ሙስጠፋ ኡመርና ለማ መገርሳ! ኦብነግና ኦነግ! (ሰርፀ ደስታ)

ነጥቦች

 • ሙስጠፋ ኡመርና አጋሮቹ የሱማሌ ክልልን ሕዝብ አልፎም የኢትዮጵያን ሕዝብ ተስፋ እየሆኑት ነው
 • ለማ መገርሳ አሁን ላለው ለውጥ የከፈለው መስዋዕትነት ከላይ ስለተሰጠው እንጂ ሊታመን የሚችል አልነበረም!
 • አብይና ለማ በኢትዮጵያውያን ሁሉ ሲወደዱ በኦነጋውያን-ሕዋሕታውያን ጥምር ቡድን እደጠላት ነው የሚታዩት እነሱን ለማጥፋት የማይቆፍሩት ጉድጓድ የለም
 • ሙስጠፋና አጋሮቹን የሱማሌ ሕዝብና ለዘመናት ለነጻት የታገለው ኦብነግ በፍቅር አብረው ለመስራት ሲሰማሙ ኦሮሞን አልፎም ኢትዮጵያን ከጉድ ያወጣው ለማን ኦነግና ደጋፊዎቹ እጅግ ፈርተውታል ይጠሉታልም፡፡
 • ኦብነግ በእርግጥም ዓላማው የሕዝብ ነጻነት እንደሆ የሚያሳይ ውሳኔ ሲወስን ለዘመናት በኦሮሞ ሕዝብ ሲቆምር የኖረው ኦነግ ከወያኔ ጋር ጥምር ፈጥሮ ዛሬም ችግር እየፈጠረ ነው፡፡
 • የሰሞኑ የአዲስ አበባ ውዝግብ ችግር አዲስ አበባን ፊንፊኔ በሚል ተለዋጭ ሥም መስጠት ላይ ነው የሚጀምረው፡፡ አዲስ አበባ በብዙሀን የታወቁ ሁለት ሥሞች አሏት፡፡ አዲስ አበባና ሸገር፡፡ ፊንፊኔ ከጅምሩ ኢትዮጵያን እናፈርሳለን ብለው የተነሱ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚጠቀሙበት ሥም ነው፡፡ አዲስ አበባ በኦሮምኛ ማን እንደምትባል ለማወቅ የፈለገ የአካባቢውን ነዋር የሸዋን ኦሮሞ ዘፈኖር ሳይቀር ማድመጥ ነው፡፡ የኦነገግ-ወያኔ ጥምር ቡድን ዋነኛ አላማ የአገርን መሠረትና ታሪክን ከማውደም ጋር ስለሆነ ዛሬ ላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይም የኦሮሞን ሕዝብ ከታሪካዊ ተሳትፎው አውጥተው የባዘነ በማድረግ ለሚፈልጉት አላማ እየተጠቀሙበት ነው፡፡ ሁሉም ወደራሱ ተመልሶ ማስተዋል የጀመረ ጊዜ የኦነግ-ወያኔ ጥምር ቡድን ያበቃለታል፡፡

አንዳንዴ ብዙ የምትከታተለው ጉዳይ ፍንተው ብሎ ይታይሀል፡፡ ሙስጠፋ ኡመርን በአንድ ወቅት በኦኤምኤን ከደረጄ ሐዋዝና ግርማ ጉተማ ጋር እነሱ ጋብዘውት ሲናገር ነበር በደንብ ማን እንደሆነ የገባኝ፡፡ በዛ ውይይት የደረጄና ግርማ ምልከታን መሬት ጥሎት ነበር፡፡ እንደመሰለኝ እነሱ የጋበዙት እንደነሱ እንዲያወራና እንዲሳተፋቸው ነበር፡፡ ሙስጠፋ ግን ግልጽና አእምሮው ለአመክንዮ(ሎጂክ) የተገዛ ስለሆነ እንደነሱ ሊሆን አልቻለም፡፡ በዚህ ላይ በጣም በሳል ነው፡፡ የኦሮሞን ፖለቲካ የሰፈር ጫዋታ ያደረጉት እነ ደረጄ፣ ግርማ፣ጀዋር፣ ጸጋዬ ሌሎችም የተለመዱት የኦኤምኤን ቡና ጠጪዎች እንደ ሙስጠፋ ያለ በሎጂክ የበለጸገን ሰው መጋበዝ ራስን ማጋለጥ አንደሆነ አላሰቡበትም ነበር፡፡ በእነሱ ቀመር ሙስጠፋ እንደነሱ የጥላቻና ዘረኝነትን ፕሮባጋንዳ በመንዛት ሕዝብን ለማወር የሚጠቀም ሀሳብ ያመጣል ብለው ነበር፡፡  ጭራሽ ሙስጠፋ ተጨቁኛለሁ ብለህ ካሰብክ በታሪክ መጨቆን አለመጨቆንህ እውነታነት ሳይሆን ራስህ በፈጠርከው የተጨቁኛለሁ ስሜት ነው የምትኖረው ብሎ የኦሮሞን የ50ዓመት እንቆቅልሽ የሆነን የነጻነት ሮሮ በተዘዋዋሪ ነግሯቸው ነበር፡፡ በቃ በዛ ቃለ ምልልስ ነበር ሙስጠፋን ግልጽ ማንነቱን ያቅኩት፡፡ ከዛ በፊት አላውቀወም፡፡ ከዛ በኋላ ግን አንዳንድ የጻፋቸውን ነገሮች ሳነብ ግምቴን አጠናከረልኝ፡፡ የዙማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሆኖ ሲሾም በጣም ነበር ደስ ያለኝ፡፡ በቃ ሱማሌ ነጻ ወጣ አልኩኝ! አንድ ራጆ የተባለ የሱማሌ ክልልን ጉዳይ የሚያቀርብ ፔጅ እከታተላለሁ፡፡ አንዳንዴ አላስፈላጊ ነገር ይፅፋሉ በአብዛኛው ጥሩ ናቸው፡፡ እና እንዲጠነቀቁም አስተያየት የሰጠኋቸው ጊዜ አለ፡፡ ስንት አመት የተበላሸን ነገር በአንድ ጀምበር እንዲሰራ የመፈለግና ስሜታዊ መሆን በሙስጠፋ ላይ ጫና የፈጠረበት ጊዜም ነበር፡፡ አሁን ጥሩ ነው፡፡ እንደገባኝ ራጆም ተደስተዋል፡፡ ሰሞኑን በሱማሌ እየሆነ ያለው ብዙ ለውጥ ነው፡፡

እንግዲህ ይሄ ገና ከተመለከትኩት ጀምሮ የገባኝ ሙስጠፋ ዛሬ ለሱማሌ ክልል እንዲሁም ለኢትዮጵያ ትልቅ ታሪካዊ ክስተትን አስተናግዷል፡፡ የኦብነግን በሰላማዊ መልክ እንዲታገልና የለውጡ አካል ሆኖ ክልሉን አልፎም በአገሪቱ የሚኖረውን ልማታዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጥረት እንዲሳተፍ ከክልሉ መንግስት ጋር መስማማቱ አንድ ነገር ነው፡፡ በአፉት በረካታ ዓመታት በሕዝብ ላይ ግፍ ሲፈጸሙ የነበሩ የክልሉ ባለስልጣናት ያለመከሰስ መብትን ማስነሳትም ሌላ ነገር ነው፡፡ ሙስጣፋን ዛሬ የሱማሌ ክልል ሕዝብ ብቻም ሳይሆን መላው ኢትዮጵያውያን ሰፍ ብለው ነበር ያደመጡት፡፡ “በህግ የሚፈለግ ተጠርጣሪን ደብቆ አልሠጥም ያለው የእኛ ክልል አይደለም። የፌዴራል ፓርላማ ያወጣውን ህግ አልቀበልም ያልነው እኛ አይደለንም። የመገንጠል አጀንዳ ይዘንም የምንቀሳቀሠው እኛ አይደለንም። ምናልባት ሊገነጠሉ የሚፈልጉ ሀይሎች ብቻቸውን ሲገነጠሉ ብርድ ብርድ እንዳይላቸው ሡማሌ ክልልም አብሯቸው አጀንዳውን እንዲያራግብ ይፈልጉ ይሆናል። ግን አይሳካላቸውም።”  ከላይ የጠቀስኳቸው እነ ደረጄና ግርማ ሱማሌን እነሱ ከተጨቆኑና ከኢትዮጵያ ነጻ መውጣት ከሚፈልጉ ነው ብለው ነብር ሙስጠፋን የጋበዙት፡፡ ዛሬ ሙስጠፋ የተናገረው ብዙ ሰው የሙስጠፋ ብቻ ይመስለዋል፡፡ እውነታው በአብዛኛው የሱማሌ በተለይ የተማሩት የሚጋሩት ሀሳብ ነው፡፡ ይሄ የኦሮሞን ፖለቲካ በዋናነት ከሚዘውሩትና ወደ የሕዝቡን አስተሳሰብ ወደ አዘቅት እየከተቱት ከአሉት ኦነጋውያን እጅግ የሚጻረር ነው፡፡ ኦብነግና የሱማሌ ክልል መንግስት ለመደራደርም ሆን ለመስማማት ብዙ ውጣውረድ አለስፈለጋቸውም፡፡ ዓላማቸው ከሕዝባቸው ጋር የነበረን በደል ለማስቆም እንጅ ለራሳቸው ንግድ ስላልነበር፡፡ ሕዝብ ሠላም ሆኖ ዛሬ ሲያዩ ይሄን ለዘመናት የታገሉለትን በደስታ ለመሳተፍ ኦብነግ አላቀማማም፡፡ ጥሩነቱ ደግሞ የሶማሌ ፖለቲክስ የተያዘው በሳል በሆኑ ሰዎች መሆኑ ነው፡፡ እንደ ኦሮሞ አሁን ላይ ደግሞ እንደ አማራ ማንም የሚቆፍረው አደለም፡፡ የኦሮሞ ፖቲክስ ለይቶለታል፡፡ አሁን ላይ የአማራ ፖለቲክስ እየሄደበት ያለው ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ነው፡፡ በሚቀጥሉት 5 ዓመት አማራም እንደኦሮሞ የጥላቻና ዘረኝነት መርዝ በብዛት እንደሚበክለው አትጠራጠሩ፡፡ አሁንም ቀላል የሚባል አደለም፡፡  የሱማሌ ክልል አሁን በአለበት ሁኔታ ከሌሎች በተሻለ በሳልና የሰከኑ ሰዎች የሚመሩት ፖለቲካ የሚስተናገድበት ነው፡፡ በእርግጥም ሱማሌ በብዙ መከራ ብዙ ጠንካራ ሰዎች እየወጡበት ይመስላል፡፡  እንግዲህ ከሰማሁት ቀን ጀምሮ የት ሊደርስ እንደሚችል የታሰበኝ ሙስጠፋ ከመሰል የክልሉ ተወላጆች ጋር ለክልሉ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያም ትልለቅ ተስፋ እየሆነ ይመስላል፡፡ ሕዝቡና አጋሮቹም እንደሚተባበሩት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

በተመሳሳይ ገና ወደ ስልጣን ሲመጣ የታየኝ ሌላ ሰው ለማ መገርሳ ነበር፡፡ ለማን እኔ ያየሁት ኢትዮጵያ ስለኢትዮጵያዊነት በይፋ መናገር ከመጀመሩ በፊት ነው፡፡ ምኑን አይተህ ተረዳህው እንዳትሉኝ፡፡ በደፍኑ አትኩራችሁ የምትከታተሉት ጉዳይ ግልጽ ሆኖ ይታያችኋል፡፡ ለማ ያስተዋልኩት ከንግግሩ ነው፡፡ ስለኢትዮጵያ ማውራቱ አልነበረም፡፡ እውነትን መጋፈጡ እንጂ፡፡ በኋላ እንደተረዳሁት ብዙ ተዓምራት የሚመስሉ ነገሮችን ሰርቷል፡፡ እኔ ጀዋር ለወከባና ለጥፋት እየተጠቀሙበትና ወደ ማያልቅ አዘቅት እየመሩት የነበረውን ቄሮ ለማ ወደራሱ አመራር ሥር በማድረግ ኢትዮጵያን ከጥፋት ታድጓል፡፡ ኋላም ብቻውን የወያኔን ነብሰበላዎች ተጋፍጧል፡፡ እንደ እውነቱ ለማ ኢትዮጵያን ለመታደግ የሄደበት ደፍረትና ቁርጠኝነት ከላይ ስለተሰጠው እንጂ ሊታሰብ የሚችል አይደለም፡፡ ኦሮሚያ ይሄን ሰው ነበር ያገኘው፡፡ ኦሮሞ ግን አንደሱማሌ አልነበረም፡፡ የኦሮሞ ምሁራ ከሱማሌ ምሁራን በተቃራኒ እጅግ የመረረ የጥላቻና ዘረኝነትን የሚያቀነቅኑ በሕዝብ ሞትና መከራ ላይ ራሳቸውን ታዋቂና ባለጊዜ ያረጉ ናቸው፡፡ የተማሩትም ብቻ ሳይሆኑ የኦሮሞ ሽማግሌ የተባሉትም እንዲሁ ናቸው፡፡ ሕዝቡ ባዘነ፡፡ የለማ ቆራጥነትና የክፉ ቀን ወሳኝ ልጅነቱን ቢረዳውም ሕዝቡ አእነዚህ ለዘመናት ሲነግዱበት በኖሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ፕሮፓጋንዳ ዳግም ሊወጣው ወደሚያዳግት የውዥንብር አዘቅት አቆለቆለ፡፡ እንደ ኦብነግ ኦነግም ሰላማዊ በሚል ገብቶ ሕዝቡን ዛሬም ድረስ ሰላም አሳጥቶት ይኖራል፡፡ ከብዙ መከራ በኋላ ሰላም ሆኖለት በራሱ ጊዜ ጦርነት ፈጥሮ ይሄው ዛሬም አልተፈታም፡፡ በኦሮሞነት ያጃጅሉታል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ይሉታል፡፡ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ አሁን ላይ ለሁሉም ግልጽ ሆኖለታል፡፡ ሥርዓትና ሕግን ሳይሆን ጎልበት አለኝ በሚል እንዲያስብ ስለተደረገና በብዙ ጥላቻ ስተምታታ እውነቱ አልገለጽ ብሎታል፡፡ ዛሬ ከዛ ሁሉ መከራ ያወጣውን ለማን ሌሎች ስለወደዱት ጠልቷል፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ ቅኝቱ ኦሮሞ ለመሆን ሌሎችን መጥላት አለብህ ነው፡፡ ለማንና አብይ በኦሮሞ ዛሬ የተጠሉበት ምክነያት ምንም ሌላ ነገር ሳይሆን ኢትዮጵያን ሁሉ የእኛ ብሎ ስለተቀበላቸው ነው፡፡ የኦሮሞ አክራሪዎች የሚመሩት የኦሮሞ ፖለቲካ በፈጹም ይሄ እንዲሆን አይፈልግም፡፡ እየሆነ ያለው ይሄ ነው፡፡ ሥርዓትና ሕግ በፍጹም አይታሰብም፡፡

ሰሞኑን እንኳን ስንታዘብ አዲስ አበባን (እነሱ ፊንፊኔ ይላሉ ከየት እንዳመጡት ገና አንጠይቃለን ሸዋ አዲስ አበባን ሸገር ነው የሚላት) ጋር በተያያዘ ጦርነት እያወጁ ናቸው፡፡ እንደነ ጀዋር ያለ ወሮበላ ነው የኦሮሞን ሕዝብ የሚመራው፡፡ ሲጀምር ጀዋርም ሆነ ማንኛውም ከአዲስ አበባ ውጭ የሆነ ነዋሪ የአዲስ አባባን ጉዳይ ከእኔ ውጭ ማለት የለየት ወሮበላነት ነው፡፡ ለመሆኑ ዲሞክራሲ ምናምን እየተባ የሚባለው በምርጫ መስሎኝ፡፡ በየትኛውም ቦታ ሕዝብ የመረጠው አስተዳዳሪና ሐሳብ ያስተዳድራል መርሆው ነው፡፡ ከዛ በላይ ይሄ ቦታ የእኔ ነው ማለት ከአገሪቱ ሕግ ውጭ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ የሚቆምሩትን መንግስት እርምጃ እንደመውሰድ አሁን ቸል እያለ ይመስለኛል፡፡ ጀዋር ዛሬ በሰፊው እየሰራ ያለው ለኦነግና-ወያኔ ጥምር ቡድን ነው፡፡ እንደዚሁ እየተምታታ ምርጫ ሲደርስ የለየለት ሽብር ለመፍጠር ነው፡፡ ይሄ ግለሰብ እነድልቡ ወንጀል ነገሮችን እያሰራጨ እስካሁን ለደረሰው ጥፋት አልተጠየቀም፡፡ ኦሮሞ ዛሬ ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ለመቀበል ዝግጁ እንዳይሆን ብዙ ተሰርቶበታል፡፡ ገና ሩቅ ነው፡፡ እንኳ አዲስ አበባ ቀርቶ አዳማና ሻሸመኔም ከኦሮሞ ሕዝብ በልጦ ሌላው ሕዝብ የሚኖርባቸው ከተማ ከሆኑ ምርጫው የሕዝብ እንጂ የወሮበሎች ፍቃድ አደለም፡፡ የሚቀበለው ከአገኘ አብን ነቀምት ላይ ሊወዳደር ይችላል፡፡ እኔ ከዚህ በፊት የሰውየውን ትክክለኛ ማንነት በአለማወቄ በቀለ ገርባ ጎንደር ላይ እንዲወዳደር ብዬ ነበር፡፡ በእርግጥም በዛን ጊዜ መንፈስ እስካሁን ቀጥሎ ቢሆን የማይሆንበት ምክነያት አልነበረም፡፡

በአጠቃላይ የኦሮሞ ፖቲካ መልካም ሰዎችን ለማስተናግነድና ለሠላም ዝግጁ አደለም፡፡ እየተመራ ያለውም እጀግ በዘረኝነትና ጥላቻ በታወሩ በሕዝብ እልቂትና መከራ ኑሯቸውን በመሠረቱ ጉድኖችና ግለሰቦች ነው፡፡ ከዚህ በፊት ተናግሬው ነበር አሁን አስጠነቅቃለሁ፡፡ እነዚህ ቡድኖችና ግለሰቦች ሕዝቡን ወደ አልሆነ መንገድና በመጨረሻም ከሁሉ የተጣላና አናሳ እንደሚያደርጉት አሳሰባለሁ፡፡ አሁንም ብዙዎች ዝም ዝላሉ እንጂ እየሆነ ያለው የሄው ነው፡፡ ሌላ ቀርቶ የውጭ አገር ዜጎች ሳይቀሩ ዛሬ የኦሮሞን ፖለቲካ በጣም ነው እየታዘቡት ያለው፡፡ ይሄን አስመልክቶ አብይ በአንድ ወቅት ጠቆም ሊያደርግ ሞክሮ ነበር፡፡ ለማና እሱ ወደ ስልጣን ሲመጡ የውጭ አገር ሰዎች ብዙ እንደተጠራጠሩ፡፡ አብይና ለማ ሌሎች ስለተቀበሏቸው እንጂ እንደ ኦሮሞ ቢሆን በሕይወትም አይኖሩም ነበር፡፡ በገንዘብና በጥቀም የተገዙ ኦሮሞዎች ሊያጠፏቸው ብዙ ጊዜ ሞክረዋል፡፡ አባ ገዳ ነን ይምትሉ ለመሆኑ ይሄ በሕዝቡ ላይ እየሆነ ያለው ይታያችኋል፡፡ ለማ እንደ ሙስጠፋ እንዲህ ሁሉም ቢተባበረው ብዙ ነገሮችን በአየን ነበር፡፡ ኦሮሚያ የተባለው ክልል ግን የወሮበሎች መፈንጫ ነው የሆነው፡፡ ከእሱም አልፎ ይሄው እንደምናየው አዲስ አበባና ሌሎች ክልሎችንም ሠላም እየነሳ ነው፡፡

መንግስት አሁን በተቋቋመው የወሰን ኮሚሽን ሸዋን ለብቻ ፌደራል ክልል ሊያደርግ ይገባዋል፡፡ ማንም በኦሮሚያ ሥም ከዚህ በኋላ እይተሳቀቀና እየተሰቃየ የሚኖር የለም፡፡ እነጀዋር እንደሚደነፉት ሳይሆን ማንም ለመብቱ አያንስም፡፡ ጀዋር ተወለዶ ያደገው አርሲ ነው፡፡ ይሄን አሳምሮ ያውቀዋል፡፡ ብዙ ኦሮሞን የአስተሳሰብ ብክለት እየፈጠሩ ለራሳቸው በባርነት እያኑሩት ያሉት የኦነግና-ወያኔ ጥምረትን ጨምሮ የኦሮሞ ምሁር ነን በሚል በሕዝብ የሚነግዱ በሚፈጥሩት ሴራ ለደረሰውና ለሚደርሰው ችግር በሕግ ሊጠየቁ ይገባል፡፡ ይሄ ደግሞ ይሆናል፡፡ እንደኦሮሞ ዛሬ ላይ አማራ ውስጥ የሚታየው ኦሮሞን ገደል የከተተው አስተሳሰብ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ነው፡፡ ማንም ሰው መብቱ የሚጠበቀባት አገር ከተባለ ማን ከየት የመጣው መሬትና ሀብት ነው? መፍትሄው እንድና አንድ ነው፡፡ በክልል ሥም ብዙ ሥፍራን እየበከሉ ያሉትን ሴራቸውን እስከወዲያኛው ለመቀበር አሁን ያለው የክልል መዋቅር መፍረስ ግድ ነው፡፡ እስከዛው ግን  ሸዋን ልዩ ፌደራል መንግስት ማረግ ግድ ይላል፡፡ ሁሉም ያስብበት፡፡ የአዲስ አበባ የዛሬው ቁማር በማይመለከታቸው ሰዎች ነው፡፡ ሸዋ ቢያንስ የአማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ከምባታ፣ ሀዲያና ብዙ የተዋጡ ሌሎች ሕዝቦች መኖሪያ ነው፡፡ የሴራና የዘረኝነት ፖለቲካ ሸዋ ራሱን ከቻለ ያበቃለታል፡፡  በማስተዋል ይሁን!

ልዑል እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን! አሜን!

ሰርፀ ደስታ

3 COMMENTS

 1. Stertse desta is a confused Amhara. OLF and OPDO are one. We Oromos love each other. Stertse is confused Amhara who does nothing about politics. Kentu DEBTERA !!

 2. “ሰርፀ ደስታ”: Your anti-Oromo psychosis disguises itself in your rabid hatred for OLF. If OLF were not there, your psychosis would manifest itself by disparaging Lamma and Co. Your mental disorder won’t heal as long as there is a single person who identifies himself/herself as Oromo. Bad luck for you!

 3. The nameless, infantile lot, have hurled insults on Tsetse. For the intellectually compromised, ahistorical and patently vulgar and illogical men such as Debella and Abba Caala, who are posing as Oromos, nothing better is expected. A deep-seated sense of inferiority riles them.

  Their ilk cannot belittle ‘debteras’.
  Can Debella and Caala tell us if there is such thing as city, suburb, highway, square, market etc in their language?
  To sum up, your childish, mindless, bizarre wish to rule over Addis Abaeba will be pipedream. One cannot possess other peoples’ city unless by illegal and violent means.

  Petty cowards like you would not dare opt for violence. Addsi Abeba is the home of Amaras, Gurages, Hadiyas, Kembattas and Oromos of Shewa. Period.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.