጋር ሲነጽጸር የበለጠ የከፋ እንጂ የተሻሻለበት ነገር እንደሌለ ለማወቅ አያዳግትም:: በሃገራችን ውስጥ የተለኮሰው የጎሳ ፖለቲካ ሰደድ እሳት ዜጎች በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሰው ሰርተው ለመኖር እንዳይችሉ አድርጓል:: በገጠር የሚኖሩት አርሶና አርብቶ አደሮችም መሬታቸው በኢንቬስትመንት ስም እየተወሰደባቸው የኑሮው ጫና ሲከፋባቸው ከቀያቸው እየተሰደዱ ወደዋናው መዲና አዲስ አበባ መምጣታቸው አልቀረም:: ዛሬ የሃገሪቱ መዲና እንድትጨናነቅ ካደረጓት ምክንያቶች ዋነኛው የጎሳው ፖለቲካ ያመጣው የደህንነት ስጋት መሆኑን ለማወቅ አያዳግትም:; ወያኔ የጀመረውን የከፋፍለህ ግዛ ዘዴ ካልቆመ ይህ ችግር የሁሉንም ዘርፍ መጉዳቱ አይቀሬ ነው:: የዛሬ 40 አመት የደን ሽፋኗ 30% የነበረው ሃገራችን ዛሬ ከዋናዋ መዲና ወደክልል ወጣ ሲሉ ዛፍ ለብርቅ የሚታይባት ገጠሪቱ ኢትዮጵያ ከአለም የአየር ንብረት መቀየር ጋር ተዳምሮ እንደገና በድርቅ የመጠቃት እድሏን ማስፋቱ አይቀርም:: ህዝቡ still በፍርሃት ይሁን ወይንም ትንንሽ ጥቅማጥቅሞች እንዳይስተጓጎሉበት ሃገር ስትፈራርስ ቆሞ ከመታዘብ ይልቅ በቃችሁ ብሎ በአንድነት ቆርጦ ለመነሳት ያደረገው ተነሳሽነት አናሳ ነው:: በርግጥ እንቅስቃሴውን ሊመራ የሚችል አመራር መኖር እንዳለበት ቢታመንም እንዳላየና እንዳልሰማ ሆኖ ማለፍ ግን የኋላየኋላ የሚጎዳው ራሱን ህዝቡን ነው:: በጣልያን ወረራ ወቅት የጣልያን ሰራዊት ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀ ቢሆንም ጀግኖች አባቶቻችን የወራሪውን ጥቃትና የባንዳውን መመሳጠር በመቋቋም የእግር ውስጥ እሳት ሆነው ጠላትን ከሃገሪቱ በማስወጣት ለኛ ትውልድ ነጻ የሆነችውን ሃገራችንን ቢያሰረክቡንም የኛ ትውልድ ግን የነርሱን ፋና ከመከተል ይልቅ ዝም ብሎ መመልከትን መርጧል:: እነዚህ ሃገር አፍራሾችን ማስቆም ካልተቻለ ውሎ አድሮ ውጤቱ አስከፊ እንደሚሆን ለመገመት ነብይ መሆንን አይጠይቅም::
  በርግጥ ሃገራችን በአሁኑ ጊዜ መስቀልኛ መንገድ ላይ ትገኛለች:: አንደኛው መንገድ ወደ መልካም ጎዳና የሚያመራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወደጥፋትና መበታተን የሚወስድ ጎዳና ነው:: በእኩልነት በፍትህና በውነተኛ ዲሞክራሲ ላይ የተገነባች ኢትዮጵያ መስርቶ ሁሉም ከህግ በታች ሆኖ በዘር ሳይከፋፈል የሃገሪቷ አንጡራ ሃብት በግለሰቦች እጅ ሳይመዘበር: አንዱ በውስኪ ሲራጭ ሌላው የሚጎርሰው አጥቶ የማያለቅስባት: ሰው የተሰማውን በመንግስት ላይ ቅር የተሰኘበትን ነገር ለመናገር ለመጻፍና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በነጻነት ያለፍርሃት ለማካሀድ የሚችልባት: መሪዋ በህዝብ: ከህዝብና ለህዝብ አገልግሎት የሚመረጥባት: መሪዎቿ ጋራ እንደናደ ዝንጀሮ በቴሌቭዥን እየቀረቡ በ90ሚሊዮን ህዝብ ላይ የማይደነፉባት: መከላከያው ሰራዊት የገዢውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ሎሌ ሳይሆን ወይንም ህዝብን ለመግደል አፈሙዙን የሚያነሳ ሳይሆን ህዝብን ለመጠበቅ የሚቆም ሃይል የሚሆንባት: ሁሉም ዜጋ በሃገሩ ላይ ሰርቶ የሚያድግባት:ተማሪው ተምሮ ያለአድልዎ ስራ የሚያገኝባት: ሰው ፍርድ ቤት ቆሞ ትክክለኛውን ፍርድ የሚበየንባት: ሰው ከሃገሩ ለነፍሱ ፍራቻ ወደሌላ ሃገር የማይሰደድባት: አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ያልሆነባት ወዘተ…ሃገር ለመመስረት የሚያስችል መንገድ ሲሆን ሌላኛው የጥፋት መንገድ ደግሞ የቀድሞው የመለስ የጭቆና ዘመን ሳይቀየር የሚቀጥልባት: ወያኔ የቀድሞውን አላማውን ከግብ ለማድረስ ሃገሪቱን ለመበታተን ወደኋላ የማይልባት ስሟን ከካርታ ላይ ሊጠፋ የሚችልበት መንገድ ነው:: ነገር ግን አምላክ ከጎኗ ስለሆነና ኢትዮጵያ የጀግና ደሃ ስላይደለች የቁርጥ ቀን ልጆቿ በዘር ሳንከፋፈል ተረባርበን ከአጠላባት አደጋ መታደግ የዜግነት ግዴታችን ነው:: ሃገራችን ኢትዮጵያ ልጆቿን ኑ ትላለች:: ኑ በተግባር ልያችሁ እያለች ትጮሃለች:: ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኽ እንዳይሆንብን እግዚአብሄር ይርዳን!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.