ኢትዮጵያ ወደ ጥልቅ ጉድጓድ እየሰጠመች የምትገኘው በጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ጥንካሬ ሳይሆን በአፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ወኔ አልባነት ነው! (እያሱ ወልደ-ነጎድጓድ)

ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችን  በቁጥር አንድና ሁለት ብለን በቀላሉ ልንቆጥራቸው እንችላለን፡፡ ነገር ግን እነዚህ ጸረ,ኢትዮጵያ ኃይሎች በአፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ድክመት ምክንያት ብዙ ተከታይ እፈሩ መጥተዋል፡፡

በአፍቃሪ ኢትዮጵያውያን እና በጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች መካከል ያለው ትልቁ ልዩነት ቁርጠኝነትና ይሉኝታ ነው፡፡

ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ  24 ሰዓት ሙሉ ለጉልበታቸው፤ ለእውቀታቸውና ለገንዘባቸው ሳይሰስቱ ተደራጅተው ሌት ከቀን ይሰራሉ፡፡ለዚህ እኩይ ተግባራቸው መሳካት ሲሉ በዋናው ግባቸው ላይ እስከ ተመሳሰሉ ድረስ ጊዜያዊ ልዩነታቸውን የማስተናገድ ችሎታቸው ከፍተኛ ነው፡፡ ሻዕቢያ፤ ህወሓትና ኦነግ ሁሉም የግል ግብ ቢኖራቸውም ሁሉንም አንድ የሚያደርጋቸው ግን ኢትዮጵያን ማፍራረስ ነበር፡፡ ስለሆነም በአንድነት ኢትዮጵያን ለመበታተን በትጋት ሰርተዋል፤አሁንም ኦነግና ህወሓት እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ለዚህም ክፉ  ተግባራቸው ያግዛቸው ዘንድ የኢትዮጵያን ህልውና ከሚፈታተኑ ሓይሎች ጋር ለምሳሌ ከሱማሊያ፣ ከሱዳን፤ ከግብጽና ከሌሎች የአረብ ሀገሮች ጋር ተባብረው ሰርተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ልዋላዊነት በ1969 ዓ.ም  በሶማሌ  ሲደፈር ከሲአድባሬ መንግስት ጋር አብረው በባንዳነት ኢትዮጵያን ለመበታተን ሌት ከቀን ሰርተዋል፡፡

ህወሓት አሁንም ከሱዳንን ጋር በመሆን የምዕራብ ኢትዮጵያ ዳር ደንበራችንን በተደጋጋሚ እንዲደፈር እድርጓል፤መሬታችንን ያለህዝብ እውቅና አሳልፎ ሰጥቷል፤ ከአሸባሪው አልሸባብ ጋር በመሆን ምስራቅ ኢትዮጵያን ዛሬም  በማተራመስ ላይ ይገኛል፡፡ ለዚህ ጸረ-ኢትዮጵያ ግቡ ይረዳው ዘንድ ለ27 ዓመት  ሙሉ ሀገሪቱን በመዝረፍ በአሁኑ ወቅት  ኢትዮጵያ በአጽሟ  ብቻ  እድትቆም አድርጓል፡፡ በዘረፈው የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሀብት ሀገሪቱን እያተራመሰ ይገኛል፤ይሕን እኩይ ምግባሩን ለማስቀጠል ከበቂ በላይ ተዘጋጅቷል፡፡

የህወሓት እኩይ ምግባር ባልደረባ የሆነው ኦነግም ኢትዮጵያን ለመናድ ያለ የሌለ አቅሙን ተጠቅሞ እየሰራ ይገኛል፡፡ ለ40 ዓመት ሙሉ አንድ ቀበሌ በውጊያ መቆጣጠር ተስኖት የኖረ ድረጅት የሠላም ጥሪ ተቀብሎ ከመጣ በኋላ ግን ትጥቅ አልፈታም በማለት ህዝብ ሲገድል፤ሲያፈናቅል፤ ሲያሸብረና የሀገር ሀብት ሲዘርፍ እየተመለክትን ነው፡፡ ኦነግ ከህወሓት በተማረው ሀገርን የመዝረፍ  አጸያፊ ምግባር ወደ ኢትዮጵያ  ከመጣ ገና ግማሽ ዓመት  ሳይሞላው 18 የንግድ ድረጅቶችን ዘረፏል፡፡ አዲስ አበባ ላይ መንግስት የሰጠውን ቢሮ እየተጠቅመና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን  ተቀምጦ ምዕራብ ኢትዮጵያን በጦርነት እያመሳት ይገኛል፡፡

እጀግ የሚያሳዝነው  ኢትዮጵያ በበጀት እጥርት እስትንፋሷ ሊያቆም እየተንገዳገደች ባለችበት ወቅትና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን  እርዳታ እየጠየቅች ባለበት አስከፊ ወቅት ላይ ነው ኦነግ የምዕራብ ኢትዮጵያን ባንኮች እየዘረፈ የሚገኘው፡፡

የአቢይ መንግስትም ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎችን  በመለማመጥ ይበልጥ የልብ ልብ እንዲሰማቸውና የኢትዮጵን ህልውና እንዲፈታተኑ እያደረገ ይገኛል፤ በተለይ ኦነግን የያዘበት አካሄድ በእጅጉ አሰፈሪ በመሆኑ በየመድረኩ ለሚያካሄደው ስብከት ከማጨብጨብ ተቆጥበን መሬት ላይ እየዘራ ያለውን የማይጠፋ አሜክላ በአንክሮ ልንገመግም ይገባል፡፡ ለህወሓት በየመድረኩ ስናጨበጨብ በመኖራችን ምትክ  የሌላት ሀገራችንን ጉድገዋድ ውስጥ እንድትገባ አድርገናል፡፡ከዚህ ልንማር ግድ ይለናል፡፡

በተቃራኒው ኢትዮጵያን እናፈቀራለን የሚሉ አካላት ግልጽ  የሆኑ መሠረታዊ ችግሮች ይታይባቸዋል፡-  ወኔ አልባነትና ይሉኝታን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡

አብዛኛዎቹ አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ችግር ጥልቅና በቀላሉ የማይፈታ መሆኑን እያወቁ  ችግሩን የሚመጥን አደረጃጀትና የሚጠይቀውንም መሰዋትነት ለመክፈል ዝግጁነት አይታይባቸውም፡፡ የኢትዮጵያ ችግር በመድረክ ድስኩር ብቻ የሚፈታ አለመሆኑን ይገነዘባሉ ነገር ግን ለሁለተኛው አማራጭ ወኔ ይከዳቸዋል፤ አንድነት ያንሳቸዋል፡፡እንወዳታለን ለሚሏት እናት ሀገራቸው ገንዘባቸውን፤ ጉልበታቸውንና ህይወታቸውን መሰዋት ለማድረግ አይፈልጉም፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶችም ይሕን ክፍተት ስለሚገነዘቡ በይፋ ኑ ጦርነት ግጠሙን በማለት ሲፎክሩ ኑረዋል፡፡ ጥቂቶቹ ጸረ-ኢትዮጵያ ኃይሎች ብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ሲያሰሩ፤ ሲያሳድዱና ሲገድሉ ኑረዋል፡፡

አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ካላቸው የህዝብ ቁጥር ብዛት አንፃር በአንድትና በቆራጥነት /በወኔ ቢንቀሳቀሱ አይደለም ባንዳዎቹ ህወሓትና ኦነግን ሌላ ኃይል ሊቋቋማቸው አይችልም ነበር፡፡ በተጨማሪም አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን ለማፈረስና ኢትዮጵያን ለመታደግ አሉታዊና አዎንታዊ አስተዋፆ ባላቸው ኃይሎች መካከል ያለውን የኃይል አሰላለፍ በሚገባ ያለመለየት ችግር በብዛት ይስተዋልባቸዋል፡፡

የአፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ሌላው ችግራቸው ይሉኝታ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ መውደቅ የጀመረው ከደረግ ጊዜ ጀምሮ ነው፡፡ ደረግ ለሀገር በነበረው ከፍተኛ ፍቅር ለ17 ዓመት ከባንዳወቹ ጋር ሲፋለም የህወሓት ሰዎች የደርግ ባለስልጣን ሁነው በሁለት ቢለዋ ሲበሉ አብዛኛዎች አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን ያውቁ ነበር፡፡ ህወሓት ያለምንም ታሪካዊ ማስረጃ ወልቃይትንና ራያን የትግራይ አካል ናቸው ሲልና በኃይል ወደ ትግራይ እንዲጠቃለሉ ሲያደርግ የአማራ ምሁራንም ሆነ ሌሎች ከሶስት አመት በፊት ጠንካራ ነው የሚባል ማስረጃ አቅርበው በአደባባይ አልተከራከሩም፤ የህወሓትን ትዕቢት የሚያስተነፍስ አደረጃጀትም ለመፍጠር አልሞከሩም፡፡ለዚህም ይሉኝታ፤ ራስ ወዳድነትና  ወኔ አልባነት እንደምክንያት ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡

ህወሓት ለ27ዓመት ሙሉ በልማታዊ መንግስት፤ በብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት እና በዴሞክራሲ ስም እቀለደ ሀገር ሲገድል ከጥቂት ቆራጥ ኢትዮጵያውያን በስተቀር አብዛኛው የኢትዮጵያን አንድነት እደግፋለሁ ባዩ ቡድን በይሉኝታ ወይም በፍርሃት ቆፈን ውስጥ ተዘፍቆ በመኖሩ አሁን ኢትዮጵያ ለምትገኝበት አሳሳቢ ደረጃ መድረስ የራሱን አሉታዊ አስተዋፆ አድርጓል፤ በተለይ በአንድነቱ ጎራ የሚገኘው አብዛኛው ምሁራን በራስ ወዳድነትና ስግብግብነት ላይ አተኩሮ ሲንቀሳቀስ ለመኖሩ ዋቢ የሚሻ አይመስለኝም፡፡

አሁንም አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን በሌላ ይሉኝታ ተጠርንፈው ይገኛሉ፡፡ የአቢይን መንግስት አካሄድ በአንክሮ በመገምገም ጉድለቱን እንዲሞላ መሞገት ሲገባቸው መሬት ላይ የማይታይውን የአቢይን የመድረክ ድስኩር ብቻ በማዳመጥ  ሀገራቸው በፍጥነት ወደ ጉድጓድ እየሄደች ባለበት ወቅት ዝምታን መርጠዋል፤ግሚሶችም የአቢይ/ኦዴፓ አካሄድ አደጋው እየታያቸው አይመስልም፡፡ ይባስ ብሎም አቢይን አትተቹ፤ አቢይ  ከሰማይ የተላከ ነው ብለው እስከ ማምለክ የደረሱ  አልጠፋም፡፡ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ከህወሓት ዘመን በበለጠ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መግባቷ ነው፡፡

በአጭሩ  አፍቃሪ ኢትዮጵያውያን  ለእናት ሀገራቸው የሚፈለገውን መሰዋትነት ለመክፈል ባለመዘጋጀታቸው ምክንያት የባዳዎቹ ቡድን የኢትዮጵያን ህልውና  በከፍተኛ አደጋ ላይ እየጣለው ይገኛል፡፡ አፍቃሪ ኢትዮጵያንም የትግል ስልታቸውን በፍጥንት ቀይረው ለሀገራቸው መሰዋት ለመሆን ካልተዘጋጁ በስተቅር ኢትዮጵያችን አይናችን እያየ  በቅርቡ ልታመልጠን እንደምትችል ልንጠራጠር አይገባም፡፡ኢትዮጵያችን ከመፍረስ የምትተርፈው በሕይዎት መሰዋትነት እንጅ በመድረክ ላይ ድስኩር አይደለም፤ አልነበረምም፡፡

 

4 COMMENTS

 1. Your discourse is good for nothing. I wonder why you lay about Wolqayit Tsegede, Metekel , Dera and Raya. AAPO has protested ever since 1992 against the illegal occupation of these Amhara lands. Why so many Amharas who were members of AAPO were killed by TPLF? The late Prof. Asrat Woldeyes, the president of AAPO, was jailed and he was not allowed to get medical treatment timely and properly during his imprisonment. Then he died and many of his groups languished in prison. Either ignoring or denying this fact why are you writting such a very nonsense article ? i can say that you’re realy a wolf in sheep’s clothing.
  Derbi

 2. Your discourse is good for nothing. I wonder why you lay about Wolqayit Tsegede, Metekel , Dera and Raya. AAPO has protested ever since 1992 against the illegal occupation of these Amhara lands. Why so many Amharas who were members of AAPO were killed by TPLF? The late Prof. Asrat Woldeyes, the president of AAPO, was jailed and he was not allowed to get medical treatment timely and properly during his imprisonment. Then he died and many of his groups languished in prison. Either ignoring or denying this fact why are you writting such a very nonsense article ? i can say that you’re realy a wolf in sheep’s clothing.
  Derbi

 3. Thank you for your clear and straightforward points of view that is rarely touched by others. Yes, you are absolutely right that it is terribly disappointing for this generation to be the very captive of crying, decrying, blaming, complaining about things that are going wrong , and condemning (accusing ) those whose agenda and behavior have been very clear for a long time and continue to be so at this very moment too. Yes, it is very difficult to understand why this generation is not still willing and able to learn from
  its own painful weaknesses of a very long and long time .
  A generation that is not willing and able to read its own self- inflicted wound and try to heal it by figuring out the right way and means of treatment will never go any where !
  A generation that is a victim of not dependent and uncritical way of thinking will never move forward meaningfully ! Yes, a generation that is accustomed to voicing back the very rhetorical deliberation of politicians just like an echo will never step forward meaningfully !
  Hopefully , we may do much better sooner, not later!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.