በግጭቱ ምክንያት ከ 39 ሺህ በላይ ሠዎች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ይፈልጋሉ

በግጭቱ ምክንያት ከ 39 ሺህ በላይ ሠዎች አስቸኳይ የምግብ አቅርቦት ይፈልጋሉ

1 COMMENT

 1. በህዝብ ጥያቄ ሽፋን የፖለቲካ ሸፍጥ ይቁም
  የለውጡን መምጣት ተከትሎ የደቡብ ክልልን በከፍተኛ የፖለቲካ ውጥረት ውስጥ እንዲከርም ካደረጉት ክስተቶች በዋነኛነት ሊጠቀስ ከሚችሉት ዋነኛው ሁሉም የከፍተኛ አመራር በሚባል ደረጃ ለውጡን በሙሉ ልብ ያለመቀበልና የለውጥ ሀይሉን ማገዝ ባይቻል እንኳን እንቅፋት ለመሆን ያለማቋረጥ መትጋታቸው በገሀድ ያሳዩ በቁጥር አብላጫውን ድርሻ የያዙት አመራሮች በስልጣን ላይ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ነገር ግን በቆይታቸው ልክ ለወከሉት ህዝብ የሚጠቅም ተግባር ለመፈጸም ያልቻሉ በአድርባይነት የኖሩ ቀደም ሲል ከለውጡ በፊት የሚፈሩት የወከላቸውን ህዝብ ሳይሆን አለቆቻቸውን እነ አቶ መለስን፤አቶ በረከትን እና ሌሎች ስለነበር በታዛዥነት የወከላቸውን ህዝብ ሲጨቁኑ ሲረግጡ ኖረዋል፡፡
  ከለውጡ ማግስት ጀምሮም ከለውጡ ጋር ራሳቸውን ማዋሀድ ባለመቻላቸው እንዲሁም ባለባቸው ሥልጣንን የማጣት ስጋት በተለይም በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል የሚከሰቱ ግጭቶችን የሚመራው አካል ጋር የነበራቸው የአለቃና የምንዝር ግንኙነት ያልተቋረጠ መሆኑ በህዝብ ጥያቄ ስም የተቀረጹ አጀንዳዎችን ማራገብ ቀዳሚ ተግባራቸው ሆኖ ብዙ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳት እንዲደርስ ምክንያት ሆነዋል ይህንኑ አፍራሽና በህዝቦች መካከል መቃቃር ያለመተማመን የሚፈጥር ነገር ግን ‹‹የህዝብ ጥያቄ›› የሚል ሽፋን የተሰጠውን በተግባር ግን በተቃራኒው የህዝቦችን መብት የሚጻረር ለውጡን እስከመቀልበስ የሚደርስ ግብ ያለው ድርጊታቸውን ቀጥለውበታል፡፡
  እነዚህ እኩይ ዓላማ አራማጆች ስልጣናቸውን በመጠቀም የብሄሩ ወጣቶችን ለመማገድ እጅግ በረቀቀ መንገድ በጥቅም የተደለሉ አክቲቪስትና ጦማሪያን ነን ብለው የሚያምኑ የሶሻል ሚዲያ ቅጥረኞችን አሰልፈው የቅስቀሳ ስራ ሌት ተቀን ይሰራሉ፡፡
  በክልሉ ዋና ከተማ በሰኔ ወር የተፈጠረውን ህገ ወጥ ድርጊት ተከትሎ ወደ አደባባይ ተመልሶ የወጣው ነገር ግን ላለፉት አስርና ከዚያ በላይ ለሆኑ ዓመታት በራሳችን በሲዳማ አመራሮች ማለትም መለሰ ማሪሞ፤ሽፈራው ሽጉጤ፤ደሴ ዳልኬ ፤ሚሊዮን ማቲዎስ፤አብርሀም ማርሻሎ፤ዮሴፍ ፤አክሊሉ፤ቃሬ ፤ቴዎድሮስ፤አያኖ እና በሌሎችም ስልታዊ በሆነ መንገድ ሲደፈጠጥ የቆየውና እነዚህ የተጠቀሱ አመራሮች ለበላይ አለቆቻቸው ታማኝ ለመሆን ሲሉ ጆሮ ዳባ ልበስ ሲሉ የቆዩትን የመዋቅር ጥያቄ መሸሸጊያ አድርገው ለጊዜውም ቢሆን ህዝቡን በተለይም ወጣቱን አታለውታል ባለፉት የስልጣን ዘመናቸው በወከላቸው ህዝብ ላይ የፈጸሙትን የመልካም አስተዳደር በደል መሸፈኛ አድርገው ተጠቅመውበታል አሁን የምናገሩትን ያህል ለህዝቡ የሚቆረቆሩና የሚያሳስባቸው ቢሆን ኖሮ ህገ መንግስታዊ ጥያቄውን ለመመለስ መስዋዕትነት እስከመክፈል የሚያደርስ እንኳን ቢሆን የነበሩበት ትላልቅ ሀላፊነት ይህንን ጥያቄ ለማንሳት እጅግ ምቹ የነበረ ነገር ግን ለጥቅምና ስልጣን ተገዥ በመሆን ያልተወጡት በታሪክ ተወቃሽ ከመሆን የማያድናቸው ትልቅ ስህተት የፈጸሙያም ሆኖ በስህተታቸውም ያልተጸጸቱና ይቅርታ ህዝቡን ያልጠየቁ በአዲስ ካባ ብቅ ያሉ ነባር አመራሮች ናቸው ፡፡
  የሲዳማ ህዝብ በክልል የመደራጀት መብት ህገመንግስታዊ መሆኑን በመረዳት ጥያቄውን ምላሽ እንዲያገኝ ድምጻችንን ስናሰማ የቆየን አሁንም ይህንኑ በሰላማዊና በሰላማዊ መንገድ ብቻ አጠናክረን ለመቀጠል የቆረጥን ወጣቶች ከላይ በገለጽናቸው ከዚህ አጀንዳ ውጪ መንጠልጠያ የሌላቸው ቡድኖች በህቡዕ(ፊት ለፊት ከሚታየውና ከሚነገረው ውጪ ) የተለየ ዓላማ ያነገቡ በድብቅ የገንዘብና የማቴሪያል ድጋፍ ከሚደረግለት ጊዜው ሲደርስ ከሚጋለጠው ቡድን በመለየት የህዝቡን ጥያቄ ይዘን ለመቀጠልና ብዙዎች ባለመረዳት በህጋዊ ጥያቄ ሽፋን ከተሰለፉበት ህገ ወጥ ተግባር እንዲወጡ ለመደገፍ ለመርዳት ቆርጠን በመነሳት እንዲሁም ወጣቶች በማወቅም ባለማወቅም የለውጡ አጋዥ እንጂ እንቅፋት እንዳልሆንን ለማረጋገጥ የወሰድነው እርምጃ ተገቢ መሆኑን በማመን ትግላችንን አጠናክረን እንቀጥላለን
  የለውጥ አመራሩ ጥያቄያችንን መቀበሉን ነገር ግን ይህ የመዋቅር ጥያቄ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ወንድሞቻችን ጥቅም፤ አብሮ መኖርና የጋራ እሴት በጠበቀና ዘላቂነት ባለው መልኩ የሚፈታበት መንገድ እየተሰራ መሆኑን እንደግፋለን
  ይህንኑ ተግባር እንዲያከናውን በህገ መንግስቱ ኃላፊነት የተሰጠው የምርጫ ቦርድ ሙሉ በሙሉ በአዲስ መልክ እራሱን እያደራጀ ያለበትን ሁኔታ እንገነዘባለን ነገር ግን አደረጃጀቱን በበቂ ሁኑታ ባላጠናቀቀበትና ከዚህ በፊት የነበረበት የህዝብ አመኔታ ማጣት ችግር ባላስተካከለበት ቁመና ላይ ሆኖ አሁን ይህንን ከባድ ተግባር በብቃት እንዴትስ ሊወጣ ይችላል የሚለው ጥያቄ ያሳስበናል
  ለሲዳማ ብሄረሰብ የተሰጠው ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በክልሉ ውስጥም ይሁን ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ ብሄር ብሄረሰቦች መብትም ጭምር መሆኑ በሚገባ እንገነዘባለን በመሆኑም ፍጹም ብሄራችንን መገለጫ ባልሆነው ‹‹ራስ ወዳድነት››በሚመስል መልኩ ቀድሞ የቀረበው የኛ ጥያቄ ነው አሁኑኑ ፤በአስቸኳይ ይመለስልን የሌሎቹ በተመቸ ጊዜ ምላሽ ያገኛል ተብሎ በክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር እየቀረበ ያለው አቀራረብ ተቀባይነት የሌለውና ዘላቂ መፍትሄ የማያስገኝ ከመሆኑም በላይ ብዙ ቅሬታዎችን የሚፈጥርና ተገቢም ያልሆነ በመሆኑ ቢያንስ ለስብሰባና ለአቤቱታ ሺ ኪሎሜትር ለሚጓዙ የማሻ ነዋሪዎች አጋርነታችንን በማሳየትናበክልሉ ከሚገኙ አዋሳኝ ዞኖችና የኦሮሚያ ክልልም ጋር የሚኖርን ወሰን በሚገባ ተሰምሮ ምላሽ ሲሰጥበት በጋራ የመልማት ዕቅዳችንን ሳያዛባ የህዝብ ለህዝብ ትስስራችንን የሚያጠናክር ከሁሉም በላይ በሰላም አብሮ ለመኖር የሚያስችለን መሆኑን እንረዳለንይህ ያለመሆኑ የሚያስከትለውን ችግር የአቶ ሚሊዮን ካቢኔ በዞን መዋቅር ደረጃ እንኳን የተፈቀደ መዋቅር የኮንሶንናየደራሼ የአሌ ህዝቦችን አይደለም የልማት ጥያቄ ሊመልስ ከእርስ በርስ ጦርነት አልታደጋቸውም ይህ ሩቅ ሳይሆን ቅርብ ያለ በኛ ተወላጅ አመራሮች የተፈጸመ ቆም ብለን ሰከን ብለን እንድናስብ የሚጠቀስ ግልጽ ማሳያ ነው
  ነገር ግን ከላይ የጠቀስናቸውን ድብቅ አጀንዳዎችን ለማስፈጸም በሚያስችል መልኩ ‹‹በህዝብ ጥያቄ›› ሽፋን ፌዴራል መንግስት ላይ ፍጹም ተገቢ ያልሆነ ጫና የማሳደር የማዋከብ የማስፈራራት ተግባር መፈጸም ፤ሌሎች በክልሉ የሚኖሩ ብሄር ብሀረሰቦች ላይ ጥያቄያችንን አይደግፉም በሚል ጥርጣሬ የሚደረግ ስውር ‹‹ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው›› ሴራ እንዲሁም የዲሞክራሲ ምህዳሩ ሰፊና የሀሳብ የበላይነት እንጂ የአመጽ ‹‹የሴራና የፍረጃ ፖለቲካ›› ጌዜ ያለፈበት መሆኑን ያልገባቸው ምሁራን የተለየ ሀሳብ ይኖራቸዋል ወይም አላቸው ብለው የሚገመቱ የብሄሩን ተወላጆች የማግለል ሴራም ተቀባይነት የሌለውና የመብት ጥያቄያችን ምላሽ እንዳያገኝ የሚደረግ አፍራሽ እንስቃሴ በመሆኑ አጥብቀን የምንታገለው መሆኑን
  ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት ከወያኔ ጉያ ስር ተሸጉጠው ወንጀል የሰሩ መሬትና መብታችንን ሲቀሙ የኖሩ በህዝብ ስም እየነገዱ መኖር እንደማይቻል አሁን ባለው የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሽግግር ጊዜ በፖለቲካ ነጋዴዎችና ሀፍረተ ቢስ ወንጀለኞች በሽፋንነት በሚጠቀሙበት መልኩ ሳይሆን ፍጹም ጥራት ባለው መልኩ የሲዳማ ህዝብና የሌሎች ወንድሞቻችን ጥያቄ እንደሚመለስ አንጠራጠርም፡፡ የሲዳማ ህዝብ በተለይም ወጣቶች ሀቀኛና ሰላማዊ ትግላችን የበግ ለምድ በለበሱ ወላጆቻችንና እኛ ወጣቶችን ሲጨቁኑ ከነበሩ የሲዳማ ተወካይ ነን ባይ አሮጌ አመራሮች ሴራ እራሳችንን በመጠበቅና ሴራቸውንና ዘርፈውን ያፈሩትን ምንጩ ያልታወቀ ሀብትንም ጭምር በማጋለጥ የሲዳማ ወጣቶችን እውነተኛ የመብታቸው ባለቤት ለማድረግ ቆርጠን ተነስተናል፡፡
  የፌዴራል መንግስትም ጥያቄው ዘላቂነት ባለው መልኩ ምላሽ ለመስጠት ሚያደርገውን ጥረት በማጠናከርና ወቅታዊ ምላሽ ለመስጠትና የህግ የበላይነትን ለማስከበር የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥል በዚሁ አጋጣሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
  ኤልቶ የሲዳማ ወጣቶች ማኅበር
  ኢትዮጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!!!
  ጥር/2011
  ሀዋሳ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.