” እነዚያ ብርቱ ክንዶቻችን ስለምን ዛሉ” (ዮቶር ግዮዎናዊው)

“እሳት ቢያንቀላፋ ገለባ ጎበኜው እንዲሉ” አበው አማሬዎች ሰሞኑን በእኛ ህዝብ ላይ እየሆነ ያሉት ነገሮች እኛን እረፍትና ሰላም ከመንሳትና
ለመበታተን ታቅዶባቸው በድብቅ እየተሰሩ የሉ ትንኮሳዎች ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም።

-በቤተ ዕምነቶች ላይ የሚደረገውን ጥፋት ሁሉም ዜጋ በተለይ አማራው ሊያዎግዝ ይገባል።

-በአማራ ምድር ላይ የሚደረጉ ማንኛውም አይነት ፀረ እምነት እንቅስቃሴዎች ለበርካት ሽህ ዘመናት በመቻቻል ተዋዶና ተዋልዶ በሚኖረው ህዝባችን መካከል ላይ የሀይማኖት ግጭቶች እንዲነሱና በአማራ ምድር ውስጥ ከፍተኛ ኃይማኖታዊ ይዘት ያለው ብጥብጥ እንዲነሳ ተልኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱትን ኃይሎች ይኸን ተግባር ሌት ቀን በተደራጄ መልኩ እየሰሩ ለመሆኑ ማሳያ ናቸው ሰሞኑን በጎንደር አካባቢ የተከሰቱ የመስጊድ ቃጠሎዎች።

-ሁሉም አማራ በአደባባይ ወጦ ይህ የኃይማኖት ተቋማትን እና አማኞች ላይ የሚደረግ ማንኛውም አይነት ትንኮሳ እና የሽብር ተግባርን የሚፈፅም አካል ህብረተሰባችንን በአደባባይ ወጦ በፅኑ ሊያወግዝ ይገባል።

– የህዝባችንን አንድነት እና ሰላም ከምንግዜውም በላይ ስጋት ውስጥ የሚከትና ሁለንተናችንን እንዲያናጋና ወደ አልተፈለገ ብጥብጥ ለመቀየር የሚሰሩ ሐይሎችን ተልኮ በማክሸፍ መላው ህዝባችን የኔ ብሎ በንቃት ይጠብቅ ግድ ይለዋል። በተጨማሪም በህብረተሰቡ ዘንድ የችግሩ ፈጣሪ እካላት ቀድሞ ችግሩ ከመፈጡሩ በፊት ተጠርጣሪዎችን ወይም ስጋቶችንን በማስወገድ በኩል ትልቅ መዋቅራዊ አደረጃጀት መፍጠር ያስፈልጋል።እንደነዚህ ያለ አፀያፊ ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ተልኮ ያላቸውን አካላትና የሽብር ቡድኖችን በማጋለጥ ተገቢውን ፍርድ እና ቅጣት ያገኝ ዘንድ ከመቸውም ግዜ የበለጠ ትልቅ እርብርብና እንቅስቃሴ ማድረግ ያሻል።

– የተቃጠሉ መስጊዶቻችን ይሰሩ ዘንድ እንዲሁም እንዲህ አሉ ክስተቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግና ዘላቂ ችግር ፈች የፀጥታ እንቅስቃሴዎች በንቃት እንዲሰራ ሁሉም አካል ኃላፊነትና ግዴታ ነው።

መልካም ቀን!!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.