ሸዋሮቢት መንገድ ተዘግቷል! እናትና ልጅን ገሎ ጠፍቷል ተብሎ የተጠረጠረውን ግለሰብ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነገረ

“ባሏ አረብ አገር የሚኖር ባለትዳርና የአንድ ልጅ እናት ነበረች። የባሏን ውጭ መኖር ተከትሎ በአካባቢው አንድ ወዳጅ ትይዛለች። በቅርቡ ግን ውጭ ያለው ባሏ መምጫው ስለደረሰ፣ ውስጥ ያለውን እንዲርቃት ትነግረዋለች። ውስጥ ያለውም በዚህ ውሳኔ አልተደሰተም፣ ተበሳጨ፣ ቅናት አንገበገበው፣ መጥፎ ውሳኔ ወሰነ። እሷንም ህፃን ልጇንም(ከህጋዊ ባሏ የተወለደ) ገሏቸው ጠፋ!” በአካባቢው የሚኖርና ቦታው ላይ ያለ ሰው፣ ከደቂቃዎች በፊት በስልክ የሰጠኝ መረጃ ነው።

ዛሬ እናትና ልጅን ገሎ ጠፍቷል ተብሎ የተጠረጠረውን ግለሰብ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተነገረ፣ ይሄን የሰሙ የተወሰኑ የከተማው ነዋሪዎች፣ ‘ግለሰቡን ፓሊስ አሳልፎ ይስጠን እና እንግደለው፣ ወይም በመንጋ እንፍረድበት’ በማለት ፓሊስ ጋር ወደ ግጭት ገብተዋል። ጥይትም በብዛት ሲተኮስ ነበር፣ ጎማ አቃጥለውም መንገድ ዘግተዋል።

በእውነቱ በእናትና ምንም በማያውቀው ህፃን ልጅ ላይ የደረሰው በደል አሳዛኝ ነው። ቢሆንም ግን፣ ፓሊስ ከየትም ፈልጎ ግለሰቡን(ተጠርጣሪውን) መያዙን ማድነቅና በቀጣይም ገዳይ ተገቢውን ህጋዊ ቅጣት እንዲያገኝ ማድረግ ሲገባ፣ ‘እኛ እንፍርድ!’ ማለት ተገቢ አይደለም።

በዚህ በቀላሉ በህግ አግባብ ፍትህ ሊገኝበት በሚችል ጉዳይም፣ አስፓልት ዘግቶ መንገደኛ ወገንን ማንገላታት ነውርም ነው። ለሌላው ህዝብም ሊታሰብ ይገባል።

አደራችሁን፡ ደግሞ ይሄንንም ቄሮ፣ ፋኖ ምንትሶ ብላችሁ፣ የብሄር ግጭት እንዳታደርጉት።

ህይወታቸውን ያጡትን እናትና ልጅ ነፍስ ይማር!!!
መንገዱ ግን በአስቸኳይ ይከፈት!!!
(credit – Anteneh birhanu)

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.