የጠቅላይ ሚንስትሩ የእጅ ሰዓት 5 ሚልዮን ብር ተሸጠ አምቦ የኦሮሞ ነፃነት ሀውልት ናት – ዶክተር አብይ አህመድ

የጠቅላይ ሚንስትሩ የእጅ ሰዓት 5 ሚልዮን ብር ተሸጠ

አምቦ የኦሮሞ ነፃነት ሀውልት ናት – ዶክተር አብይ አህመድ

#Yonas Alemayehu

ለአምቦ ልማት የጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድን የእጅ ሰዓት በጨረታ 5 ሚልዮን ብር ተሸጠ

ትናንት ምሽት በ #Hyatt Regency ሆቴል በነበረው ለአምቦ ከተማ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ወቅት የጠ/ሚር አብይን ሰአት በጨረታ 5 ሚልዮን ብር የገዙት አቶ ገምሹ በየነ (የኢሊሌ ሆቴል ባለቤት) ናቸው።

“ዕውቀትና ሀብት ድንበር የለውም፡፡”

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለአምቦ ልማት የእጅ ሰዓታቸውን በጨረታ በ5 ሚ ብር ባበረከቱበት መድረክ ላይ ከተናገሩት

ሌሎች:
– አቶ ተክለብርሀን አምባዬ 1 ሚልዮን ብር

– ድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ 100ሺ ብር

– ሌሎችም እስከ 15 ሚልየን ብር ሲሰጡ አምሽተዋል

… አቶ በላይነህ ክንዴና ሜድሮክን ለግሰዋል።

ጠ/ሚሩ፣ የክልሉ ፕሬዝዳንት እና የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ በተገኙበት በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን “ምነው አምቦ?” ግጥም የተጀመረ በሀያት ረጀንሲ ሆቴል የተካሄደ የገቢ ማሰባሰብያ መድረክ ነበር። በዚህም መሰረት:

1. 12ሺ ተማሪ ማስተናገድ የሚችል በሃገሪቱ የመጀመሪያው የሚሆን ስታንዳርዱን የጠበቀ ሃይስኩል ት/ቤት- (155-170ሚ ብር)

2. 20ሺ ሰው በመቀመጫ የሚያሰተናግድ አለም አቀፍ ስታድየም- (350-400ሚ ብር) እና

3. የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን የአርት ጋለሪ- (እስከ 250ሚ ብር) የገቢ ማሰባሰቢያው መነሻ ፕሮጀክቶች ነበሩ።

አምቦን ለመደገፍ በአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አስተባባሪነት በተደረገ የገቢ ማሰባሰቢያ የእራት ፕሮግራም ጠ/ሚሩ ከሃገር መሪ በስጣታ የተሰጣቸውን የእጅ ሰዓት ለጨረታ ባቀረቡት የተገኘ 5 ሚሊየን ብር መነሻ ከሁሉም የሃገሪቱ ክፍል ባለሃብቶች በጥቅሉ 350 ሚሊየን ብር ለመሰብሰብ ተችሏል። የእርዳታ የባንክ ሂሳብ ቁጥርም ይፋ ሆኗል።

በምሽቱ ጠ/ሚሩ ለአምቦ ህዝብ ይህችን መልዕክት አስተላልፉልኝ ብለዋል፦

” በኦሮሚያ እያለሙ ያሉ የሌሎች አካባቢ ባለሃብቶች በክልሉ በነፃነት እንዲሰሩና ምንም ስጋት እንዳይገባቸው እነርሱን በመጠበቅ ግንባር ቀደም ሁኑ”

ለአምቦ ከተማ እርዳታ ማድረግ ልምትሹ

የአካውንት ስም፦ የአምቦ ከተማ እድገት
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ Acc.No. 1000273326417

የኦሮሚያ ኢንትርናሽናል ባንክ Acc.No. 1014375

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ Acc.No. 1000044088421

አዋሽ ባንክ No.01307213953401

(ጌጡ ተመስገን) FB የተገኘ

1 COMMENT

  1. please take the revered and the quintessential Ethiopian name, Laurriet Tsegaye GebreMedhin out of the dirty woyanes crowd such as the con artist abiy.

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.