በአማራ ሰማእታት የተፈጠመው ግፍ በቅዱሳን ሐዋርያት ከተፈጠመው ግፍ ይከፋል! (በላይነህ አባተ)

እርምና እዳን እየበላን መቃብር ከመግባት ያድነን!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚያስተምረው ቅዱስ እስጢፋኖስ ለእምነቱ እንደ ሳሙኤል አወቀ በድንጋይ ተወግሮ ተገድሏል፡፡ የሐዋርያት ገድሎችና ታሪክ እንደሚያስተምሩት ሐዋርያው ጴጥሮስና ጳውሎስ አንገታቸውን ተቀልተው ተገድለዋል፡፡

የአማራ ሰማእታት ግን የጠየቁትንና እረፍት የሚሰጣቸውን ሞትን ተነፍገው ለአስርተ-ዓመታት የክርስቶስ ሐዋርያት ያልተቀበሉትን ፍዳ ተቀብለዋል፡፡ ፓትሪያሪኮች፣ ጳጳሳትና ሌሎችም ካህናት የነፍሰ ገዳዮች ገረድ ሆነው በሚያገለግሉበት ዘመን እነዚህ ሰማእታት ነፍሰ ገዳዮችንና ዘራፊዎችን አሻፈረኝ ብለው ከኢዮብ የበለጠ መከራን ታግሰው ታግለዋል፡፡ ፓትሪያሪኮች፣ ሼሆችና እንደ ኤፍሬም ይስሀቅ ያሉ የእንጨት ሽበቶች በሐሰት በሚመሰክሩበት ዘመን እነዚህ ሰማእታት የሐሰት ምስክር አንሆንም ስላሉ ጥፍራቸው በጉጠት ተነቅሏል፣ ህብለ-ሰረሰራቸው ተቦጭቆ ሺባ ሆነዋል፣ አይናቸው ተመንግሎ ታውረዋል፣ ብልታቸው ተሰለቦ መንኩሰዋል፣ ህሊናቸው ተናውጦ ዓለም ጨለማ ሆኖባቸዋል፡፡

ቅዱሳን ሐዋርያት ካደጉ በኋላ በመረጡት ሃይማኖት ምክንያት ግፍ ተፈጽሞባቸዋል፡፡ የአማራ ሰማእታት ግን በመረጡት እምነታቸው ብቻ ሳይሆን ገና ሳይወለዱ በተካኑት ማንነታቸው የከፋውን የግፍ ጽዋ ተቀብለዋል፡፡

እኛ ከርሳሞች እንደ ቅንቡርስ ስንውጥ ኖረን አፈር ለመብላት ከገዳዮች እየተሞዳሞን ገንዘብ በምናካብትበት ወቅት የእነዚህ ሰማእታት ቤተሰቦች እረኛ እንደሌለው በግ ተበትነዋል፡፡ እነዚህ ሰማእታት ጧሪ አጥተው በችጋርና በሕመም የምድር ሲኦልን ሲኖሩ እኛ በእነሱ መስዋእትነት የታየችውን ጮራ ሞጭልፈን እንደ ነፃ አውጪ የአበባ ጉንጉን በአንገታችን ይጠልቅልናል፡፡ የሰማእታቱን ታሪክ እየደበቅን ለገራፊዎቻቸውና ለአሽከሮቻው የለውጥ ሐዋርያ፣ ሙሴና እያሱ እያልን ዘፍነናል፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን የግፍ ክምር እንደ ራስ ዳሽን እየቆለልን እግዚአብሔርስ በምን ምልጃ ይታረቀናል? በእንደዚህ ዓይነት የግፍ ጎርፍ ተጥለቅልቀን የሰላም ቄጠማ በየትኛዋ እርግብ ይመጣል?

የአማራ ሕዝብ ሆይ! እነዚህ ሰማእታት ላንተ ሲሉ ቅዱሳን ሐዋርያት ከደረሰባቸው የከፋ ግፍ ተቀብለዋል፡፡ እነሱ የመለኮትን ትዕዛዝ ለመፈፀም ለእምነታቸው ሥጋቸውን ሰጥተዋል፡፡ የሕዝብን ሰቆቃ እንደ ቅርፊት ለመቅረፍ በተሳተፉበት ቅዱስ ተልእኮ ቤተሰባቸውን በትነው ዛሬ ጧሪ አልባ አካለ-ስንኩላን ሆነዋል፡፡ እነሱ ከቅዱሳን ሐዋርያት በላይ መሰዋእትነትን ከፍለው መለኮት የጣለባቸውን እዳ በሚገባ ከፍለዋል፡፡ በእነዚህ ሰማእታት የደረሰው አሰቃቂ ግፍ የኔና የአንተ እዳ ሆኗል፡፡ ይህ ከባድ እዳ ከአንተና ከእኔ ጫንቃ እንደ ቀንበር ተጭኗል፡፡ የእዳውን ቀንበር ዛሬ ካላወረድነው ከሚመጣው ትውልድ ጫንቃ ያርፋል፡፡

እዳና እርም በልቶ መሞት ባህላችንም ታሪካችንም አይደለም፡፡ ያለባህላችንና ታሪካችን እርም በልተን ከእነ እዳችን ከመቃብር ላለመግባትና መጪውን ትውልድም እዳ ተሸካሚ ላለማድረግ እዳችንን መክፈል ይጠበቅብናል፡፡ እነዚህ ሰማእታት የፍትህን ጮሯ እንዲያዩ መስኮቱን መክፈት ይኖርብናል፡፡ የሰቆቃ መመሪያ አውጪዎች፣ ትዕዛዝ ሰጪዎች፣ ገዳዮች፣ ገራፊዎች፣ ዐይን አውጪዎች፣ ጥፍር ነቃዮች፣ በአፍ ሸኚዎች፣ ሰላቢዎችና የእነሱ አሽከሮች እንደ ናዚ ሰው-በላዎች ችሎት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰው-በላዎች የዘረፉትና በውስጥም ሆነ በውጪ የሚያንቀሳቅሱት ንብረት ተመልሶ በህይወት ላሉት ሰማእታት መጦሪያ ለሞቱትም መታሰቢያ መሆን ይኖርበታል፡፡

እርምና እዳን እየበላን መቃብር ከመግባት ያድነን!

 

ተመሳሳይ ጽሑፎች፡-

፩. ይሁዳ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር ሸጠው! 

ይሁዳ ክርስቶስን በሰላሳ ዲናር ሸጠው! (በላይነህ አባተ )

፪ .ፍትህ የሌለው እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

የሰማእታት ደሞ ይጮኻል! የግፉአን ህይወት ያቃስታል! ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ! ፍትህ የሌለው እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው! (በላይነህ አባተ )

፫. ፍትህ የሌለው እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

http://quatero.net/amharic1/archives/30170

 

፬. የንፁሓን ደም ይጮሃል!    https://www.ethiopianregistrar.com/amharic/archives/52522

 

፭. No One Has the Right to Forgive on Behalf of the Dead Souls!

https://ecadforum.com/2018/06/28/no-one-has-the-right-to-forgive-on-behalf-of-the-dead-souls/

፮. We  Shall  never  Feed  or Trade  on  Dead  Souls!

https://www.zehabesha.com/we-shall-never-feed-or-trade-on-dead-souls-by-belayneh-abate/

፯. We Shall  Never Forget the Dead Souls to Lick Ice Cream of Political Advantages from Blood Stained Spoons

http://ethioforum.org/we-shall-never-forget-the-dead-souls-to-lick-ice-cream-of-political-advantages-from-blood-stained-spoons/

 

፰.Let Us Be Mature Readers and  Listeners, http://quatero.net/let-us-be-mature-readers-and-listeners-belayneh-abate/

Has Christos ever negotiated or reconciled with Satan? https://www.zehabesha.com/has-christos-ever-negotiated-or-reconciled-with-satan-by-belayneh-abate/

 

 

የካቲት ሁለት ሺ አስራ አንድ ዓ.ም.

 

 

 

 

1 COMMENT

  1. የአማራ ህዝብ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ግፍ የተፈጸመበት ገና በበረሃ እያለ በላይና በታች አርማጭሆ፤ በጠገዴና ወልቃይት በወሎ እና በሌሎችም ሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ነው። ሌላው ቀርቶ በስደት በሚኖርበት ሃገር ሳይቀር በወያኔ ክፍያ የተገደሉ፤ በደቦ የተደበደቡ፤ በሱዳና በሌሎች የዓረብ ሃገሮች ታፍነው ተወስደው ድካቸው የጠፉ ቀጥራቸው ብዙ ነው። በሰፈራ ጣቢያ፤ በስደተኞች መንደር፤ በኢሚግሬሽን ሥራና ሌላም የሥራ መስክ አማራ የሆኑ ሁሉ ስኬታማ እንዳይሁኑ ፋይልን በማፋለስ፤ ዘበኞችንና ሰራቶኞችን ጉቦ በመክፈል የወያኔ የስለላ መረብ የብዙዎችን ህይወት ጥላቻ ቀብቷል።
    የከተማ አለቃ ከሆኑ በህዋላ ወያኔ የፈጸመው በደል የጣሊያኑ ሞሶሎኒ ከፈጸመው በሺህ ጊዜ ይከፋል። እውቁ ኢትዮጵያዊ የተዋጊ ጀት አብራሪና አሰልጣኝ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ “ሞቶ መነሳት” በተሰኘው ጽሁፋቸው እንዳስነበቡን ግፍ በወያኔ ጊዜ ሞልቶ የሚፈስ ለመሆኑ አመላካች ነው። ባንጻሩ ከ 24 ዓመት በፊት አማራ በመሆናቸውና የአርበኛ ዘር አለባቸው ተብለው በወያኔ ታፍነው ተወስደው አራት ወንድሞቿን የት እንደገቡ የማታውቀውን እህታችንን ሰቆቃ ለተመለከተ መፈጠርን ያስጠላል። የካፒቴን ተንኮሉ እናትና የአራት ልጆቹ እናት የልጆቻቸውን ሁኔታ ሳያውቁ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለዮት። ጧትና ማታ እየየ እንዳሉ። ወያኔ አማራን መርዝ በማብላት፤ አፍኖ በመሰወርና በይፋ በመረሸን፤ አካለ ጎዶሎ በማድረግ፤ ሃብት እንዳያፈራ እርሻውን የእህል ክምሩን፤ የንግድ ሥፍራውን በእሳት የሚያጋይ ከሰው ያልተፈጠረ አውሬ ድርጅት ነው። በአርሲ ሰዎች ከእነ ህይወታቸው ገደል እየተገፉ እንዲሞቱ ያደረገው ከኦነግ ጋር በመተባበር ወያኔ ነው። በወለጋ፤ በአርሲ፤ በሃረር፤ በጅማ በቤኔሻንጉል ቤት እየተዘጋ እሳት የተለቀቀበት የአማራ ህዝብ ነው። አሁን ዋናው ነገር ወያኔ በደል ፈጸመ አልፈጸመ ብሎ መከራከሩ ሳይሆን ከበረሃ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ወያኔ በአማራው ህዝብ ላይ ያደረሰውንና በማድረስ ላይ ያለውን ግፍ መረጃ በፊልም፤ በድምጽ፤ በጽሁፍ ማሰባሰብ ነው። ህዝባችን ሊያውቀው ይገባል። የዓለም ህዝብ የወያኔን አረመኔነት ማውቅ አለበት።
    በመሰረቱ ወያኔ አማራን እንደሚጠላ ገና ከጅምሩ እናውቃለን። ለትግራይ ህዝብ አማራ ጠላታችሁ ነው እየተባለ ነው ለዘመናት የተሰበከለት። ለትግራይ ህዝብ ያለፈና የአሁን መከራ ምንጭ አማራ ነው በማለት ነው ባሩድ እንጂያሸቱ ያደረጋቸው። ፕሮፌሰር አሥራት ወ/የስን ማን ገደላቸው? ወያኔ ነው። ወያኔ በመኪና ገጭቶ የገደላቸው ስንቶች ናቸው? የንጹሃን ደም ዛሬም ወደፊትም ይጮሃል። እናት አባታቸውን ያጡ ህጻናቶች ጩሁት በምድሪቱ ያስተጋባል። ወያኔ ፋሺስት ነው። ዛሬም ወደፊትም አይታመኑም። ብልህና ህብር በሆነ ዘዴ ወያኔን መፋለም አስፈላጊ ነው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.