የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የስራ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል

የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የስራ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው ተነሱ
የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የስራ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው ተነስተዋል፡፡

ከሀላፊነታቸው የተነሱት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮማንደር አማኑኤል ረዳ እና ምክትላቸው መሆኑን ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ ባለፈው ቅዳሜ ዕለት ከመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ጋር መነጋገራቸውን ተከትሎ ነው የስራ ሀላፊዎቹ ከስልጣናቸው እንዲነሱ የተደረገው ተብሏል፡፡

ከሀላፊነታቸው በተነሱት የስራ ሀላፊዎች ምትክ አቶ አህመድ መሀመድ ዋና ዳይሬክተር፤ ኮማንደር ተሰማ ነጋሽ ደግሞ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመዋል፡፡

በባለስልጣኑ የተደረገው ሹም ሽር በመስሪያ ቤቱ ያለውን መልካም አስተዳደር ችግር ለመፍታትና ተቋሙን በተሻለ መንገድ ለማዋቀር በማሰብ የተሻለ አቅም ያለው አመራር ለመመደብ እንደሆነ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.