የተጋነነው አዲስ አበቤነት ( ተሰማ እውነቱ)

አስታውሳለሁ በJuly/2016 አዲስ አበባ ነበርኩ::
በኦሮሚያ ከNovember/2015 በአምቦ አካባቢ የተቀሰቀሰው አመፅ በየአካባቢው እየተስፋፋ ነበር:: ታዲያ ይህቺን ቀን የማስታውሳት አንድ አውስትራላያዊ ቱሪስት የነገረኝን ነው::ከጥቂት ቀናት በፊት ሀገር በሙሉ አማን ነበር ማለት ይቻላል::ይህ ፈረንጅ ወደጎንደር ጉብኝት እንደሚሄድ ነግሮኝ ተሰናበትን::ከትንሽ ቀናት በሗላ በድንጋጤ አዲስ አበባ ተመልሶ የነገረኝ ጎንደር ከተማ ሆቴሌ ታግቼ ነው ያሳሰፍኩት አለኝ:: ከተማው በጥይት እሩምታ ሰላሟ ተናግቷል:: እኔም ሰግቼ ጉብኝቴን አቋርጬ ተመልሼአለሁ አለኝ:: ላምነው አልቻልኩም::ሗላ በቪኦኤ ሳጣራ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ አየለ እጁን ላለመስጠት ያደረገው ተጋድሎ የተኩስ ልውውጥ ሆኖ አገኘሁት:: ጎንደር ሲታመስ ኦሮሚያ ከጫፍ እስከጫፍ በአመፅ ሲቀጣጠል አዲስ አበባ ከተማ ድምፁን አጥፍቶ የራሱን ኑሮ የሚያሳድድ ህብረተስብ ነበር:: በሌላው አካባቢ የተቀጣጠለው ተቃውሞ አዲስ አበባን ዘሎ ደቡብ ምናልባት ይሄድ እንደሆነ እንጂ አዲስ አበባ እንዳችም ኮሽታ አልነበረም:: ሊሆንም እንደማይችል አምናለሁ:: ከመቀሌ ባልተናነሰ የአዲስ አበባ ህውሀት ሰንሰለት እጅግ ረቂቅና የተወሳሰበ ነው::ህውሀት የአዲስ እበባን ኤኮኖሚ በሙሉ ቁጥጥሩ ስር ያደረገ ድርጅት ነው::ይህን ለመበጠስ ገና እጅግ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል::
ይህቺን ቀን July 2016 የማልረሳት ጎንደር በጥይት ታጅቦ ማመፁን ስሰማ ነው:: ህውሀት እንዳለቀለት ያቺ ቀን ቁልጭ ብላ ታየችኝ:: ከ20 አመታት በፊት በመአሕድ እንቅስቃሴ አብዛኛው ጎንደሬ ከዳር ቆሞ ከማየት በትግሉ የመሳተፍ ፍላጎት አልነበረውም ::ህውሀትም ያለ ብአዴን ተላላኪነት በእግሩ መቆም እንደማይችል በሙሉ ስላመንኩበት ያቺ የተኩስ ቀን ጦሷ ብዙ እንደሚያስከትል ያለምንም ጥርጣሬ በሙሉ ለራሴ አሳማኝ ነበር:: በኢትዮጵያ ለውጥ ከውጪ ከዳያስፖራው እንደማይመጣ ተስፋ ከቆረጥኩ 20 አመታት አለፉ:: እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው ብአዴን የህውሀት ተላላኪነቱን በሚያበቃበት ጊዜ እንደሚሆን ግልፅም ነበር::የአማራ ወጣት በብአዴን አመፀ ብአዴን ደግሞ በፈጣሪ ጌታው ህውሀት ላይ ማመፁ የህውሀትን እድሜ አሳጠረ:: የእዲስ እበቤው የትግል አስተዋፅኦ ለጊዜው ዜሮ ነው ማለት ይቻላል:: ከቅንጅት በሗላ አዲስ አበባ ፈዛለች::
ይህ ጎንደር የጀመረው አመፅ አባይን ተሻግሮ አዲስ አበባ መቼ እንደሚደርስ ነበር ለመገመት የሚያስቸግረው:: አዲስ አበባ ለትግል እጅግ የሟሸሸ ከተማ ነበር::ድንገት ምናልባት ድንገት ትንሽ የሚነቃው ከኦሮሚያ ጫትና ሌላ እንዳይገባ ካገቱ ምናልባት ከጎንደር ጋር የትግል አጋርነቱን ያሳይ ይሆናል የሚል ግንዛቤ ነበረኝ::ሆኖም እዚያ ሳይደርስ ብእዴን የመጨረሻ ካርዱን ስለመዘዘ ህውሀት በዝረራ ተሸንፎ ዛሬ በሽሽት መቀሌ መሽጏል:: ህውሀት በአዲስ አበባ የዘረጋው ሰንሰለት ግን ገና የላላ አይመስለኝም::ይህ ነው በአጭሩ የ 2010 ለውጥ ተብሎ በታሪክ የሚመዘገበው::66 የንጉሱ ግለበጣ 83 የደርግ አሁን መጨረሻ 2010 የህውሀት ስርአተ ግለበጣ!
ዛሬ በኢትዮጵያ ለመጣው ለውጥ የአንበሳውን ድርሻ የሚይዘው የኦሮሚያና የጎንደር ወጣት ተሰውቶ ያመጣው ለውጥ ነው::አዲስ አበባ ከመቀሌ ባላነሰ ለህውሀት ምቹና እንኳን ለህውሀት ተቃሙሞ ቀርቶ የድርጅቱ እጅና ጏንት ሆና አገልግላለች:: እንደ አዲስ አበቤዎች ትግል ቢሆን ኖሮ እስክንድር ነጋም ሆነ እንዷለም አራጌ የመፈታታቸው ነገር በጭራሽ አይታየኝም:: ስለዚህ ዛሬ ይህ እስክንድር ነጋ የጀመረው ሚዛናዊነት የጎደለው ጋዜጥኝነት ና እንካሰላንታይ ከታከለ ኡማ ጋር ለእኔ የበላበትን ውጪት ሰባሪነት ውጪ ለይቼ አላየውም:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ታከለ ኡማን ሲመርጥ ጊዜያዊ እንደሆነ ገልፆ ነበር:: ወደፊት አዲስ አበባ በራሷ ለራሷ በምትመርጠው ከንቲባ እንደምትተዳደር ገልፆም ነበር:: ታዲያ በትእግስት መጠበቅ ምን ጉዳት አለው? ዐቢይን በመገዝገዝ የለውጥ ቀልባሾችና ሀይሎችን ከማገዝ ውጪ? እስከዚያም ቢሆን ታከለ ኡማ ከማንም የበፊቱ ከንቲባዎች የበለጠ ሲሰራ ለህዝብ በግልፅ እየታየ ነው:: አዲስ አበባ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ዋና ከተማ ናት:: የሁላችንም የጋራ ከተማ ናት በማለት አቅዋሙን በአደባባይ ገልፆዋል:: ለአዲስ አበቤው ኢትዮጵያዊነትን ሰጪና ተቀባይነት ማን ውክልና ሰጠው? በማያስፈልግና የተጋነነ ዘገባዎችን በማናፈስ ዞሮ ዞሮ አማራውንና ኦሮሞውን ለማጋጨት ባለፈው አመት 2 የግል ሚዲያ ተብዬዎች ለህውሀት እንደሚሰሩት የተለየ ሆኖ አላገኝሁትም:: መልክ ባለው መንገድ ዐቢይን መቃወም ገንቢ ነው:: ከፈለገም ዐቢይን ተወዳድሮ እስክንድር ነጋ በሚቀጥለው ምርጫ ይፎካከርና አማራጭ ፕሮግራሙን ለህዝብ ያቅርብ!
ከአመታት በፊት ያለፈው ስርአት ሰዎች እንዲነሱ ያስተላለፈውን ገና ዐቢይ ሙሉ በሙሉ ያላቀናጀው የቀበሌ እስትዳደር በህዝብ ላይ የሚያድርሱትን ግፍና በደል ዐቢይ ህዝብን እያሰቃየ ነው ብሎ ሀላፊነት የጎደለው ዘገባ መስራት ለለውጥ ቀልባሾች ዱላ ከማቀበል ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
ሌሎችም የታከለ ኡማን ጎጆ ውስጥ መወለድ እንደ ዋቢ መጥቀሱ ምን ፍሬ ነገር አለው? 90% የኢትዮጵያ ህዝብ ሙልጭ ያለ ድሀ ነው:: የአክራሪ ኦሮሞዎችን እንደምንቃወመው ሁሉ ኦሮሞ ሆነው ኢትዮጵያዊነታቸውን ጥርጣሬ ውስጥ ለማስገባት የሚፈልጉትን ፕሮፓጋንዲስቶች ህሊና ያለው ሁሉ ሊሞግታቸው ይገባል:: ይህ ግጭቶችን የሚጋብዙ እንቅስቃሴዎች እንዲታረሙ ሁሉም አዳማጭ መሆን የለበትም:: ለምን ህዝብ ቀስቃሽ በሆነ መንገድ የተጋነነ ፕሮፓጋዳ ይናፈሳል? ታከለ ኡማ ይህን ሁሉ ኦሮሞ በተጨናነቀው አዲስ አበባ የህዝብን ቁጥር በሚያዛባ ሁኔታ ነቅሎ ቢያመጣ ዬት ሊያኖራቸው ነው? እንዴትስ የ6 ሚሊዮን ህዝብ አሰፋፈር ሊያዛባ ይችላል? ለዚያውም በእውነተኛ ካደረገ:: አዲስ አበባም የዛሬዋ ኦሮሚያም ኢትዮጵያ ናቸው:: አዲስ አበባ በውቅያኖስ ላይ የምትንሳፈፍ ደሴት አይደለችም:: ዛሬ አዲስ አበባ የማን ናት? ፊንፊኔ ! አንደኛ ይህ የአፋን ኦሮሞ ቃል አይደለም:: ፀረ ኢትዮጵያ ኦሮሞዎች የፈጠሯት ድራማ ናት:: ፊን ፊን የፍልውሀ ውሀ አለ ብሎ ፊንፊኔ? መጠርያው ከኦሮሚኛ ያውም በአማርኛ ያስኬዳል::ሀቀን ሸምጠን እንካድ ካልሆነ በስተቀር የአዲስ አበባ መጠሪያ በሸዋ ኦሮሚኛ “ሸገር “ነው:: ሁላችንም ያድግንባት ኢትዮጵያ ከገጠር ስንመጣ ሸገር እንውጣ ብለን ነው:: ይህ የአዲስ አበባ ሙግት ስራፈት ሞልቃቃዎች ቡና ማጣጫ ጉንጭ አልፋ ክርክር ነው:: ችግሩ እነሱ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ለለውጥ ሀይል እንቅፋም እየሆኑ ነው:: እኔ እንደ አንድ አማራ ኢትዮጵያዊ በታከለ ኡማ ምንም የተጋነነ ስህተት አላየሁበትም:: ህሊናዬ እንድደግፈው ያስገድደኛል::
ምርጫ ሲመጣ ህዝቡ ታከለን እንደሚመርጥ አልጠራጠርም:: የኢትዮጵያ ህዝብ አስተዋይ ነው::

3 COMMENTS

  1. ተሰማ ሁሌም long term consequence ስለምታይ ሐሳቦችህን እጋራለሁ ። እስክንድር ምን እንደነካው አላውቅም ። እነጃዋር ከሱ ይልቅ ወጣትነት; አደረጃጀት ; ብልሀት (crookedness) አላቸው ። ቄሮን የማሳመጽ የኦሮሚያን ለአዲስ አበባ የዉሀ; የኤሌክትሪክ ; sewer.. አቅርቦት ሊያቆሙ ይችላሉ ። Eskinder is playing with a fire

  2. በዚህ ጉዳይ ላይ ከጸሃፊው ጋር በመሰረታዊ ጉዳይ የምስማማው የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የኢንጂነር ታከለ በጎ ስራ ማጠልሸትና ያላስፈላጊ የፊንፊኔ አዲስ አበባ ባለቤትነት የሁለቱ ዋና ብሄሮችን የማጋጨት የወያኔ ሴራ ነው::ከዚህ በተረፈ አዲስ ኣአበባ ፊንፊኔ ተብላ የኦሮሞ መዲና ለመሆኗ የታሪክ ምሁሩ ብላቴን ጌታ ህሩይ ጽፈውት ሳይታተም በመካነኢየሱስ ቄስ ባድማ ዘንድ ቆይቶ የታተመው መጽሃፍና የአቶ ይልማ ደሬሳ መጽሃፍ ይመስክራሉ::በትግሉ ወቅት ደብረታቦር ላይ ወያኔን ህዝቡ ሲፋለም ጎጃምና ሸዋ ሰተት ብሎ ሲገባ የፊንፊኔ አዲስ አበባ ህዝብ በሞስሎኒ ወራሪ ከተጠቃበት ዘመን ጀምሮ ዝምታም የስውር ትግልም ነበረው::ወያኔን ለመጣል በተደረገው ፍልሚያ በኮተቤ እነሽብሬ በመርካቶ ለጋዎቹ ሰማእታት ኑረዲንና እሱባለው በስተቀር ዝምታው ሰፍኖ መሞዳሞዱ በዝቶ የቄሮና የጎንደር ወጣቶች ፍልሚያና በመጨረሻም ጣና ኬኛ የጋራ ትግል ወሳኝ መሆኑ ትክክል ነው::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.