የቀን ጅቦች ከቤተ መንግስት ከተባረረሩ በኋላ የኦነግ ደጋፊ መስሎ በመቅረብ ፋሽኑ ቢያልፍበትም እንደለመዱት አማራን እና ኦሮሞን በማጋጨት 

ተስፋ የቆረጡት እና ድባቅ የተመቱት የአሮጌዉ ስርአት ቁማርተኛች(የቀን ጅቦች) ግጭቶችን
ብሔር ተኮር እንደሆኑ በማስመሰል እና 27 አመት ሙሉ አሸባሪ ጠባብ ሲሉት የኖሩትን ድርጅት #ኦነግን ማለቴ ነዉ ዛሬ ላይ ከቤተ መንግስት ከተባረረሩ በኋላ እነሱ የዚህ ድርጅት ወዳጅ እና ደጋፊ መስሎ በመቅረብ ፋሽኑ ቢያልፍበትም እንደለመዱት አማራን እና ኦሮሞን በማጋጨት
በግርግር ድጋሜ ወደ ቤተ መንግስት ለመግባት ሌት ተቀን የለመዱትን ሰይጣናዊ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ።
ስለዚህ ወጣት ሆይ ሰከን በል ። ነገሮችን በሰከነ አይምሮህ ተርጋግተህ አስብ። በስሜት መነዳት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል።
በጥቃቅን ልዩነቶች ምክንያት ህዉከት እና ግርግር ፈጥረህ በስንት መስዋእትነት የተገኘን ነፃነት በድጋሜ ለቀን ጅቦች አሳልፈክ ትሰጥና ታሪካዊ ዉርደትክን እንዳትጎናፀፍ። ወጣት ሆይ ተጠንቀቅ!
በድጋሜ ለወያኔ መጠቀሚያ እንዳትሆን!

ፊታውራሪ ገበየሁ

 

3 COMMENTS

  1. ውድ ፊት አውራሪ ልክ ነህ ይህ ሀሳባቸው አይሰምርም ቢሆንም እንኳ ሊሆን የሚችለው ራሱን አብን እያለ በሚጠራው ከፋፋይ እና ጎጠኛ ቡድን እና ሌት ተቀን ጠብ አጫሪ ጽሁፍ በሚፈበርኩ ደጋፊዎቹ በነ ጌታቸው ሽፈራው ፣ ግርማ ካሳና መስል ገልቱዎች ምክንያት ነው ።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.