አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች እንጂ የ ኦሮሞ ብቻ አይደለችም!!!

“ቄሮዎች” ኢትዮጵያን በኦሮሚያ ለመቀየር?  እሱ እንኳን ሲያምራችሁ ይቅር ።
እንዴ ዝም ሲሏችሁ ፤ሲያከብሯችሁ እወቁ እንጂ የምን አዋራ ማስነሳት ነው።
Ethiopians wave national flags and celebrate in the streets of Addis Ababa

አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች እንጂ የ ኦሮሞ ብቻ አይደለችም!!!  የ ‘ኦነግ’ን አርማ መስቀል መብታችሁ ነው።በአዲስ አበባ ውስጥም እናንተ ብቻ ሳትሆኑ መላው ኢትዮጵያዊ እኩል መብት እና ስልጣን አለው። የኢትዮጵያን ባንዲራ መናቅ ግን ዋጋ ያስከፍላችኋል! እናም ቆም ብላችሁ አስቡ።

የሆነው ሆኖ ግን በ ኦሮሞ ምሁር ነን ባዮች እና እንደ እስስት ቀለሙን እየቀያየረ የተንኮል መርዙን በሚረጨው ጃዋር መሀመድ እየተጋለባችሁ አገር ለማጥፋት አትንቀሳቀሱ። እስቲ ለ 21ኛው ክ/ዘ የሚመጥን አስተሳሰብ ይዛችሁ ኑ’ና አስገርሙን በምታምኑት ነገር እንለምናችሁ!?
በነገራችን ላይ ኢትዮጵያ ማንንም ጠበቃ ማንንም ወታደር አያስፈልጋትም። እራሷ ጠላቷን ቀን ጠብቃእስከወዲያኛው አፈር ታለብሳለች። ባንዲራዋን የናቀውን የዘለአለም ባርነትን ታከናንበዋለች።
ኢትዮጵያን ማፍረስ ሲያምራችሁ ይቅር። የህልም እንጀራ ነው። እንደው ልባችሁ ጠማማ ሆኖ፣ አይናችሁ ተጋርዶባችሁ ፣ከመሰሎቻችሁ ውድቀት መማር አቅቷችሁ ነው እንጂ ሩቅ ሳንሄድ ከትናንትናው ከወያኔ ውድቀት መማር እና አደብ መግዛት በተገባችሁ ነበር።
እንዴ ምነው አዲስ አበባ ላይ ሙጥኝ አላችሁ ?
እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ አዲስ አበባ ያለማች ባድማ መሬት ብትሆን ኖሮ  ይህን ሁሉ ወከባ ትፈጥሩ ነበር? አይመስለኝም ። እስቲ እባካችሁ ህዝብን ለመበጥበጥ ሀገርን ለማፍረስ ከምትዳክሩ እስቲ ሌላ አዲስ አበባን ገንቡ እና ደማቅ ታሪክ ፃፉ። እኛም እናድንቃችሁ፤ ያለማወላወል እንደ ዶ/ር አብይ አህመድ እና እንደ አቶ ለማ መገርሳ ምርጦቻችን እናድርጋችሁ።
እኔ ግን የእናንተን አድሮ ቃሪያ መሆን እና ልበ ጠማማነት ስመለከት በጣም እያሳሰበኝ የመጣው ነገር የ ኢትዮጵያ ህዝብ ይኸው ያገኘውን የነፃነት ተስፋ እያጣጣመ 5 ወር አለፈው። ይህ እንዲመጣ ትልቅ ስራ የሰሩት ደግሞ ከእናንተው የተገኙት ዶ/ር አብይ እና ኦቦ ለማ መገርሳ ናቸው። እናንተ ግን ዛሬም እያለቃቀሳችሁ ነው። አሁንም የመጣውን እድል በልበ -ቀናነት እና በክብር ማ ስተናገድ አቅቷችሁ አሁንም ለሌላ ተጨማሪ ዘመናት ስታለቅሱ እንዳናይ።
የኢትዮጵያ ህዝብ ትልቅ ህዝብ ነው።ኢትዮጵያን እስካለ ድረስ “ከየትኛው ብሄር መጣህ? እምነትህ ምንድነው?” ጭንቀቱ እንዳልሆነ በተግባር አሳይቷል።
በነገራችን ላይ እነ አቶ ጃዋርም ሆኑ ሌሎች ፀረ ኢትዮጵያ አካላት አገር ውስጥ መግባት የቻሉት እኮ በኢትዮጵያዊነት ይሁንታ ቪዛ ስለተፈቀደላቸው እንደሆነ መታወቅ አለበት።
የሆነው ሆኖ ወንድሞቼ አደብ ግዙ። ለማንም ስትሉ ሳይሆን ለራ ሳችሁ ስትሉ። ምክንያቱም ከማንም ጋር ሳይሆን ችግር እየፈጠራችሁ ያላችሁት ከ ኢትዮጵያ ጋር ነው አደጋ አለው ከባድ አደጋ።
መስከርም በቀለ

4 COMMENTS

  1. aye y Y ETHIOPIAN bandira yenaqe MNM sew yelem..gin y minilik y nefxengan bandira b oromo hizb nidetun miyanesanw.dgmom b hige mengistu teqebayinet yelewum mikiniyatum y nefxenga bandira teqeyiro wede kokeb alebet teqeyirewal……Oromo mebtun maskeber bichanew mifeligew..

  2. Right on! Someone has to say it.
    What the heck! These groups don’t respect or beleive in Ethiopia or Ethiopian history, Ethiopian national language. They don’t tolerate differences. They’re putting their own fellow people in the dark age.You know what? Woyane put these people up in the sky with their endless demands.

    Woyane is the one who screwed us up. They should thank Woyane for listening their crocodile tears for many years now. Under the name of Democracy Woyane let them name, rename historical Ethiopian cities. woyane let them re- fabricate their own history, falsified Ethiopian history, allowed them to create their own ridiculous writing style, even paved the way for these group to create their own nation. How far they want to push our button the good, respectful, welcoming, patriotic Ethiopian people? What makes them so important to get all these privileges over the rest of the nation? They totally getting out of control. We’re awake now! Enough already. Either these groups are with Ethiopia and Ethiopians or against us, Enough already!

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.