ላጋጣፎን መፈናቀል አስመልክቶ  (ከአባዊርቱ)

ወገኖች
ከታዘብኩት በጥቂቱ
፣፩) በሸገር እንኩዋንስ ዳርዳሩ ቀርቶ መሀሉም ከ፪፯ አመታት ጀምሮ ሰዎች ህገወጥ በሆነ መንገድ የሆነች ቆርቆሮ ለጣጥፈው ከፍ ሲልም ጎጆ ቀልሰው ከፊሉ ህጋዊ አስደርጎ ሌላው መሄጃ አጥቶ በራሱ የሚኖር ወገን ለመኖሩ ውሸት ነው? እና አዲስ ዘመንና አስተዳደር ሲመጣ ከተማዋን አዘምኖ በአዲስ መልክ ቢዋቀርና እነዚህ ጎዳና ተጣሉ ተብሎ የሚባልላቸው ወገኖች ቤት ይሰጣቸው እንዳልሆነ ምን ታውቃላችሁ? በበኩሌ ይህ ሁሉ የመአት ደወልን የምትደውሉ ሰዎች እንዲህ ትመስሉኛላችሁ፣፣
ሀ) የለየላችሁ ለኢትዮጵያ ትንሳኤ የማትተኙ ምቀኛ ወያኔዎች
ለ) ስልጣን ከጃችሁ መራቁን የተገነዘባችሁ አገር ወዳድ የዜግነት ፖለቲካ አቀንቃኞች፣፣ የአንድነት ሀይሎች፣፣ ከልቤም አዝናለሁ ለናንተ፣፣ለምን ብትሉኝ የናንተ አገርና ወገን መውደድ ከስልጣን ጋር የተቆራኘ በመሆኑ፣፣አይመስለኝም ነበር፣፣ ግን ነው፣፣ ከዚህ የምትለዩና የዜግነት ፖለቲካ አራማጅ ሆናችሁ በቅንነት ለወገን የሆናችሁ ትኖሩ? አዎ አላችሁ ቁጥራችሁ ግን ብዙ አይመስለኝም.
ሐ) ጃዋር ክርስትያን ሸዋን አስልሞ እስላም ሪፐብሊክ ፈጠራ የሽብር ወሬ ጃዋርም እራሱ መጀመርያ ክርስትናን ይቀበላል እንኩዋን ይህን ሊያስብ፣፣ በጭራሽ አያልመውም፣፣ ባለቤቱ ግማሽ ጎኑ ክርስትያን እኮ ነች፣፣  አያደርገውምም፣፣ ይህ ሽብር በመፍጠር የአቢይን አስተዳደር ለማጠልሸት ሆን ተብሎ የሚረጭ መርዝ ነው፣፣ ታላቁን የሸዋን ዖሮሞ ካለማወቅም ነው ወይም አውቆ ከመስሊም  ዖሮሞ  ይሁን አማራው ወገኑ ብሎም ከወንድም ክርስትያን አማራው ወገኑ ለመለያየት የታቀደች ፕሮፖጋንዳ መሆኑዋ ነው፣፣ አቤት ክፋት፣፣
ወገን ተረጋጋ!!
ከባድ የሽብር ያውም የወሬ ዘመቻ እየተካሄደ ነው፣፣
የባለፈው የአሜሪካን ምርጫ ያስታውሰኛል፣፣ ትራምፕ የሚሉት ቅሌታም ሰውዬ በንዲህ አይነት ፌክ ወሬ ውስጥ ነበር የመጣው
መ) አንዳንድ አንቱ የምንላቸው ሰዎች ወጥመድ ውስጥም እየገቡ ወይ ሳያውቁ ከከፋ አውቀው ግን መከረኛ ስልጣን የሚሉዋት ነገር ሆኖ ወይም በቅንነት የሚያዩት ድህነትና የሰው ኑሮ አንገብግቦአችሁም ይሆናል፣፣ ትራንዚሽን ከባድ ነው፣፣ ያማልም፣፣
ሳጠቃልል
አገር ወደአዲስ ምእራፍ ስትሄድ ዲስፕሌስመንት ይኖራል፣፣ ከተማዎች የሚሰፉትና የሚያድጉት ሰው እየተፈናቀለ እየሞተም ነው ከባሰ፣፣ የአለም ከተሞችን አመሰራረት ታሪክ የታደላችሁት ጉግል አርጉ እስቲና እዩት፣፣ ሁሉ በዘር አይን ስለሆነ ያገራችኑ ይቺን ቀዳዳ ተጠቅመው ነገሩን አባብሰው ሊያባሉን ፅልመቶች መልአክ ተመስለው መተዋልና በሮቻችሁን ጠበቅበቅ አድርጉ፣፣ አቢይ ፋታ አጥተውና ለሁሉም መልስ አያስፈልግም ብለው እንጂ አንድ ቀን ልክ ያኔ የሱማሌው ጊዜ ጠፍተው ብቅ ብለው ሴረኞቹን ያሳፈሩ ጊዜ ቢሆንስ ብላችሁ አስባችሁዋል? ወሬና አሉባልታ የፈታው ህዝብ!!
ማሳሰብያ!
ለክቡር አቶ ለማ መገርሳ አስቸኩዋይ፣፣
የላጋጣፎው ቤት ማፍረስ ህጋዊ እንኩዋ ቢሆን ወቅቱ አይደለም ክቡር ለማ፣፣ ይህ በአስቸኩዋይ ይታሰብበት!!! መቀሌ የመሸጉት ሳይፈናቀሉ ላጋጣፎን ማፈናቀል መዘዙ ብዙ ነውና!!!
ይህን የለገጣፎውን ማፍረስ ያስቁሙ ባስቸኩዋይ፣፣ ለምን ይበሉኝ፣፣ ሴረኞቹ ህዝባችን ዬቱን ያህል በኢሞሺን እንጂ በሪዝኒንግ እንደማይሄድ አይጠፋዎትምና ይቺን ክፉ ሀይሎች ተጠቅመው ሊያባሉን ቆርጠዋልና ለጊዜው ይቁም፣፣ ወሬ በፈታው ሀገር ጥቂት ቤተሰብን ይዘው እልፍ አእላፍ እንዲህ እየሆነው ነው ብለው ሙሾ የሚያወርዱና የናንተን “ለሁሉ” ስራ የዖሮሞ ብቻ ነው ለማለት የወዳጅ ጠላት ሁሉ ተነስቱዋልና ለጊዜው ቆም አርጉት፣፣ ትራምፕን የመሰለ ከንቱ ሰውዬ በሽብር ወሬ ውስጥ ነው የመጣው፣፣ ፈጣሪ ይርዳችሁ፣፣

4 COMMENTS

  1. You are a comrade of Girma Kassa who have been demanding special rights for the Shewa -Nefteenya in the name the Shewa Oromoo.

  2. ጉዱካሳ አንብቦ የመረዳት ችግር ስላለህ አዝናለሁ፣፣
    አንተንም በዖሮሚፋ ልሞክርህ ነው ወይስ በእንግሊዘኛው? እስቲ መለስ ብለህ አንብበው የፃፍኩትን፣፣ ዬትኛው ይሆን የበላህ? ሀ) ለ)? ብለህ ብለህ የ ፩ ዶላር ቅፈላዋንም እንድናስቀር ዘመቻ መሆኑ ነው? አንተን ነበር ገመዳ እንዳይሰድብህ እማለደው የነበረው በዖሮሚፋ? እረ ቢያስታጥቅህ ይገባሃል፣፣ ደሞ እኔን ስለ humanity ልታስተምርም ይከጅልሃል? መጀመሪያ የትራምፕን ምሳሌ እንኩዋ ለምን እንዳመጣሁ አንበህ ተረድተህ ነው በኔ ደረጃ ለመወያየት የምፈቅድልህ፣፣ ዛሬ ማምሻውን አቢይ ወይም ለማ መጥተው የሆነ እናንተ ያልጠበቃችሁት መልስ ቢሰጡበት ማፈር እንደሚመጣ እንኩዋ አልተረዳችሁም፣፣ ተመልሼ እንኩዋን መልስ ልስጥህ ቀርቶ ዞሬም አላይህ፣፣ ንገሩኝ ባዮች፣፣

    @gamadaa
    ዬ ጋማዳ፣ ጄቴ? ሀማን ሲንጡቂን፣፣ ኢሱማካሚቱ ሉቡኬ ኛቴ ላታ? ናሙማ ‘ዳብዴቱ ናሚቲ ራቱ ሳኒፋና ዋልናፋኬሲፍታ? አኩማን ሲንጄ’ዴ፣፣ አቲ ዋራ ማቃሌፍ ፋልሚታ ማሌ ዖሮሙማን ቡኬ’ዱምኬሌ ሂን’ዳባኔ፣፣ አማ ናጋሌራ፣፣ “የመቀሌው ሳይፈናቀል እንዴት የለጋጣፎው ” ኢሳንጄዴቱ ሲጉቤሚቲ? 🙂

  3. ጉዱ ካሳ የተባልክ ደካማ በምን ሞራል ነው አንድ ዶላር በየቀን አይዋጣ ብለህ የወረደ ጥሪ የምታቀርበው? ኢትዮጵያን እወዳታለሁ ብለህ አታስቀኝ:: ይህ የፖለቲካ ደላላነት ውጪ ሌላ ትርጉም የለውም::ይህን ዶላር ለዐቢይ አሕመድ ኪስ የምናዋጣ መሰለህ? አንተ ሰውዬውን የመጥላት መብትህ የተጠበቀ ነው ሆኖም ሚሊዮኖች በዐቢይ ይተማመናሉ:: የእናንተ ግዝገዛ ለጊዜው ከወሬ አሟሟቂነትና የወያኔ ፊታውራሪነት አያልፍም::

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.