የኢንጅነር ስመኘው በቀለ አሟሟት በተመለከተ የፌዴራል ፖሊስ የደረሰበትን የምርመራ ውጤት ይፋ አድርጓል

ባሕር ዳር፡ ጳጉሜን 02/2010 ዓ.ም(አብመድ)
• ‹‹በፎርንሲክ ባለሙያዎች ተመርምሮ በራሳቸው ሽጉጥ መሞታቸው ተረጋግጧል፤ አሻራው የኢንጅነር ስመኘው መሆኑንም ለይተናል ፡፡
• ፖሊስ ከቦታው ከመድረሱ በፊት የስልክ ልውውጦች የ 9 ደቂቃ ልዩነት ነበራቸው፡፡
• መኪናው በወቅቱ ሞተሩ ተከፍቶ ነበር ፣አራቱ በሮች ተዘግተው ነበር፡፡ 
• የመጨረሻ ስልክ ልውውጥ ባደረጉበት ወቅት ለልጃቸው ደህንነት ይጨነቁ እንደነበር አረጋግጠናል፡፡
• መኪናው ሞተሩ እየሰራ በሩ መዘጋት እንደማይችል በባለሙያዎች አረጋግጠናል፡፡
• በምርመራው መሠረት ራሳቸውን እንዳጠፉ በምርመራ መታወቁን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
• ለምን ራሳቸውን እንዳጠፉ በቀጣይ የሚጣራ ይሆናል ነው ያሉት፡፡
• ስራቸውን በተመለከተ -በሳሊኒ ተጨማሪ ወጭ ከ250 ሚሊዮን ዩሮ ወጭ የተጠየቁ መሆኑን፣
• የህዳሴው ግድብ ስራ በሚፈለገው መልኩ እየሄደ አለመሆኑ መጨናነቅ እንደፈጠረባቸው በምርመራ ተረጋግጧል›› ብለዋል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል፡፡

የአማራ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ

1 COMMENT

  1. አይ መርማሪ ፓሊስ! ዝም ብለህ ትቀባጥራልህ! ማፈሪያ! የሚሰራበት ድርጅት ውስጥ ያሉትን ወያኔ ጅቦች እየተከላክልክ መሆኑን ይታወቅብሃል። እንደው ማን ይሙት እራሱን እንደሚገድል አውቆ ሰው እንዲያውቅለት ማስተዋሻ “ጽፎ” የሰጠው ማስረጃ አለ እያልክን የገዛ መኪናውን ግን ቆልፎ እራሱን ይገላል? ገና ለገና የወያኔን ወንጀል ለመደባበስ የንፁሁን ዜጋ ደም ደመ ከልብ ለማድረግ አትጣር እግዜርም አይወደው!
    ኢንጂነሩ ጎንደሬ ነው ሲሉህ ግዜ ጎንደሬ ሁሉ እንደ አጼ ቴዎድሮስ እራሱን ይገል መሰለህ እንዴ?
    ኧረ መቼ ነው የወያኔን ዘመን ግፍና ወንጀል ፍትህ የምናየው???????????

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.