ጎንደርን በተመለከተ ክልሉ <እኔ አልችልምና መከላከያ ገብቶ ያረጋጋ› የሚል ጥያቄ አልጠየቀም ....ጄነራል ብርሀኑ ጁላ 

‹‹መከላከያ በግልጽ በተቀመጠ ሕግ ነው የሚሰራው፤ በሕገ-መንግሥቱ መሰረት ነው የሚመራው፡ ፡ የትኛው ግዳጅ ላይ እንደሚሳተፍ ያውቃል፡፡ ጎንደርን በተመለከተ ክልሉ ‹እኔ አልችልም፤ የእኔ የጸጥታ ኃይሎች እዚህ ያለውን ግጭት ማቆም አልቻሉም፣ ስለዚህ መከላከያ ገብቶ ያረጋጋ› የሚል ጥያቄ አልጠየቀም፡፡ ሲጠይቅ ሕጉን ተከትለን እንሰራለን፡፡ አሁንም ቢሆን ከአቅም በላይ የሆኑ ሁኔታዎች በአንዳንድ አካባቢዎች ሲከሰቱ ከክልሉ ኃይሎች ጎን በመሆን እየተከላከለ ያለው መከላከያ ነው፡፡ ሙሉ ስምሪት ውስጥ ለመግባት ግን ግልጽ የመንግሥትን ትዕዛዝ ይጠይቃል፡፡››
ጄነራል ብርሀኑ ጁላ
(የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የዘመቻና መረጃ መምሪያ ዋና ኃላፊ)
ዛሬ ለንባብ ለበቃው መንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ የተናገሩት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.