ትንሽ ምክር ለህወሃት ባለሥልጣናት

ህወሃት በትግሉ ዘመን ከሱዳን ትግራይ እንደ መዳረሻ መንገድ የኋላ ኋላም ትግራይን ሲገነጥል ለሱዳን በሰጠው መሬት እየተንጎማለለ እታች ቤንሻንጉል ድረስ በመቆጣጠር አባይ ግድብን ለንዋየ ጥቅም ለማዋል በማሰብ ወቃይጥ ጠገዴን ከአማራው ጎንደር ሕዝብ ነጥቆ ወሰደ። ይህን በመቃወም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማሮች ሲገደሉ በርካቶች ተሰደዋል፣ ታስረዋል፣ ግፍ ተፈጽሞባቸውል፣ ተፈናቅለዋል። ተጋዳዮቹ ደደቢት በነበሩበት ወቅት ባልበሰለ ጭንቅላት የወጠኑት ይህ ስህተት የትግራይ ሕዝብን እጅግ አስቸጋሪ የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት የተሳሳተ ውሳኔ ለመሆኑ የዛሬው ተጨባጭ ሁኔታ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ቀድሞ ኢሕዴን (ኢትዮጵያ ሕዝብ ደሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ስሙን ለውጦ ደግሞ ብአዴን (ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) የተባለው ድርጅት አማራን ፈጽሞ የማይወክል ይልቁንም አማራን ለማጥፋትና ለማምከን የተጎነጎነ የደደቢቱ ወፍራሙ የሴራ ጅራፍ ነው። ብአዴን የበላይ አመራሮቹ አማራ ያልሆኑ የወያኔን ስውር ፍላጎት ለመፈጸም ቃል የገቡ የግፈኞች ስብስብ ነው። ብአዴን የህወሃት ወታደራዊ ክንፍ ነው። የድርጅቱ አባሎቹ አብዛኛዎቹ ትግራይዋዎች ቢሆኑም ኤርትራውያንም አሉበት። ብአዴን አወቃቀሩ የናዚው ሄንሪክ ሂምለር ከሚመራው ቫፈን ኤስ ኤስ (Waffen-SS) ጋር ሳይመሳሰል አይቀርም። ቫፈን ኤስ ኤስ ዋናው ተልዕኮ ከጀርመን ውጭ የሚገኙ ሃገሮችን እየወረረ የጀርመንን ዘረኝነት ፖሊሲ ማስፈጸም ሲሆን ብአዴንም በአማራው ክልል ላይ ተሰማርቶ የህወሃትን የዘረኝነት ፖሊሲ የሚተገብር ድርጅት ነው። የጀርመኑ ቫፈን ኤስ ኤስ መሠሪነትን የተካኑ አባሎች ነበሩት። ብአዴንም አማርኛ መነጋር የሚችሉ የአማራውን ሥነ ልቦና የተላበሱ አድፋጭና ሴራ ጎንጓኝ አባላቶችንም አቅፏል። የጀርመኑ ኤስ ኤስ በደፈጣና በስውር ዘዴ አባላቱን ማስወገድ እንደሚችል ሁሉ ብአዴንም ያልፈለገው ላይ ሁሉ ስውር ጥቃት መፈጸም የሚችሉ ከልጅነት እስከ እውቀት ክፋትን የለበሱ አባሎች አሉት።

ዛሬ ሁሉም ነገር በፍጥነት እየተለወጠ ነው። ተራማጁ ብአዴን መሰሪ አባሎችን በግልጽ እያስወገደ አማራነቱን እየተቀባ ነው። አማራው መሰሪውን የብአዴንን አመራር እንትፍ ብሎ ነጻነቱን በማስመለስ ደረጃ ላይ ደርሷል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ጭቆናን፣ ሙስናን፣ ዝርፊያንና ሌብነትን በክንዱ እየደቆሰ ቀስ በቀስ የብልግናውን ሥርዓት እያፈራረስው ይገኛል። ለይስሙላ የተቀረጸው ህገ መንግሥትም በተለይም ደግሞ የራሱ ተወካይ የሌለውን አማራ ነጥሎ ለመምታት የተዘጋጀው ህገ መንግሥትም በአዲስና ሃገራዊ መልክ እንዲሻሻል ብዙዎች ሃሳብ እየሰጡ ነው ።

ስለዚህ ጉዳይ ብዙ ስለተጻፈ ምንም አዲስ ነገር አላመጣም። ህወሃት ቢሰማኝ አንድ ነገር ብቻ ለማለት እፈልጋለሁ። ህወሃት ትልቅ ችግር ተሸክሟል። ህወሃት ችግሩ የአስተሳሰብ ድህነቱ ነው። ህወሃት አስተሳሰቡን ማሳደግ አልቻለም። እንደውም የህወሃቱ ቱባው ባለስልጣናት አሰሳሰባቸው አንዳች አልተለወጠም። አስተሳሰባቸው ከግሎባላይዜሽኑ ጋር ሊራመድ ቀርቶ ራሱን የደደቢቷን ትንሿን መንደር መሻገሩ ያጠራጥራል። ህወሃቶቹ ፖለቲካ ተለዋዋጭ መሆኑን ፈጽሞ አልተረዱም። ህወሃቶች አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚለው የሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት የሌብነት ሥርዓትን እንደዘላለማዊ ሥርዓት ያመልኩታል። ይህ የማኦ ቁንጽል ሃሳብን ያዘለው ትንሽ እውቀት ነው እውስጣቸው ተደንቅሮ አዙሮ እንዳያዩ አንገታቸውን ያፈረጠመው። እኔ እንደሌሎቹ ተስፋ ሳልቆርጥ ህወሃትን ትንሽ ምክር ልለግሰው።

ህወሃቶች እባካችሁ ራሳችሁን በጡረታ አግልላችሁ ለምስኪኑን የትግራይ ሕዝብ ነጻነቱን መልሱለት። አያይ – አያገባችሁም፣ በክልላችን ያለውን ጉዳይ ለኛ ተዉልን ካላችሁም በኃይል የያዛችሁትን የጎንደሩን ወልቃይጥ ጠገዴና ወሎ ራያ የመሳሰሉትን የአማራውን መሬት ለአማራው ተዉለት። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ነገ ለሚከሰተው ትንቅንቅ እናንተስ ግድየለም በልታችኋል፣ በናንተ ምክንያት ምስኪኑን የትግራይ ህዝብ ግን ጭንቀት ውስጥ ቢገባ እጅግ ያሳዝናል። አማራው ቢቻል በውድ ካልሆነም በትግሉ መሬቱን ማስመለሱ አይቀሬ ነው። ማስተዋል ከቻላችሁ ዛሬውኑ የአማራውን መሬት ኮሽ ሳይል ለቃችሁ ልዩ የምትሉትን ዘረኛ የፖሊስ ኃይላችሁን አስወጡ። ውድ ህወሃቶች! ይህን ምክሬን ብትሰሙ ትጠቀማላችሁ እንጂ አትጎዱም። እባካችሁ ምክሬን አትናቁ። አምባገነን ገዥዎች ነገን የሚያዩበት ዓይናቸውን ምቾት፣ ገንዘብና መዝናናቱ ይጋረዳል። እካችሁ ህወሃቶች ዓይናችሁን የጋረደውን ስንክሳር አሽቀንጥራችሁ ጥላችሁ የክብር ሞት ሙቱ። ዛሬ የሕዝብ ኃይል እምን ደረጃ ላይ እንደደረስ ቆም ብላችሁ አስተውሉ። እባካችሁ ምክሬን ስሙ። ታላቁ ገዥ አብዲ ኢሌ ራሱ የድሆችን ምክር ቢሰማ ኖሮ ከዛሬው ውርደቱ ይድን ነበር። ህወሃቶች እባካችሁ ደሃ ነው ብላችሁ ምክሬን አትናቁ። የአማራውን መሬት እባካችሁ ለአማራው ተዉለት። አመሰግናለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

በየነ ከበደ

2 COMMENTS

  1. እባክህን ከቻልክ የድንበሩን ጉዳይ ታሪክ አምብበህ ተረዳው ገና ወደ ትግራይ የሚመለስ መሬት አለ። ስለ ህወሓት ምክር ላነሳሃው ጉዳይ ህወሓት በእንደ አንተ አይነቱ ከንቱ የሚመከር ድርጅት አይደለም በህዝቡ እና በአባላቱ እንጂ። ህወሓት ይህን ግማታም አፍህ በነፃነት እንድታወራበት ያደረገህ ድርጅት ነው። የምታደርጉትን እናያለን ጦርነቱ እኛም ናፍቆናል ተሎ በጀመራችሁት.ሀሀሀሀሀሀሀሀ።

  2. ye hewehat cheger weyem dekamanet yetayebet mert lewt b/c neger ketekeyer behuala bomb mafendat masheber lela neger memoker gezuf sehtet new .mehon yeneberebet erasen mermero selamawi tegelen memoker neber.yehe yeahunu lewt abiy seletemerete aydelem yemetam enante meshashal selalchalachehu new.mesrek.megdel betakomu ena yehezb mengest betadergut hulem be ethiopia tarik west telek bota yenorachehu neber .mastekakeyachehu lemetewekelut le tegray hezb lesera yemifelegewen material amualto beseraw endibereta erdut kelash tekem yelewem

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.