በዘጠኙ የጋራ ኮሚቴ አባላት እና በጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መካከል የተደረገው ስብሰባ እና የውይይቱ የውሳኔ አቅጣጫዎች!

ዘጠኙ የጋራ ኮሚቴዎች ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር ባደረጉት ውይይት የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄ የነበረውን ነፃ የሆነ መጅሊስ በጠንካራ መሰረት ላይ ለመመስረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሙሉ ለሙሉ መግባባት ላይ መድረሳቸው ታውቋል: :

ዶ/ር አብይ በውይይቱ ላይ ትኩረት ሰጥቶ አቋም ከያዘባቸው ጉዳዬች መካከል ሙስሊሙ ነፃ ተቋሙን መመስረት እንደሚኖርበት እና በመካከል ያሉ የአይዲዎሎጂ ልዩነቶች ሙስሊሙ የሚያምንበት ነፃ ተቋም ከተመሰረተ ቡሃላ በመነጋገር መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባ ነው::

ኮሚቴው ሃላፊነት የተሰጠው መጅሊሱ ጠንካራ ቁመና ኖሮት ሙስሊሙን በአንድነት ሊያገለግል በሚችልበት ሁኔታ እንዲዋቀር ጥናት አድርጎ ማቅረብ መሆኑን በመግልፅ በቅርብ ቀናት ውስጥ ሶስት መቶ የሚደርሱ የተለያዪ ባለድርሻ አካላት ከመላው ሃገሩቱ በመሰባሰብ ኮሚቴው አጥንቶ ባዘጋጃው የመጅሊስ መዋቅር እና የህግ ማዕቀፍ ዙሪያ ውይይት አድርገው ጥናቱ ወደ ተግባር በሚለወጥበት ሁኔታ ላይ አቅጣጫ እንዱያስቀምጡ ከስምምነት መድረሳቸው ታውቋል::

ጠ/ሚኒስትሩ በሚገኝበት የመጅሊሱን መዋቅር እና ህጋዊ ማዕቀፍ ዙሪያ ውይይት ከተካሄደ ቡሃላ የመጅሊሱን አመራሮች ምርጫ ለማካሄድ አስመራጭ ኮሚቴ በዛው ጉባኤ ላይ እንዲመረጡ ለማድረግ ተስማምተዋል::

በጉባኤው ላይ የሚሳተፉ ኡለሞች፣ምሁራን እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ዘጠኙ የኮሚቴ አባላት ምርጫውን እንዲያስፈፅሙ ከተስማማባቸው እነሱ የሚያስፈፅሙት ሲሆን ሌሎች ይሁኑ ከተባለም ገለልተኛ ሰዎች በጉባኤው ተመርጠው ምርጫውን እንዲያስፈፅሙ እንደሚደረግ ተስማምተዋል::

ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በውይይቱ ወቅት የመጅሊሱ ምርጫ ቶሎ መካሄድ እንዳለበት እና ሙስሊሙ የራሱን ነፃ እና ጠንካራ ተቋማት የመገንባቱን ሂደት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል::

በሙስሊሙ መካከል ያሉ ልዩነቶች ጠንካራ ተቋም ከተመሰረተ በሂደት ችግሮቹን መፍታት እንደሚቻል በማንሳት ኮሚቴው መጅሊሱን በአዲስ መልኩ ለማቋቋም የጀመረውን እንቅስቃሴ ሶስት መቶ የሚደርሱ ባለድርሻ አካላትን በማወያየት ፍፃሜውን እንዲያገኝ እንዲደረግ አቅጣጫ መቀመጡ ታውቋል::

ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚሰባሰቡት ባለድርሻ አካላት ውይይት የሚያካሂዱት የመጅሊሱን መዋቅር እና ህጋዊ ማዕቀፍ ዙሪያ በተጠናቀቀው የጥናት ውጤት ላይ ብቻ መሆኑ ተገልፆል::

ይህ ጉባኤ በቅርብ ቀናት ውስጥ እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን ከጉባኤው መጠናቀቅ ቡሃላ ህዝበ ሙስሊሙ ለረጅም አመታት ሲታገልለት የነበረው የነፃ የሃይማኖት ተቋም ባለቤትነት ጥያቄ በአላህ ፈቃድ ፍፃሜ እንደሚያገኝ ይጠበቃል::

ከጠ/ሚንስተሩ ጋር የተደረገው የትላንቱ የኮሚቴው ውይይት ከመቼውም ጊዜ በላይ የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት እና ጥያቄ መፍትሄ እንዲያገኝ ተተግባራዊ አቅጣጫ የተቀመጠበት እንደነበር ተገልፆል::

ህዝበ ሙስሊሙ በብዙ እንቅፋቶች ጫፍ የደረሰውን የነፃ ተቋም ባለቤትነት ጥያቄ ፍፃሜውን እንዲያገኝ አሁን ካለበት መነቃቃት ይበልጥ በመጠናከር በጥቂት ቀናቶች ውስጥ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ኮሚቴውን በማገዝ እና እንቅፋቶች እንዳይፈጠሩ በማድረግ ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል::

በአሉባልታ እና በጥርጣሬ ጥፋት ላይ እንዳንወድቅ በመጠንቀቅ እውነታውን ቀርበን በመጠየቅ እና በማጣራት ለኡማው የሚበጀውን አካሄድ ከስሜታዊነት በመላቀቅ ልንከተል ይገባናል::

የታሰበው ለውጤት እንዲበቃ አላህ ይርዳን!

ሸረኛውን እና ሴረኛውን አላህ ይያዝልን
አቡዳውድ ኡስማን
(ሼር ፖስት በማድረግ ያስተላልፋ)
(

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.