እነ ሙሏለም አበበ (ሙሏለም ባህል ማዕከል በስሙ የተሰየመው) እና ሌሎች እንዴትና ለምን? በማን? ተገደሉ?

አያሌው መንበር

ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው ለረጅም ጊዜ አጣርቸ ደረስኩበት ያለውን እና በቅርቡ ወደመፅሀፍ እንደሚቀይረው የሚጠበቀውን ማስረጃ በኢሳት በኩል እንደሚከተለው ይፋ አድርጎታል።

በረከትና ቲሙ ድራሻቸውን ካጠፋቸውና ካስገደላቸው ውስጥ እነ ሙሏለም አበበ፣ አቶ ሸጋው ጥሩነህ፣አንዳርጌ አበበና የአቶ ስማቸው ጎበዜን ጉዳይ ጀነራሉ በግልፅ ያብራራል።በረከት ከጠመደህ ያለህ ምርጫ መሞት ወይም ሀገር ጥሎ መሰደድ ነው

1.#ሙሏለም_አበበ (በስሙ ሙሏለም ባህል ማዕከል የተሰየመለት የቀድሞው የኢህዲን ታጋይና የአዲስ አበባ ከንቲባ የጎንደር አማራ) በበረከትና በታደሰ ጥንቅሹ እንዴት ተገደለ?

ታደሰ ጥንቅሹ የሙሏለም አራቱን ጥበቃዎችን ወደ ባህር ዳር እንዲሄዱ ካደረገ በኋላ በማግስቱ አቶ ሙሏለም ስብሰባ ሲመራበት ከዋለው ቢሮ ውስጥ በተጠመደ ቦንብ እንዲገደል ተደረገ።ምክንያቱ ደግሞ የእነ በረከት ጋር የሀሳብ ልዩነት ደሴ በነበረው ስብሰባ ላይ አቋም ይዞ ስለወጣ ጥርስ ተነክሶበት ነበር።ያነሳው ሀሳብም “ችግሩ ያለው ከፍተኛ አመራሩ ነው፣ ለምሳሌ አቶበረከት ሁለት መኪና አለው።ይህንን ሳንታገል ለምን የታችኘው አባል ላይ ግለኝነት ችግር አለበት ብለን እንጭንበታለን? ብሎ ተቃውሞ ነበር።በዚህም መጀመሪያ ከከንቲባነቱ ተነሳና ክልል ተላከ።ከክልል ምስራቅ ጎጃም ለድጋፍ እንደሄደ በተቀነባበረ ስልት ተገደለ።

2.#ሸጋው_ጥሩነህ (በብአዴን/ ኢህዴን የሪጅን አመራር ቡድን ውስጥ በረከት፣ አዲሱ፣ ታደሰ እና ሸጋው ጥሩነህ የሪጅን ቡድን ሁነው ይሰሩ ነበር።አቶ ሸጋውም ልክ እንደ ሙሏለም በረከት ፅፎት ለውይይት በቀረበው ሰነድ ላይ ተቃውሞ በማናሳታቸው ዞኑ ሳያውቅ ወደ ሁለቱእጅ እነብሴ ለተልዕኮ ሂደዋል ተብለው ሽፍታ ገደላቸው በማስባል በረከት አስገድሏቸዋል።
አቶ ሸጋው በረከትን የተቃወሟቸው በረከት በፅሁፉ “አማራ ክልል የትምክህት ማዕከል ነው፣ የኢህአዴግ የስጋት ቀጠና ነው በተለይም ሸዋና ምስራቅ ጎጃም” የሚል ነገር በማካተታቸው ነው።አቶ ሸጋው ይህንን በእጅጉ ተቃውመው ነበር።ነገር ግን ተገደሉ።

3.የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪና የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ የነበሩት አቶ #አንዳርጌ_አበበ እነ አቶ #ስማቸው_ጎበዜ አንዱ የቀን ሰራተኛ ሌላኛው ከ16 ዓመት እስራት በኃላ አለም በቃኝ ብሎ ገዳም ገብቷል።

አቶ አንዳርጌ እነ በረከት የገደሉትን ሙሏለምን ወንጀሉን ገልብጠው በውሸት ከሰውት 9 ዓመት ታስሮ ከተፈታ በኋላ እንደገና በቀይ ሽብር እንዲከሰስ ተደርጎ ስድስት ዓመት ታሰረ።ይህንን ጨርሶ ከወጣ በኋላ ነው እንግዲህ ምን አለም አለኝ ብሎ ገዳም የገባው።

አቶ ስማቸው (በፎቶው የሚታየው) ደግሞ ከስራው አባረውት ሌላ ቦታም እንዳይቀጠር አደረጉት።ቤኒሻንጉል ክልል ሂዶ ቡናና ሻይ ተቋም ተቀጥሮ ሲሰራ እነ በረከት በማየታቸው ያረጋል አይሸሽምን ነግረው ስማቸውን እንዲያባርረው አደረጉት።
መጨረሻም የቀን ስራ በስድስት ብር ቢቀጠርም እዛም ሂደው እንዲባረር አስደረጉት።በመጨረሻም ሚስቱም ሞታበት ነበርና ከገጠር እህቱን አስመጥቶ ጠላ እያስጠመቀ እርሱ ራሱ ጠላ እያሳለፈ ሊኖር ተገደደ።አሁን ወደ ንግዱ ገብቷል ተብሏል።

ልሣነ ዐማራ- Amhara Press ይህንን ጉዳይ ከቦታው ድረስ ተጉዞ ሁለቱን ግለሰቦች ቢያናግራቸው ደስ ይለኛል።አማራ ቴሌቪዥንም ይህንን ታሪክ ቢያንስ ሁለቱ ግለሰቦች ህይወታቸው ሳያልፍ ቢሰራው መልካም ነው።

ይህንን መረጃ ብርጋዴር ጀነራል መላኩ ሽፈራው በተከታዩ ቪዲዮ በማስረጃ ያብራራዋል።

በረከትና ቲሙ ማለት እንዲህ ናቸው።

4.ያራያው መብረቅ ሀውጃኖ (ይርጋ አበበ)ም አገዳደሉ ይለያይ እንጅ ምክንያቱ በተመሳሳይ ህወሃትን መቃወሙ ነው።ሀውጃኖ “ህወሃት ጠባብ ድርጅት ሁና አማራን ልትጨቁን እየተጒዘች ነው ሀይ ትባል” በማለት ባለ 41 ገፅ ሰነድ በማዘጋጀቱ ነው በእነ ህላዊ ፊትለፊት ተጋጥሞ ያለፈው።ስለ ሀውጃኖ አገዳደልም ባለፈው አመት በዝርዝር መፃፌ ይታወሳል።ሀውጃኖም ልክ እንደ እነ ሙሏለም በተቀነባበረ ስልት አዲስ ዘመን ላይ ስብሰባ እያሉ እንዲታሰር ታዝዞ ሊይዙት ሲሉ ያውቃቸው ነበርና የትግል አጋሩን ገድሎ ራሱን አጥፍቷል።መቃብሩ አዲስ ዘመን ሲሆን ወደ ራያ ወስዶ በክብር ለማሳረፍ እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

ስለ አገዳደላቸው የሚያብራራውን የጀነራሉን ንግግር የያዘውን ሊንክ የኮሜንት መስጫው ላይ አያይዠዋለው።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.