ባለፉት 6 ወራት ሀገሪቱን ከጎበኙ የውጪቱሪስቶች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

ባለፉ ስድስት ወራት ከውጪ ሀገራት ቱሪስቶች 1 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ ።

ይህ የተባለው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር በባህር ዳር ከተማ እያካሄደ ባለው የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ላይ ነው ።

በስራ አፈፃፀም ግምገማው ላይ ባለፉት 6 ወራት ከውጪ ሀገራት ቱሪስቶች 2 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር ገቢ ለማግኘት  ታቅዶ 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ማግኘት መቻሉን የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳ ተናግረዋል ።

በግማሽ አመቱ 380 ሺህ 376 የሚሆኑ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት መዳረሻዎችን መጎብኝታቸው ነው የተገለፀው።

ይህ ውጤት ሚኒስቴሩ የእቅዱን 53 በመቶ ያከናወነ መሆኑን የሚያሳይ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፥የቱሪስት ፍሰቱ ግን 46 በመቶ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የቱሪስት ፍሰቱ ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀርም በተሻለ ሁኔታ መጨመሩን ዶክተር ሂሩት ተናግረዋል ።

በተያያዘ ዜና በ2011 በጀት ዓመት ለመጠገን ዕቅድ ከተያዘላቸው 26 ቅርሶች ውስጥ የላሊባላ ውቅር ዓብያተ ክርስቲያናት፣የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትና የአክሱም ሀውልት ቅድሚያ የሚሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።

በናትናኤል ጥጋቡ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.