በድሬዳዋ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ 54 ግለሰቦች ከእስር ተፈቱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድሬዳዋ ከተማ ተከስቶ በነበረው ግጭት ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር ተጠርጥረው የነበሩ 54 ግለሰቦች ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር መፈታታቸውን የከተማዋ ፓሊስ አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በዛሬው ዕለት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ከእስር ተለቀዋል፡፡

በዚህ የውይይት መድረክ በፍትህ ተቋማት በአስተዳደርና በሌሎች ፈፃሚ ተቋማት ላይ ሊስተካከሉና ሊታረሙ ይገባሉ የተባሉ ጉዳዮች ተነስተው ከወጣቶች ጋር ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በውይይቱ ከፌደራል የተወከሉ የስራ ሀላፊዎች እና የተጠርጣሪ ቤተሰቦች ተገኝተዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የእግዚአብሔር አብ ታቦትን አስገብተው በሚመለሱ ምእመናን ላይ ድንጋይ መወርወሩን ተከትሎ በተፈጠረው ግጭት በቁጥጥር ስር የዋሉ ነበሩ።

ተከስቶ በነበረው ግጭትም በወቅቱ በተባራሪ ጥይት ተመትቶ የነበረ አንድ ህፃን ህይወቱ ያለፈ ሲሆን፥ በ10 ሰዎች ላይ ደግሞ መጠነኛ የመቁሰል አደጋ መድረሱ የሚታወስ ነው፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.