ለኦህዴድ (ኦዴፓ) ስትራቴጅካዊ ወዳጁ ህወሃት እንጅ ብአዴን (አዴፓ) አይደለም!!!    (ከህዝባዊ ሰልፉ)

እንደሚታወቀው ኦዴፓ የስልጣን መንበሩን ለመቆጣጠር ባቆበቆበበት ወቅት ደጋፊ ይፈልግ ነበርና በዚህም በዚያም ብሎ የአዴፓን ድጋፍ አገኘ። ኦዴፓ ይህንን የአዴፓን ድጋፍ የፈለገው በህወሃት ሰዎች ተይዞ የነበረውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ የበላይነት ለሞቆጣጠር አስቦ እንደነበር ለመረዳት ስልጣን ላይ ከወጣ በኋላ እየወሰዳቸው ያሉ ርምጃዎችን በማየት መረዳት ይቻላል።

ኦዴፓ አሁን ስልጣኑን ከሞላ ጎደል እያደላደለ ስለመጣ የአዴፓ ድጋፍ አያስፈልገኝም እያለ ይመስላል። ምክንያቱም ድሮውንም ቢሆን የኦዴፓና የአዴፓ ወዳጅነት ታክቲካዊ (Tactical) እንጅ ስትራቴጂካዊ (Strategical) አልነበረምና። በነዚህ ሁለት ድርጅቶች መካከል ያለው ግንኙነት ታክቲካዊ እንጅ ስትራቴጅካዊ የማይሆንበትን ሁኔታ ሶስት ዋና ዋና የሆኑ ምክንያቶችን በመጥቀስ ብቻ መረዳት ይቻላል።

በመጀመሪያ ደረጃ ኦዴፓ ውስጥ የተሰባሰቡት አብዛኛዎቹ አመራሮች በማንነት ላይ የተመሰረተው ፌዴራሊዝም አቀንቃኞች ናቸው። በተቃራኒው አዴፓ ውስጥ ያሉ አብዛኛዎቹ አመራሮች ደግሞ አህዳዊ የሚል ስሜት የሚንፀባረቅባቸው ናቸው። ሁለተኛ ኦዴፓዎች በህገመንግስቱ ላይ ከሞላ ጎደል እምነት አላቸው። አዴፓዎች ግን ህገመንግስቱ እኔን አይወክልም በሚል የማህበረሰብ ክፍል ጫና ምክንያት በህገመንግስቱ ላይ የተሟላ እምነት አላቸው ብሎ ለመናገር አስቸጋሪ ነው። ሶስተኛ ብዙዎቹ ኦዴፓዎች ሲሻቸው አማራ ሌላ ጊዜ ደግሞ የአማራ ገዥ መደብ ለረጅም ጊዜ ሲጨቁነን ኖሯል የሚል ያደረ ቂም እንዳላቸው መረዳት ይቻላል። ቁጥራቸው ቀላል የማይባል የአዴፓ ሰዎች በበኩላቸው ኦዴፓ በአዲስ አበባና በኦሮምኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋነት ጉዳይ ላይ ባለው አቋም ብዥታ ውስጥ የገቡ የሚመስሉበት ሁኔታ መኖሩ ነው።

ይህን የሁለቱን ድርጅቶች ግንኙነት ስትራቴጅካዊ አለመሆን የሚያጎላው ደግሞ ሁለቱም ድርጅቶች በሚንቀሳቀሱባቸው አከባቢዎች ያሉት የፖለቲካ አቀንቃኞችም ይሁኑ ሌሎች አካላት ያላቸው እሰጥ አገባ ነው። በኦሮሚያ ውስጥ ያሉት ሃይሎች አማራ ሲጨቁነን ኖሯልና እንዲህ በቀላሉ ይቅር የምንልበት አንጀት የለንም ይላሉ። በዚህም ምክንያት የአፄ ሚኒሊክንና በዙሪያቸው የነበሩ ሰዎችን ሃውልት ማየት አንፈልግም በሚል ሽንጣቸውን ገትረው ይከራከራሉ። በአማርኛ የሚጠሩ የቦታ ስሞችም በክክልላችን እንዲኖሩ አንሻም ብለውም አምርረው ድምፃቸውን ያሰማሉ። እስካሁን የተቀየሩ ብዙ የቦታ ስሞችም አሉ።

አዴፓ በዋነኛነት በሚንቀሳቀስበት አማራ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ ሃይሎች ደግሞ ኦዴፓ የበላይነቱን ለማንገስ እየሰራ ስለሆነ ህዝባችን በእኩልነት ላይጠቀም የሚችልበት ሁኔታ ይኖራል ብለው ይሰጋሉ። ምናልባትም አማራ ክልል ውስጥ ያለውን የኦሮሚያ ልዩ ዞን በመጠቀም ግዛታችን አልፈው ለመምጣት ሊሞክሩ ይችላሉ ብለውም ጥርጣሬያቸውን ያጋራሉ። በአዲስ አበባ የባለቤትነትና በኦሮምኛ የፌዴራል የስራ ቋንቋ ይሁን የሚሉ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች ጉዳይ ላይም ጎራ ለይተው እሰጥ አገባ የገቡ መሆኑን እያየን ነው።

በዚህ ሂደት ኦዴፓ እቅዶቹንና አላማዎቹን ለማሳካት በሚገባ በተጠናና በተደራጀ መንገድ እየተንቀሳቀሰ ለዚህም አዴፓን በፈለገው መንገድ የተጠቀመበትና አሁንም እየተጠቀመበት ያለ ሲሆን አዴፓ በበኩሉ መያዣ መጨበጫው ጠፍቶበት ተበትኖ ያለ ፓርቲ ሆኗል። እንዲያውም ብዙዎቹ የሚያምኑት አዴፓ ልክ በብአዴን ስም የህወሃት አገልጋይ እንደነበረ ሁሉ አሁን ደግሞ ለኦህዴድ አጋፋሪና አጃቢ እንደሆነ አድርገው ነው። አዴፓ እንደፓርቲ ያለው ግምገማ ግን ከዚህ እውነታ ተቃራኒ እንደሆነ መረዳት ይቻላል። በአሁኑ ወቅት አዴፓ የሚያምነው በሃገሪቱ ውስጥ መጣ ለተባለው ለውጥ ከኦዴፓ ጋ እኩል ድርሻ እንዳለውና አሁንም ለውጡን በማስቀጠል ረገድ ከኦዴፓ ጋ መሳ ለመሳ ሆኖ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ነው። በዚህም አለ በዚያ ግን አዴፖ የወቅቱን የሃገሪቱን ፖለቲካ ተንትኖና ሰፋ አድርጎ ብልህነት በተሞላበት መንገድ የተረዳው አይመስልም። ለመረዳት ፍላጎት የለውም ብቻ ሳይሆን አቅም እንደሌለውም ከሚያደርጋቸው እሰጥ አገባዎች መረዳት ይቻላል። አዴፓ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ የአማራውን ህዝብ ተገቢ ጥቅም (Legitimate Interest) ሊያስጠብቅ ይቅርና የራሱን ህልውናም ሊታደግ የሚችል ፓርቲ አይሆንም። በመሆኑም ይህን የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥቅም የሚተነትን፣ የሚያቅድና የሚያስፈፅም ብቃት ያለው ግን ደግሞ  ዴሞክራሲያዊ  የሆነ ፓርቲ የማጎልበት ወይም የመፍጠር ጉዳይ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የአማራ ሙህራንና የፖለቲካ ልሂቃን በደንብ ተገንዝበው ለተግባራዊነቱ ሊንቀሳቀሱ ይገባል።

የኦዴፓና የአዴፓ ግንኝኙነት ከላይ በተገለፀው መልኩ ታክቲካዊ/ጊዚያዊ ነው ከተባለ የኦዴፓና የህወሓት ግንኑነት ስትራቴጅካዊ ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው የሚለውን ደግሞ ከዚህ በታች ለማብራራት ይሞከራል። በእርግጥ በህወሃት ሰዎች ይፈፀም የነበረ ግፍና በደል ስፍር ቁጥር ያልነበረው በመሆኑ የኦዴፓን ሰዎች ለትግል አነሳስቷል። በዚህ ወቅት ወትሮውንም ቢሆን ለህወሃት የመረረ ጥላቻ የነበራቸው ብዙዎቹ የአዴፓ አመራሮች ከኦዴፓ ጎን በመሰለፍ ለህወሃት ሰዎች መንኮታኮት ታላቅ ሚና ተጫውተዋል። ይህን የተረዱት ኦዴፓዎች ደግሞ በቀላሉ ስልጣን ሊጨብጡ ይችሉ ዘንድ የአዴፓን አመራሮች በበለጠ ወደነሱ ቡድን እንዲሳቡ አድርገዋቸዋል። ለዚህ እቅዳቸው መሳካት የተጠቀሙበት ዋነኛው ዘዴ አማራ ክልልን መጎብኘት ነበር። መጎብኘት ብቻም ሳይሆን ስለኢትዮጵያዊነት ከፍታ እንዲሁም ስለኢትዮጵያ ሱስነት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሰብከዋል።

እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ታላቅ ቁምነገር ግን ኦዴፓ በጊዚያዊነት ከአዴፓ ጋ ቡድን ፈጥሮ የተንቀሳቀሰው ከህወሃት ጋ መሰረታዊ የአላማና የአደረጃጀት ልዩነት ኖሮት ሳይሆን ስልጣንን ከህወሃት ሰዎች ነጥቆ የራሱ ለማድርግ ካለው የጠለቀ ፍላጎት ተነስቶ ነው። ይህን መሰረታዊ የሆነ በህወሓትና በኦዴፓ መካከል ያለ ስትራቴጅካዊ ግንኙነት ለመረዳት የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በደንብ ማጤን ብቻ ይበቃል።

አንደኛው ነጥብ ህወሃትም ሆነ ኦዴፓ በአማራ ገዥ መደብ ተጨቁነናል የሚል ጠንካራ የሆነ አቋም አላቸው። ሁለቱም ይህን ጭቆና ለማስወገድ ዋጋ ከፍለናል ይላሉ። የኦዴፓም ሆነ የህወሓት ሰዎች የአፄ ሚኒልክን አስተዳደር እንደወራሪና ቅኝ ገዥ እንጅ እንደ አገር ባለውለታ አያዩትም። በዚህም ምክንያት በሚኒልክ አስተዳደር ላይ ያላቸው ስር የሰደደ ጥላቻ አሁን ድረስ የሚታይ ነው። ይህ አስተሳሰብ በሁለቱ ድርጅቶች ሰዎች ብቻ ሳይሆን በዙሪያቸው ባሉ ሁሉ ይቀነቀናል።

ሁለተኛ ኦዴፓም ይሁን ህወሓት በህገመንግስቱ ላይ ፅኑ እመንት አላቸው። ሁለቱም ድርጅቶች ህገመንግስቱ የትግላቸው ውጤትና ዘላቂ ጥቅማቸውን ሊያስከብር የሚችል መሳሪያ ነው ብለው ያምናሉ። እነዚህ ሁለት ድርጅቶ የመገንጠልን መብት ጨምሮ ብሄራዊ ጥቅማችንን ልናሟላበት የምንችል ትልቅ መሳሪያ ቢኖር ህገመንግስቱ ነው የሚል የማያወላውል አቋም አላቸው።

በሶስተኛ ደረጃ ሁለቱም ድርጅቶች የኢትዮጵያ ችግር በዘላቂነት የሚፈታው በፌዴራሊዝም ስርዓተ- መንግስት ነው ብለው ያምናሉ። እነዚህ ሁለት ድርጅቶች የሚያምኑበት የፌዴራሊዝም አይነት ደግሞ መልክዓ ምድራዊ ሳይሆን በማንነት የተመሰረተው ፌዴራልዝም ነው። በሁለቱም ድርጅቶች ከዚህ አይነቱ የፌዴራል ስርዓተ-መንግስት ነቅነቅ ማለት የሃገር ህልውናን እንደማናጋት ተደርጎ ይቆጠራል። ለዚህም ነው ሰሞኑን ኦዴፓም ሆነ ህወሓት በፌዴራሊዝም ስርዓተመንግስት ላይ አንደራደርም የሚል ጠንካራ መግለጫ እየሰጡ ያሉት።

ይህ በህወሓትና በኦዴፓ መካከል ያለ ስትራቴጅካዊ ግንኙነት በደጋፊዎችም ሆነ በሌሎች አካላት በተለያዩ መድረኮች ጎላ ብሎ በመገለፅ ላይ ይገኛል። ለምሳሌ እነዚህ ሃይሎች ሁለቱም ድርጅቶች በማንነት ላይ የተመሰረት የፌዴራል ስርዓተ-መንግስት አቀንቃኞች መሆናቸውን በመግለፅ በዘላቂነት አብረው ሊሰሩ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳለ በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰማሉ። ይህን ጠንካራ የሆነ አቋም ለመረዳት ለአጭር ጊዜም ቢሆን የማህበራዊ ትስስር መድረኮችን መከታተል በቂ ሊሆን ይችላል።

ከላይ የተገለፁት አጠቃላይ ሁኔታዎች ሲቃኙ መረዳት የሚቻለው የአዴፓ (ብአዴን) እና የኦዴፓ (ኦህዴድ) ግንኙነት ታክቲካዊ/ጊዚያዊ ሲሆን በህወሓትና በኦዴፓ (ኦህዴድ) መካከል ያለው ግንኙነት ግን ስትራቴጅካዊ/ዘለቄታዊ መሆኑን ነው። በመሆኑም ኦዴፓና ሀወሓት አዴፓን በማግለል ተመልሰው የሚገጥሙበት ጊዜ ሩቅ አይመስልም።

6 COMMENTS

 1. The ODP has never promised the ADP to reign it on the Oromo people. The ODP has also never promised to bring back the throne of Menilik. The ADP has been ruling the Amahara regional state freely since Dr. Abiy become PM of Ethiopia. The ADP shares Federal state powers with all stakeholders. What do you need more? Do you want to have the old Ethiopia?

  You will never see the Ethiopia of Menilik, Haile Selassie, Mengist and Melese. It was already dead. You will see the new Ethiopia with many interesting and fascinating hopes in the near future. We will be all proud of it. Watch out!

  Please try to open your mind and heart to understand what the Oromo nation has achieved in the last 50 years as a result of its struggles against the inhuman systems of the ex-Neftegnas and that of the TPLF. If you are a genuine person you must be grateful of the Oromo struggles against the TPLF. That is why you are now in a position to speak out freely. Please you should have to be thankful!

  The struggles of the Oromo heroes and heroines have exposed the falsehoods of the fake Ethiopia nationalism. The Oromo intellectuals have reactivate and reasserte the Oromo nationalism (OROMUUMA). All the Oromo are now proud of their cultural heritages, history and  social values.

  The current ethnic federal structure of Ethiopia is the political arrangements which were mainly constructed and promoted by the beloved Oromo intellectuals and OLF leaders like Gelassa Dilbo,  Lenchoo Lataa,  Dima Nagawo and others. The TPLF has accepted it by making few modification. The TPLF tried to implement it at least nominally after banning the OLF, in order to win the hearts of the Oromo nation. Therefore, the main shareholder of this federal arrangement is the OLF, the freedom fighter. Accusing the TPLF in regard of the federal structure is unfair. The TPLF must be accused for shortcomings of the implementation and wrong boundaries.  Thus, this federal structure was not implemented at the free will of the TPLF. It is a fruit of the century old bitter struggles of the Oromo nation and other subjugated nations. Consequently, accepting these federal arrangements is a must for all stockholders. 

  There is nobody without national background and heritages in this planet. All human beings have ethnic backgrounds regardless of the composition of their ethnicity. Those who try to nullify their ethnic backgrounds are claiming Amhara ethnicity by default under the mask of Ethiopianism. They speak amharic and claim the cultures from north as their culture. They try to impose their default identity (Amaharaism as Ethiopianism) on the others. But it is not acceptable! Therefore, the current Ethiopian nationalism is equivalent to the Amahara nationalism. Which will be voided soon. It will be replaced by the multinationalism of all Ethiopians. You should have to swallow this truth.

  No more the politics of one language, one culture  and a single nation. We will build the new Ethiopia with all its facets as a multinational country. Please also don’t forget about the peoples of Agawo, Qimant, Waito and others. They will confront you soon with all their demands.

 2. ወያኔ በኣጀንዳው የያዘውን ኢትዮጵያን የማጥፋት ተንኮሉ ባሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በሚመራው መንግስት በኩል አየተገበረው አንዳለ ከማንም የተሰወረ ኣይደለም፥፥ የዛሬ ፰ ወር ገደማ ህዝብ ድጋፉን የገለጸው ብሔራዊ እርቅና የሽጝር መንግስት ተቋቁሞ በእኩልነት በፍትህና በውነተኛ ዲሞክራሲ ላይ የተገነባች ኢትዮጵያን መስርቶ ሁሉም ከህግ በታች ሆኖ በዘር ሳይከፋፈል የሃገሪቷ አንጡራ ሃብት በግለሰቦች እጅ ሳይመዘበር፥ አንዱ በውስኪ ሲራጭ ሌላው የሚጎርሰው አጥቶ የማያለቅስባት፥ ሰው የተሰማውን በመንግስት ላይ ቅር የተሰኘበትን ነገር ለመናገር ለመጻፍና ህዝባዊ ስብሰባዎችን በነጻነት ያለፍርሃት ለማካሀድ የሚችልባት፥ መሪዋ በህዝብ፥ ከህዝብና ለህዝብ አገልግሎት የሚመረጥባት፥ መሪዎቿ ጋራ እንደናደ ዝንጀሮ በቴሌቭዥን እየቀረቡ በ፺ሚሊዮን ህዝብ ላይ የማይደነፉባት፥ መከላከያው ሰራዊት የገዢውን ጥቅም የሚያስጠብቅ ሎሌ ሳይሆን ወይንም ህዝብን ለመግደል አፈሙዙን የሚያነሳ ሳይሆን ህዝብን ለመጠበቅ የሚቆም ሃይል የሚሆንባት፥ ሁሉም ዜጋ በሃገሩ ላይ ሰርቶ የሚያድግባት፥ተማሪው ተምሮ ያለአድልዎ ስራ የሚያገኝባት፥ ሰው ፍርድ ቤት ቆሞ ትክክለኛውን ፍርድ የሚበየንባት፥ ሰው ከሃገሩ ለነፍሱ ፍራቻ ወደሌላ ሃገር የማይሰደድባት፥ አንዱ ልጅ ሌላው የእንጀራ ልጅ ያልሆነባት ወዘተ ሃገር ለመመስረት የሚያስችል መንገድ መስሎን ነበር አንጂ ሌላኛው የጥፋት መንገድና የቀድሞው የመለስ የጭቆና ዘመን ሳይቀየር የሚቀጥልባት፥ ወያኔ የቀድሞውን አላማውን ከግብ ለማድረስ ሃገሪቱን ለመበታተን የሚጠቀምበት ሎሌ ይመጣል ብለን ኣልነበረም።ነገር ግን የኢትዮጵያ አምላክ ከጎኗ ስለሆነና የጀግና ደሃ ስላይደለች የቁርጥ ቀን ልጆቿ በዘር ሳንከፋፈል ተረባርበን ከአጠላባት አደጋ መታደግ የዜግነት ግዴታችን ነው፥፥ ጅብ ካለፈ ውሻ ጮኽ እንዳይሆንብን በኣቢይ ኣህመድ ኣደንዛዥ ቱልቱላ ሳንወሰድ ሃገራችንን ከወያኔና ከኦነግ ኣሻጥር ብንታደጋት መልካም ነው።

 3. ጭራሽ ኦዴፓ ነበር የትግል አጋር ይፈልግ የነበረው? ማነው በኦሮሞ ትግል ውስጥ የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው ያለው? መቀሌ ናት ባንተ ካልኩሌሽን::
  ማፈሪይ ቅጥፈት ባህላቹ መሆኑን ለሁሉም ህዝብ ሣይታወቃቹ እያሳያቹ ነው::
  ምድረ ፈልፈላ!

 4. Gamaada
  I have never read where the ADP is out to subjugate the Oromo people. What you are missing here there are political forces who see their dream of coming on top is going badly. Therefore they are out to create every opportunity to divide the new found coalition between ODP and ADP and weaken it. I don’t think they would succeed. I guess when you are desperate you try every angle.

 5. It is sad that some of the commentators are still talking in the terminology taken from the west. All of this ism and ists and blalblabla is meaningless except for the so called educated know nothings who learn these word and try to apply it to Ethiopia. There is etiopiawinet what which is an all inclusive transcendent idea and philosophy which binds us all. Oromo speakers amaregna speakers, Tigrinya speakers and so on and on. I fear the writer perhaps trying to sow discord so I won’t waste time commenting except to say learn Ethiopias intertwined history of all its people before coming here and talking about strategic and tactical. There is nothing strategic about any of Ethiopias people we are connected by more than that we are connected by etiopiawinet.

 6. TPLF is dreaming again. No Oromo and Amhara will ever forget the torture and killings committed by TPLF Regime for the last 27 harsh years. These evils MUST GO.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.